Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2021-09-12 15:25:03 #ሰላም_እለኪ

ሰላም እለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ማርያም እምነ ናስተበቊዐኪ
እምአርዌ ነዓዊ ተማሕፀነ ብኪ

በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ ማኅበረነ ዮም|፫| ድንግል ባርኪ

@wdasemaryam
@wdasemaryam
Share
Share
#✥ደሳለኝ✥
እልልልልልል
እልልልልልልልልልል


እልልልልልልልልልልልልልል
3.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 20:03:49 የ2014 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
፩. ዘመን፡ ዘመነ ማርቆስ
፪. አዲስ ዓመት፡ ቅዳሜ መስከረም 1
፫. በዓለ መስቀል፡ ሰኞ መስከረም 17
፬. ጾመ ጽጌ፡ ረቡዕ መስከረም 26
፭. ጾመ ነቢያት (ጾመ ልደት)፡ ረቡዕ ኅዳር 15
፮. በዓለ ልደት፡ ዓርብ ታህሳስ 29
፯. ጾመ ገሃድ (ጋድ፣ ጾመ ድራር ጥምቀት)፡ ማግሰኞ ጥር 10
፰. በዓለ ጥምቀት፡ ረቡዕ ጥር 11
፱. ጾመ ነነዌ፡ ሰኞ የካቲት 7
፲. ዐቢይ ጾም፡ ሰኞ የካቲት 21
፲፩. በዓለ ደብረ ዘይት፡ እሁድ መጋቢት 18
፲፪. በዓለ ሆሳዕና፡ እሁድ ሚያዝያ 9
፲፫. በዓለ ስቅለት፡ ዓርብ ሚያዝያ 14
፲፬. በዓለ ትንሳኤ፡ እሁድ ሚያዝያ 16
፲፭. ርክበ ካህናት፡ ረቡዕ ግንቦት 10
፲፮. በዓለ ዕርገት፡ ሐሙስ ግንቦት 25
፲፯. በዓለ ጰራቅሊጦስ፡ እሁድ ሰኔ 5
፲፰. ጾመ ሐዋርያት፡ ሰኞ ሰኔ 6
፲፱. ጾመ ድኅነት፡ ረቡዕ ሰኔ 8
፳. ጾመ ፍልሰታ፡ እሁድ ነሐሴ 1
፳፩. በዓለ ደብረ ታቦር፡ ዓርብ ነሐሴ 13
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ ፣ ከ2013 ዓ.ም ወደ 2014 ዓ.ም በሰላም በጤና ያሻግረን፤ አሜን። ለይኩን።
@wdasemaryam
Share.
Share.
5.8K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 20:49:07
ነሐሴ ፳፰ እንኳን ለአበው ቅዱሳን አብርሃም: ይስሐቅ እና ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይማረን በረከታቸው ይደርብን አሜን!!!
@wdasemaryam
@wdasemaryam
4.3K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 11:19:21
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ኃያላን ሊቃነ መላእክት በፊትህ መቆም የማይቻላቸው። አንተን ልባቸው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ጭፍሮች በሕዝብ አደባባይ ፊት አቆሙህ አቤቱ ! !
ፈጣሪየ ክርስቶስ ሆይ፤
ያለመጉደል እግዚአብሔር ዘሲና እግዚአብሔር ዘግብፅ እየተባልክ የምትመሰገን ዘንድ እግዚአብሔር ነህ። ዬ ዬ ዬ ስለኛ እንጨት ላይ ሰቀሉህ። አቤቱ ! አዲስ በታነፀ መቃብር መቃብር ጨምረው ቀበሩት። አቤቱ ! ! ።
ተማኀፀንኩ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
መጻጻውን መሪር ሐሞት በአጠጡህ ጊዜ ሁሉ ተፈጸመ በማለት በ 9 ሰዓት በገዛ ሥልጣንህ ነፍስህን ከስጋህ ለለየህባት ፀዓተ ነፍስህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
የኃያላን ጌታ የፍጥረታትም ሁሉ ፈጣሪ እንደ መሆንህ በዚያች ነፍስህ ከሥጋህ በተለየችበት ሰዓት የሲኦል ጠባቂዋ እስኪፈራ ሞት እስኪደነግጥ ድረስ መሬት ተነዋወጠች መቃብራት ተከፋፈቱ።
ተዘከረነ እግዚኦ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
አስቀድሞ ፊያታዊ ዘየማንን እንዳሰብከው አቤቱ አዳኝ ቤዛ በሚሆን መስቀልህ አስበን።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ ቸር ጠባቂ ነህና እንደዓይን ብሌን ጠብቀኝ። አቤቱ እኔን መከረኛውን ኀዘንተኛውን ሰው በምስጋናህ የወይን ጠጅ አስደስተኝ አረጋጋኝ።
ኦ ዘአዖሩከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
እጅ እግርህን በመቸንከር የኛን መከራ አሸክመው በቀራንዮ በተራራ ላይ ለአቆሙህ ማቆም ሰላም እላለሁ።ነገር ሊናገር ክሂሎት ይኖረዋል።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ የመልከ ጼዴቅ ምሳሌው ካህን ሆይ አንተ ግን በአንደበቱ መናገር ሲጀምር ባርከው አክብረው በሱላይ ቅዱስ መንፈስህን አሳድር::
ዘጸውአ ስመከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ስምህን የጠራ መታሰቢያህንም ያደረገ እሱ በዚያ በቁርጥ የፍርድ ቀን ከንቱ ሁኖ አይቀርም።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ቅድመ ዓለም የነበርክ ዛሬም ያለህ ለዘለዓለሙም ጸንተህ የምትኖር አምላክ ስትሆን የታሠሩ አገልጋዮችህን አንተ ታስረህ ፈታሃቸው በሞትህም ሞተህም የሞቱትን ወገኖችህን አስነሳሃቸው።
ለኀጡአ ምግባር
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ሃይማኖት ስንዃ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ አነስተኛው አገልጋይ ማደሪያ ቤት መኖሪያ ቦታየ ከቅዱሳኖችህ ጋር ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን አቤቱ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከከንቱ ሞት አድነኝ።ሁሉ ከንቱ ነው። የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው። ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።
ስብሐት ለከ
አቤቱ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ምስጋና ይገባል። አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ የምትሆናቸው ለአንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።
አቤቱ ነፍስና ስጋን አዋህደህ በምግባር ሃይማኖት አጽንተህ የምታከብራቸው ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።
አቤቱ በመንግስትህ ሽረት በህልውናህ ሞት ኀልፈት የሌለብህ ለአንተ ለንጉሥ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል አቤቱ የቅዱስ አብ አካላዊ ቃል ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
አቤቱ አምልካችን ህያው ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ እንደ ቸርነትህ ሀገራችን ኢትዮጵያ አስባት
@wdasemaryam
@wdasemaryam
4.2K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 11:19:21 ግተህ የተቀመጥህ አንተ ነህ። የአብን ፈቃድ ትፈጽም ዘንድ ከሰማየ ሰማያት ወደዚህ ዓለም የመጣህ አንተ ነህና ክቡር ምስጉን አምላክ ነህ።
ለአማዑቲከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የኃጥኡን ሰው ውሳጣዊና አፍአዊ ሰውነቱን ለሚቀድሰው ንዑድ ክቡር ለሚሆን ውስጣዊ ገንዘብህና ለአማዑትህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከዚህ ዓለም ጥፋትና ጥል ፡ ጭቅጭቅና ንዝንዝ ሁሉ አድነኝ። በሰማይና በምድር፤ በባሕርና በየብስም ቢሆንም ያለአንተ ቸር ሰው ወዳጅ ንጉሥ የለምና።
ለሕንብርትከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በአምሳለ ቅዱስ መስቀል ማዕተብነ፤ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ለተማተበው ሕንብርትህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ ከችግርና ከፈተና አድነኝ፤ አባትህም በምስሐ ደብረጽዮን በሚያደርገው ታላቅ የምሳ ግብዣ ላይ ይዘኸኝ ግባ ከአንተ በቀር ሌላ የማውቀው ዘመድ የለኝምና።
ለሐቌከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የሲኦልን በር የናሱን መዝጊያ ቀጥቅጠህና ሰባብረህ የብረቱንም ቁልፍ እንደ ሰም አቅልጠህ ነፍሳትን ከሲኦል በአወጣህበት ሰዓት መለኮታዊ ዝናርን ለታጠቀ ወገብህንና ኃይለአርያምን ለተጎናጸፉ አቍያጾችህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
መሐሪ ይቅር ባይ አንተ እግዚአብሔር እንደመሆንህ መጠን በምሄድበት መንገድ ሁሉ ቀናውን ጎዳና ምራኝ። የጽድቁንና ዕውነተኛውን መንገድ ፈጽሞ ለማወቅ አልችልምና።
ለአብራኪከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ከሁለቱ እግሮችህ ጋር ወደ ብሔረ ሞት በፈለሱ ጊዜ በደም ቅንዋት ለተጥለቀለቁ ጉልበቶችህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ቃልህ የማይታበይ ዕውነተኛ አምላክ ነህ፤ አቤቱ ጌታዬ እኔን አገልጋይህን ለመጎብኘት በየጊዜው በመመላለስ ወደ እኔ ና ና አቤቱ ጌታዬ አንተ የዓለም ግርማ ሞገሱ ነህና።
ለሰኰናከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ፈጻሜ ፍቅር ወሰላም ለሆነው ተረከዝህ ሰላም እላለሁ። ዓለሙን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት የወረድህ አንተ ቸር አምላክ ነህ፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
የአርያም ጽንዕ ኃይል ስትሆን እንደደካማ ሰው ክቡዱንና ግዙፉን ዕፀ መስቀል በመሸከም ምንኛ ድካምንና መከራን ልትታገስ ቻልክ። ለዚህ ረቂቅ ትሕትናህ አንክሮ ይገባል።
ለመከየድከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ያለበደልና ያለአበሳ ሰውና መላእክትን የፈጠርክ ሆይ በብረት ችንካር ለተቸነከሩት ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ ጌታ መሐሪ ይቅር ባይና ቸር እግዚአብሔር እንደመሆንህ መጠን በዚያ የቁርጥ የፍርድ ቀን በምትመጣበት ጊዜ ማረኝ ይቅርም በለኝ አቤቱ በፊትህ እንደ እኔ ያለ በደለኛ የለምና
ለአጸብዓከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በለቢሰ ስጋ ለደከሙና ለወዙ ጣቶችህ ሰላም እላለሁ። በጎዳና ላይ በድንጋይ ዕንቅፋት ላልተሰናከሉ ለእግሮችህ አጽፋርም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ፍለጋህ ተመራምሮ ሊገኝ የማይቻል ነው። አቤቱ የወዳጅህ የዳዊት መጽሐፍ እንደተናገረው በዚህ ዓለም ስለዕውነት ስለጽድቅህ የደከመ በወዲያኛው ዓለም የዘላለም ሕይወት እንዳለው አምናለሁ ተስፋም አደርጋለሁ።
ለቆምከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
አይሁዶች ተሰባስበው በቀራንዮ አደባባይ ለአቆሙት አካለ ቆምህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ግዙፍ ሥጋን በተላበሰ አንደበቴ ልመናዬን ሳቀርብልህ አሳልፈህ ለጠላት አትስጠኝ።እንዳንተ ያለ ጠቃሚ ዘመድ በቂ ወገን አይገኝምና።
ለመልክእከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ለጻድቃን ያይደለ ኀጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ሥነ መልክእህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በየጊዜው በነጋ በጠባ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ። በመስቀል ላይ ሳለህ አባት ሆይ፤ ይቅር በላቸው በማለት የተናገርከውን የቸርነትና የርኀራኄ ቃል አስቀድሜ ሰምቻለሁና።
ለፀአተ ነፍስከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በመስቀል ላይ ልዩ ልዩ አምላካዊ ተአምራትንና ሕማማተ መስቀል ከተፈጸመ ቡኃላ በገዛ ሥልጣንህ ለተፈጸመው ጸዓተ ነፍስህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ዓለምን ለማዳን በተሰቀልክበት በዚያን ሰዓት እንሆ ጌታዬ ሆይ፤ ፀሐይ ብርሃኑን ከመስጠት ተከልክሎ ጊዜው ጨለመ ጨረቃም ደም ሆነ።
ለግንዘተ ሥጋከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ከጽጌረዳ መዓዛ ይልቅ መዓዛ ላለው ግንዘተ ሥጋህ ሰላም እላለሁ። በኢየሩሳሌም አደባባይ ለሚገኘው መካነ መቃብርህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ሰይጣናዊ በሆነ በይሁዳ ወገኖች ቅናት ሞተህ የሔዋን ልጆች ባልተቀበሩበት አዲስ የሚሆን በታነፀ የሕንጻ መቃብር ተቀበርህ። አቤቱ ሞት የማይገባህ ላንተ ምስጋና ይገባል።
ለትንሣኤከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የመቃብር ጠባቂ ጭፍሮችን አሸብሮ የጻድቃንን ትንሣኤ ለገለጠው ትንሣኤህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በልዩ ትንሣኤህ ጨለማን ካስወገድህ ቡኃላ በግብር አምላካዊ በዝግ ቤት ገብተህ ደቀመዛሙርትህን በጦር የተወጋውን ጎኔን በችንካር የተቸነከሩ እጅ እግሬን ተመልከቱ አልካቸው።
ለትንሣኤከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ከእንቅልፍ እንደመንቃት ለሆነ ትንሣኤህ ሰላም እያልኩ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ተአምራትህን እናገራለሁኝ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ለአዳም ልጆች መድኀን እንደመሆንህ መጠን የእኔን የደካማውን አገልጋይህን ልመና ተቀብለህ አቤቱ ከዚያ ርጉም ከሚሆን ጠላቴ እጅ አድነኝ።
ለዕርገትከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በዓውሎ ንፋስ በእሳተ ነበልባል አምሳል መንፈስ ቅዱስን ትልክልን ዘንድ በነጎድጓድና በመባርቅት የሠረገላ ዘባን ለተከናወነ ዕርገትህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በአንዲት መንግሥትህ መንግሥቱን ለዘላለም አገዛዙም ለትውልደ ትውልድ ነው እያሉ ሰማያውያን መላእክት በየዕለቱ በየሰዓቱ ያመሰግኑሃል።
ለዕርገትከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የቃል ኪዳኑን ሥነ ሥረዓት ለፈጸመ ዕርገትህና ሁሉን ለማዘጋጀት በኃለኛው ዘመን አመጣጥህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ቅድመ ዓለም በጌትነቱ ክብር ከአባትህ ዘንድ የነበረ ወደዚህ ዓለም በዓውሎ ነፋስ አምሳል የላክኸው እሱ መንፈስ ቅዱስ የኃጢአቴን እሾህ በማቃጠል አቤቱ እሱ ኃይሉን ይግለጽ።
አልቦ እምሰብእ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ከሰው ወገን ማንም እንደ እኔ ኃጢአት የሰራ በደለኛ የለም። እንደ አንተም ያለ መሐሪ ይቅር ባይ አምላክ አይኖርም።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ዓለማትን ሁሉ የፈጠርህ ፈጣሪ እንደመሆንህ መጠን በኃለኛው ዘመን በዓለም ላይ ለመፍረድ በምትመጣበት ጊዜ ከጎንህ በፈሰሰው ደም ኃጢአቴን እጠብልኝ አሜን።
አቄርበ ወትረ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ስለኃጢአቴ ሥርየት በጭንቅና በመከራምስጋናን ዘወትር አቀርባለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
የሰማይና የምድር ጌታ እንደመሆንህ እኔ ጎስቋላው አገልጋይህን ኃጢአቴን ይቅር ብለህ ማደሪያዬን ስጠኝ እያልኩ በምለምንህ ጊዜ በዱርም ቢሆን በተራራ ላይ በአስፈላጊው ቦታ ሁሉ በፍላጎት መጠን ምግቤን አዘጋጅልኝ።
አጽምዓኒ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
መሪር የሆነ የሰቆቃው ነገር የምጽፍልህ ነኝና በጆሮህ አድምጠኝ ቅዱሳን በሆኑ እጆችህ ጹሑፌን ተቀበለኝ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
መላእክት ሊቃነ መላእክት በመንቀጥቀጥ በፊትህ የሚቆሙ አንተ በጲላጦስ አደባባይ ቆምክ አቤቱ። ዬ ዬ ዬ ስለኛ እንደዚህ ዓለም ሰው ተቆጠርክ አቤቱ። ዬ ዬ ዬ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ ጎንህን በጦር ተወጋህ አቤቱ! ።
ኦ ሊቀ ካህናት
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
አቤቱ የካህናት አለቃ ስትሆን እንደ ቀማኛ እንደዐመፀኛ እንደወንጀለኛ የራሄልና የልያ ልጆች የኃሊት አሰሩት።አቤቱ!።
ፈጣሪየ ክርስቶስ ሆይ፤
ስለኛ ለሞት ተላልፈህ ተሰጠህ አቤቱ።
ዬ ዬ ዬ ስለኛ በጦር ወጉህ። አቤቱ ዬ ዬ ንጹህ ክቡር ስጋህን መሬት ሸፈነው አቤቱ! ! ።
ኦ ክርስቶ
2.5K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 11:19:21 መልክአ መድኃኒዓለም
ለዝክረ ስምከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ምስጋና የሁል ጊዜ ተግባራቸው የሆነ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ጻድቃን ሰማዕታት ተመራምረው ለማይደርሱበት ለስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በሞትህ ሞትን ታጠፋው ዘንድ ከርቤ የተቀላቀለበትን መራራ ሀሞትን ስለ እኔ ሕይወት የጠጣህ የአቀረብኳትን አነስተኛ የምስጋና መባየን በቸርነትህ ተቀበል።
ለስእርተ ርእስከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
እኛን ስለማዳን መከራን ለመቀበል ዘንበል ላለው ርእስህና ስእርተ ርእስህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከሰማየ ሰማያት ወርደህ ከድንግል ማርያም ተወልደህ በሥጋ ብእሲ በሕጻን አርአያ በተገለጽክበት ወራት እናታችን ሔዋንን ያሳተ ከይሲ ዲያቢሎስ ፈራ ደነገጠ በኀዘንና በልቅሶም ተዋጠ።
ለገጽከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ከሁለቱ ቀራንብቶችህ ጋር ለሚያንባርቀው አመጸኛንና ከዳተኛን በማስደንገጥ ብቻ ለሚያንበረክከው ለገጽህ ግርማ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
የኃጢአትን ማእበል ባሕር እንደምትገስፀው መጠን። አቤቱ በገሃነመ እሳት ከመቃጠልና ከሲኦል ትላትል ቁንጥጫ በቸርነትህ አድነኝ።እሳቱ የማይጠፋ ትሉ የማያንቀላፋ እንደጋለ ብረትና እንደተሣለ ምሳር ነውና።
ለአዕይንቲከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የቅዱሳንን ጥሪ ለሚሰማ ዕዝንህና ድሆችን ለሚመለከቱ ዓይኖችህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በላይ በዘባነ ኪሩቤል ተቀምጠህ የባሕሮችን ጥልቀት ትመለከታለህ። አቤቱ ሰውነቴን ከሰይጣን ፈተና ከአመፀኛ ከተንኮለኛ አድናት። አቤቱ ባሕሩን አድርቀህ ደረቁን ሳር የምታለመልም ክሂሎት ያለህ አሸናፊ አምላክ ነህና።
ለመላትሒከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ሕማመ ተጾፍዖን ለመቀበል ለተዘጋጁ ጉንጮችህ ሰላም እላለሁ። ኀሊናን ደስ ለሚያሰኙ አዕናፍህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ ሠራዊተ መላእክት እየተንቀጠቀጡ በፊትህ የሚቆሙ አንተ በቀያፋና ሐና አደባባይ ቆምህ። አቤቱ የኔ ጥፋት በአንተ ዘንድ ተፈላጊ አይደለምና እንደሰማሁትና እንደማውቀውም ሁሉ በመስቀልህ ቤዛነት አድነኝ።
ለአፉከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
አቤቱ እንደከረመ የወይን ጠጅ የሐሞትን መራራነት ላጣጣመ አፍህ ና ከናፍርህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ አምላካዊ ተአምራት የማድረግ ስልጣን በአንተ እጅ በመሆኑ። ዳግም በምትመጣባት በዚያች ዕለት ሑሩ እምኔየ የምትለውን የፍርድ ውሳኔ እንዳታሰማኝ በቸርነትህ እማፀናለሁ።
ለአስናኒከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ላይ ሣለህ ስለዓለም ነፃ መውጣት የሰበከ አንደበትህና መለኮታዊ አስናኖችህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ቃልህ የማይታበል የማይለወጥ ነውና መልአከ ሞት ነፍሴን በፊትህ ባቆማት ጊዜ አቤቱ ገጸ ምሕረትህን አትመልስብኝ።
ለቃልከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
አባት ሆይ፤ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ። በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህንም በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እሳት ትንፋሽህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከዚያ እስከዚህ ድረስ የሰራሁትን ኃጢአቴን ይቅር በል። አቤቱ ቅዱስ ስጋህን ከበላሁ ክቡር ደምህን ከጠጣሁ ቡኃላ ነፍሴ ጥፋት እንዳያገኛት በፍጹም ትጋት ደጅ እጠናለሁ።
ለጕርዔከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ክቡር ልዑል ለሚሆን ጕርዔህ ሰላም እላለሁ። በገመድ እየሣቡ ለጎተቱት ክሣድህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በቀራንዮ አደባባይ የተሰቀልከው ለሰው ልጅ ደህንነት እንደመሆኑ መጠን ስለእናትህ ስለድንግል ማርያም ብለህ ምሬሃለሁ ይቅር ብየሃለሁ በለኝ። ከአንተ በቀር ቸር ይቅር ባይ የለምና።
ለመታክፍቲከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በጎልጎታና በቀራንዮ አደባባይ አርዑተ መስቀልን ተሸክመው ለተንገላቱ መተክፍትህ ሰላም እላለሁ። ዙፋኑን በዘባነ ኪሩቤል ለአዘጋጀ ዘባንህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በቀል የሌለብህ አምላክ እንደመሆንህ በቅዱሳኖች በወዳጆችህ አማላጅነት እማፀናለሁ። ስማችሁን የጠራ እምርላችኃለሁ ስትል ቃል ኪዳን ገብተህላቸዋልና።
ለእንግድዓከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የአዳምን ዘር ለማዳንና በጠቅላላው ለዓለም ቤዛ ለመሆን ሐፃውንተ መስቀልን ለታቀፉ ክንድህና ደረትህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ለሰውነቴ መልካሙን የዕረፍት ጊዜ ስጣት። አቤቱ ሰውነቴን፤ ነፍሴን የሚፃረሯትን ጠላቶቼን ሁሉ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና አባቴ ሆይ ይቅር በላቸው ብለህ እንዳስተማርከን ይቅርታ ታደርግላቸው ዘንድ እማጸናለሁ።
ለአእዳዊከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ለቤዛ ዓለም ስትል ለፈሰሰው ደምህ፤ ለተቸነከሩና በደም ለተጠመቁ እጆችህ ሰላም እላለሁ። በሌሊት የሚዘዋወረውን ድንገተኛ ጠላትና በቀን የሚጻረረውን የቀትር ኃያለ አጋንንት ለሚያዳሽቀው መለኮታዊ ግርማህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በጎ ነገርን አሰጀምረህ የምታስፈጽም ቸር አምላክ ነህ። አቤቱ ከጎንህ የፈሰሰው ደመ መብረቅ ከላይ ወደታች በተቈለቈለ ጊዜ ድምፀ ጉህናው ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ አስተጋባ።
ለኵርናዕከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
በቅዱስ መስቀል ላይ በተሰቀልክ ጊዜ በግራና በቀኝ ተዘርግተው ለተንሰራፉ ክንድህና ውርቾችህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ ደዌ መከራ ከሌለበት፤ ተድላ ደስታ ከአለበት ኤዶም ገነት ታገባኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
ለእራኀከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የእናታችን የሔዋንን በደሏን ይቅር ትልላት ዘንድ መከራን ለተቀበሉ መዳፎችህና ዓለማትን ሁሉ በመለኮታዊ ጥበብ ለፈጠሩ ዓሥሩ ጣቶችህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪየ ክርስቶስ ሆይ፤
የኃጥአን ነፍስ መጠጊያ አንተ ነህ፤ለዓለምም የምታበራላቸው እውነተኛ ፀሐይ አንተ ነህ።
ለአጽፋረ እዴከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
የዓሠርቱ ቃላተ ኦሪት ትእዛዛት ለተጻፉባቸው ንዑዳት ክቡራት ለሚሆኑ ለእጆችህ አጽፋር ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ክቡር ዳዊት እንደተናገረው ጠላቶቼ ሰውነቱ ዱር ለዱር ተቅበዘበዘ እያሉ እንዳይዘባበቱብኝ በየጊዜው በየሰዓቱ በየዕለቱ ልመናዬን ሳቀርብልህ ፈጥነህ ተቀበለኝ እንጂ ቸል አትበለኝ።
ለገቦከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ኀዘን ትካዜን ለሚያስወግድ መለኮታዊ ጎንህ ሰላም እላለሁ። በዓለሙ ሁሉ በጭንቅና በመከራ ላይ የሚገኙትንም ለሚያረጋጋ አምላካዊ ከርስህም ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
መድረቅ መጽነፍ የሌለበት ባሕረ ምሕረት እንደምሆንህ የቸርነትን ቃል መቼ ታሰማኝ ይሆን? እያልኩ ሁል ጊዜ አምላኬ አምላኬ እላለሁ።
ለልብከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ናዝራዊ የተባልክ ለአንተ ለእግዚአብሔር ነቢይ ወመንፈሳዊ ለተባልክ ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልቡና ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ስለትሕትና ሕጻን ወአረጋዊ እየተባልክ የምትመሰገን አንተን በመስፍኑ በጲላጦስ አደባባይ እንደወንጀለኛ አገልጋይ ባሪያ የሌዊና የይሁዳ ልጆች የሚሆኑ ካህናት እንዴት ሊገርፉህ ተበረታቱ አቤቱ ለትዕግሥትህ አንክሮ ይገባል።
ለኵልያቲከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
እንደ አጥቢያ ኮከብ በግራ በቀኝ ሆነው ለሚያበሩ ሁለት ኵልያቶችህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በአካል ሦስት በባሕርይ አንድ እግዚአብሔር እየተባልክ ትመካለህ። አቤቱ አንተ ክርስቶስ ለኃጥአን ስንዃ ሕይወታቸው ነህና፤ አቤቱ ስንልህ በከንቱ እንዳንጠፋ ጠብቀን።
ለኀሊናከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ዳግመኛ ከሰሜን እስከ ደቡብ በዓራቱም ማዕዝነ ዓለም የብርሃኑ ጸዳል ለሚንጸባርቀው ኀሊናህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
በዘባነ ኪሩቤል ላይ ዙፋንህን ዘር
2.4K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 11:19:01
2.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-01 11:44:04 ​​#ነሐሴ_26
#አቡነ_ሃብተ_ማርያም_ጻድቅ

እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::

ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::

ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::

የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::

ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::

ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን መከፋትን አላሳደሩም::

በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::

"1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ
2.ስለ ምናኔሕ
3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ
4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ
5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ
6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ
7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::

ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::

አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@wdasemaryam
2.6K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-01 11:43:52
2.3K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-30 06:09:29 እንኳን ለፃድቁ ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእለተ ቀናቸው የልባችሁን መሻት ይሙሉላችሁ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ አሜን አሜን አሜን::
አሜን አሜን አሜን
ገድሉ ታአምራቱ
*************************
ገድሉ ታአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋህዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለሐይማኖት ዘኢትዮጵያ
አ.ዝ .........................//
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፍር የታጠቀ
ንጹህ ባሕታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የፀጋዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አሰከተለ
አ.ዝ .........................//
ደካማ መስሏቸው በአንደ እግሩ ሲያዩት
ባለ ስድስት ክንፉ ተክልዬ የእኛአባት
እሱስ አንበሣ ነው ይናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አ.ዝ .........................//
ከካህናት መካከል ህሩይ ነው ተክልዬ
መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ
እትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቷን ባረካት
አ.ዝ .........................//
የባረከው ውኃ የረገጠው መሬት
ገላው ያረፈበት ሆኗል ፀበል እምነት
ኑና ተመለከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክልዬ ዛሬም እንደ ጥንቱ
@wdasemaryam
@wdasemaryam
✥ደሳለኝ✥
2.8K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ