Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2021-10-21 07:20:11 +++ #ምድረ #ግብፅ ፦ እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ምድረ ግብፅ ሲጓዙ ሦስት ቀን ጫካ ውስጥ ሰነበቱ፡፡

በጣም ተራቡ፣ ተጠሙ፡፡ በበረሃ በረሃብና በውሃ ጥም እንዳይሞቱ እመቤታችን ጸለየች፡፡ ወዲያው የተሠራ ማዕድ /የተዘጋጀ መግብ / መጣላቸው በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢንፍሎን ወደተባለ አገር ሄዱና ርግባዳ ከተባለ ሰው ቤት ተቀመጡ፡፡ ብዙ ሰዎች ዕውቀት ፈልገው ወደ እመቤታችን ይመጡ ነበር፡፡ እመቤታችን ከጥበበኞች ከእስራኤል አገር ስለመጣች ብዙ ጥያቄዎችን ይጠይቋት ነበር፡፡ እመቤታችን ብዙ ምሳሌ እየመሰለች ጥያቄዎቻቸውን ስትመልስላቸው እያደነቁ ይሄዱ ነበር፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዚያች አገር ገዥ ሞተ፡፡ ቤተሰቦቹ መጥተው ለእመቤታችን ነገርዋት፡፡ እመቤታችን ስትሄድ ሞቶ አገኘችው፡፡ የሚያለቅሱትን ሰዎች ዝም በሉ አለቻቸው፡፡ አልቃሾቹ ዝም አሉ ፡፡ በቀኝ እጅዋ ይዛ በእግዚአብሔር ስም ተነስ አለችው፡፡ የሞተው አገር ገዥ ሕያው ሆኖ ተነሣ፡፡ ለለቅሶ የተሰበሰቡት ሰዎች የጣዖቶቻቸውን ስም በመጥራት አጵሎንና አርዳሚስ ሰው ተመስለው መጡ አሉ ፡፡ እመቤታችንም እናንተ የምትሏቸው ጣዖታት አይደለሁም፡፡ ከይሁዳ ምድር ተሰድጄ የመጣሁ ሰው ነኝ ካለቻቸው በኋላ የሞተውን ሰው ማስነሣት የሚቻለው እግዚአብሔር መሆኑን እንዲያውቁና በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አስተማረቻቸው ፡፡ በሀገራቸው ውስጥ የሚኖሩ በሽተኞችን እየፈወሰችላቸው ጥቂት ወራት ተቀመጠች፡፡ ምድራቸውን ባርካ ውሃ አፈለቀችላቸውና በዚህ ተፈወሱ አለቻቸው፡፡ የታመመ ሰውም ሆነ እንስሳ እመቤታችን ባፈለቀችው ውሃ ሲታጠብ ይፈወስ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ራፋን ወደተባለ አገር ሄዱ ፡፡ የራፋን ሰዎች መለከት እየነፉ ወጥተው እመቤታችንን ዮሴፍንና ሰሎሜን በድንጋይ ቀጠቀጧቸው፡፡ እነዮሴፍም ከዚያ አገር ወጥተው ሄዱ ፡፡ በአረብ አንፃር ቄድሮስ ከተባለ አገር ደረሱ፡፡ በተቃራኒው የሚጾሙ የሚጸልዩ ደጋግ ሰዎችን አገኙ፡፡ አገሩም በጣም ደስ የሚያሰኝ ልምላሜ የተሞላበት አገር ነበር፡፡ በቄድሮስ ስምንት ወር ተቀመጡ፡፡ ዮሴፍም እመቤታችንን ሁሉን ነገር ትተን ከዚህ አገር እንቀመጥ አላት፡፡ አገር ለአገር ዋሻ ለዋሻ መንከራተቱን ትተን እንረፍ ማለቱ ነው፡፡ እመቤታችንም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ መቀመጥ አንችልም አለችው ዮሴፍን፡፡ በዚያች ሌሊት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ እመቤታችንን ከዚህ አገር ውጪ አላት፡፡ ከዚያች አገር ወጥተው ወደ ደብረ አሞር ሄዱ፡፡ የተለያየ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ወጥተው ተቀበሏቸው፡፡ እመቤታችን ሁሉንም ፈወሰቻቸው እነዮሴፍ በደብረ አሞር ብዙ ጊዜ ተቀመጡ ፡፡
ከደብረ አሞር ወጥተው ሲሄዱ ጌላውዳ ከተባለ አገር ደረሱ፡፡ በዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው አገኙ፡፡ ርኩስ መንፈስ ከያዘው 70 ዓመት አልፎታል፡፡ ሰውየው አይተኛም ሥጋውን በድንጋይ ይቦጫጭቃል በሰንሰለትም ሲታሰር ሰንሰለቱን ይሰባብራል፡፡ እመቤታችንን ባያት ጊዜ ይቅር በይኝ ብሎ ከእግሯ ስር ወደቀ፡፡ እመቤታችንም ርኩሱንም መንፈስ በእግዚአብሔር ስም ውጣ አለችው፡፡ ርኩሱ መንፈስ ወጣ፡፡ ክፉ አራዊት የርኩሳን መናፍስት መገለጫዎች ናቸው፡፡ ዮሐንስም በእባብና በዘንዶ ዲያብሎስን ሲገልጸው እንዲህ ይላል፡፡ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ ( ራእ . 12÷9 ) ። ርኩሱ መንፈስ የወጣለት ሰው ከአንቺ አልለይም ብሎ እየሰገደ እመቤታችንን ተከተላት፡፡ እመቤታችንም ወደ ዘመዶችህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ንገር አለችው ፡፡
እመቤታችን የተለያዩ ተአምራትን እንደምታደርግ በአካባቢው ተሰማ፡፡ አንድ ሆዱን የነፋው ሀገረ ገዢ መጥቶ ፈውሺኝ አላት፡፡ እመቤታችንም በልጄ እመን ትድናለህ አለችው፡፡ እርሱም አምናለሁ አለ፡፡ ከሆዱም እባብ ወጣለት፣ ከበሽታው ተፈወሰ፡፡ እነዮሴፍን ዘጠኝ ወር ያህል ከቤቱ አስቀመጣቸው፡፡ ከዘጠኝ ወር በኋላ ከቤቱ ወጥተው ሲሄዱ ሊባ የሚባል ባሕር ካለበት አገር ደረሱ፡፡ የዚያ አገር ሰዎች በጅራፍ እየገረፉ አባረርዋቸው፡፡ እነዮሴፍ ቤልቤል ከሚባል ዛፍ ስር አደሩ፡፡ ነገር ግን መልአክ ወርዶ በሰረገላ ወስዶ ካሳደድዋቸው ሰዎች አገር መካከል አስቀመጣቸው፡፡ እመቤታችንም ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ያደሩበት አገር በጅራፍ እየገረፉ ያሳደድዋቸው ሰዎች አገር እንደሆነ አወቀች፡፡ እመቤታችንም የትናንቱ ጅራፍ ተመልሶ እንዳይመጣ ወደ እግዚአብሔር አጥብቃ ጸለየች፡፡ በጅራፍ የገረፍዋቸው ሰዎችም ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለወጡ ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሰዎች የሚቀጣበት መሣሪያው የተለያየ ነው፡፡ አእምሮ ያለውን ሰው አእምሮ የሌለው እንስሳ ያደርገዋል፡፡ ይህ አይነት ቅጣት በጣም የሚታበዩ ሰዎች የሚቀጡበት ነው፡፡ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በትዕቢቱ ምክንያት ወደ አውሬነት ተለውጦ ቤተመንግስቱን ለቅቆ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ሰባት ዓመት ኖርዋል ( ዳንኤል 4÷28-34 ) ፡፡
@wdasemaryam


1.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-20 06:19:12 ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው ቁርአን በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE
61 views| ፼ ωΑνЄ |, 03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 22:01:02 እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
217 views| ፼ ωΑνЄ |, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 06:36:34


ሰብስክራይብ ያድርጎ መረጃ እንዲደርሶ
3.7K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-06 21:59:44


@wdasemaryam
@wdasemaryam
907 views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 17:17:03 እንኳን ለጽጌ ጾም በሰላም አደረሰን

ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኀዳር 5 ያለው አንድ ወር ከአሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ ፤ ዘመነ ጽጌ፤ ተብሎ ይጠራል!

=>ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን በዚህ ወር የፅጌሬዳ አበባ የሚፈካበት ወር ነው ።

ጽጌሬዳ አበባ መአዛው እጅግ ያስደስታል
ለአይንም ይማርካል እመቤታችንም በአበባው እንመስላታለን ጉድፍ የሌለባት ለነፍስም ለስጋም ደስ የሚል ውበት የስጋ ድንግልና በነፍስም ድንግል ናትና
ጾመ ጽጌ እመቤታችን ስደቷን የምናስብበት ነው።

=> ጾመ ፅጌ የአዋጅ ፆም አይደለም የእመቤታችን ፍቅር ያለው ሰው በውዴት ይጾመዋል

=> ፆመ ፅጌ የድንግልን ስደት ለምለም አካላቷ ያልጠና ሰውነቷ በሀሩር በውርጭኝ ያለ ሀጥአቷ እንግልት በማየቷ በረከትን ለማግኘት እንጾማለን ማለት ነው።

=>ፆመ ጽጌ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ከርስቶስ
ከተወለደ በኋላ የጥበብ ሰዎች በኮከብ መሪነት ሲጓዙ ከዛም ኮከቡም ተሰወረ ወደ ንጉስ ሄሮድስም ደረሱ የአይሁድ ንጉስ ወዴት አለ ብለውም ጠየቁ ሄሮድስም ደንግጦ በመልካም አቀባበልም ተቀበላቸው ተነስተውም ሲጓዙ ሄሮድስ የአይሁድ ንጉስ ሲሉት መንግስትነቱ የምድራዊ ንጉስ መስሎትም ንግስናዬን ይቀማኛል ብሎም ተሸበረ የጥበብ ሰዎችም ሲሸኛቸው ስለ ህጻኑ ባገኛችሁት ጊዜ መጥታችሁ ንገሩኝ እኔም እሰግድለት ዘንድ ብሎ ሸኛቸው


=> እነሱም ቀድሞ ይመራቸው የነበረ ኮከብ
ተገለጠላቸው።እየመራ ቤቴሌሄም እየተመሩ ወደ ህጻኑንም ከእናቱ ከድንግል ማርያም እና ከጠባቂዋ ዮሴፍ ጋር በቤቴሌሄም በከብቶች በረት አገኙት እጅ መንሻም ወርቅ እጣን ከርቤ አገቡለት
✥ወርቁ ለንግስናው
✥እጣኑ ለክህነቱ
✥ከርቤው በፍቃዱ ስለሰው ልጆች መሞቱ ያመለክታል።
ከዛም በመጡበት እንዳይመለሱ የእግዚአብሔር መልአክ በህልም ተገለጠላቸው በሌላ መንገድም ወደ ሀገራቸው ሄዱ።

=> እነርሱም ከሄዱ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ተገልጦ እናቱና ህፃኑን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ እስክነግርህም ድረስ በዛ ቆይ አለው። ዮሴፍም እናቱና ህፃኑ ይዞ ስደት ጀመረ.። ሄሮድስም የጥበብ ሰዎች እንዳታለሉት ባወቀ ጊዜ አዋጅ አወጀ የሁዳ ሴቶች ሆይ እርዳታ እሰጣለሁ ልጆቻችሁ አስመዝግቡ ብለዎ አወጀ ከሁለት አመት ጅምሮ ያነሱትንም ህጻናት አሰበሰበ በነዚህ መካከል ሕጻኑ ክርስቶስን ያገኘ መስሎት ሁሉም በሰይፍ አሰየፋቸው ዲያብሎስም ለሄሮድስ በሞቱት ህፃናት መካከል እንደሌለ አማከረው ጭፍሮችም በፈረስ እንዲፈልጉትም ሽልማት አሲዞ ላካቸው ሌላው ሽልማት ሲያገኙት እንደሚሰጣቸው ተናግሮ
✥✥✥
ማቴ 2÷1........
•ጾሙ የበረከት የሰላም ያድርግልን ድንግል ሆይ በስደትሽ የጎበኘሻት ሀገር ኢትዮጵያ ዛሬም ጎብኛት
@wdasemaryam
@wdasemaryam
✥ደሳለኝ✥
1.7K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 17:16:43
1.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 12:37:59



ሰብስክራይብ ይደረግልኝ እባኮ
1.2K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, edited  09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 12:37:00



ሰብስክራይብ ይደረግልኝ እባኮ
1.2K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, edited  09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 21:11:57 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 24-የላዕላይ ግብፁ ታላቁ ተአምረኛው አባት አቡነ ጎርጎርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ አድሊጦስ ዕረፍቱ ነው፡፡
አቡነ ጎርጎርዮስ ዘላዕላይ ግብፅ፡- ደገኛ የሆኑ ወላጆቻቸው እጅግ ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ልጃቸውንም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምረው በሃይማኖትና በምግባር ኮትጉተው አሳደጓቸው፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስም ሲያድጉ ወደ ኤጲስ ቆጶሳቱ
ዘንድ ወስደዋቸው አናጉስጢስነት ተሾሙ፡፡ ከዚህም በኋላ ወላጆቻቸው በሥርዓት ሚስት ሊያጋቧቸው ሲሉ ጻድቁ ግን ይህንን አልወደዱምና ፈጽሞ እምቢ አሉ፡፡ሁለተኛም ወደ ጳጳሱ ዘንድ ወስደዋቸው ዲቁና ተሾሙ፡፡አቡነ ጎርጎርዮስ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ አዘውትረው እየሄዱ ይማሩ ነበር፡፡
እጅግ ባለጸጎች ከሆኑት ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ከፍለው በመውሰድ ለአባ ጳኩሚስ በመስጠት ለመነኮሳቱ መጠለያ ቤትና ሌላም በጎ ሥራዎችን ሠሩ፡፡ከዚህ በኋላ አቡነ ጎርጎርዮስ ዓለምን ፍጹም ንቀው ተጠቃለው ወደ ገዳሙ
በመግባት በአባ ጳኩሚስ እጅ መንኩሰው በታላቅ ተጋድሎ ለ13 ዓመታት ኖሩ፡፡የቅድስና ሕይወታቸውን አርአያነታቸውንና ምሳሌነታቸውን ያዩ ብዙ አምነዝራዎች የክፋት ሥራቸውን እየተው ንስሓ እየገቡ ንጹሐን እስኪሆኑ ድረስ የሚጋደሉ ሆኑ፡፡አቡነ ጎርጎርዮስ በአባ ጳኩሚስ ዘንድ ለ13 ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ ታላቁ አባ መቃርስ ወደ አባ ጳኩሚስ መጥተው አብረው አገለገሉ፡፡ አባ መቀርስም ወደ ገዳማቸው አስቄጥስ ለመመለስ በፈለጉ ጊዜ አባ ጳኩሚስ አቡነ ጎርጎርዮስን አብረው እንዲሄዱ አዘዟቸውና ጻድቁ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄዱ፡፡ከአባ መቃርስ ዘንድም ብዙ ዘመን በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ከዚህም በኋላ አቡነ ጎርጎርዮስ ብቻቸውን በዋሻ ውስጥ እየተጋደሉ ይኖሩ ዘንድ አባታቸውን እንዲያሰናብቷቸው ጠየቋቸው፡፡ አባ መቃርስ ፈቅደውላቸው መርቀው ሸኟቸውና አቡነ ጎርጎርዮስ ተጋድሎአቸውን በዋሻ ውስጥ ለመፈጸም ወጡ፡፡በተራራ ላይ ቆፍረው ባዘገጇት አንዲት ዋሻ ውስጥም ለ7 ዓመት ሲጋደሉ ኖሩ፡፡አባ መቃርስም በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ብቻ በልደትና በትንሣኤ ቀን እየመጡ ይጎበኟቸው ነበር፡፡ ሥጋ ወደሙንን አብረው ተቀብለው አባ መቃርስ ወደ ገዳማቸው ይመለሳሉ፡፡አባታችን ከ22 ዓመት ተጋድሎአቸው በኋላ ጌታችን መልአኩን ልኮ ከ3 ቀን በኋላ ጊዜ ዕረፍታቸው እንደሆነ ነገራቸው፡፡ መልአኩም መጥቶ ‹‹ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ወጥተህ ወደ ዘላለም ሕይወት ትገባ ዘንድ አለህ›› አላቸው፡፡ አባታችንም በአስቄጥስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳትን ጠርተዋቸው ከተሰናበቷቸውና ከተመራረቁ በኋላ መስከረም 24 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ የአባታችን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +
ሐዋርያው የቅዱስ አድሊጦስ፡- ይህም ሐዋርያ ከአቴና ታላላቅ ምሁራን ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ጌታችንንም አምኖ ተከተለው፣ አገለገለውም፡፡ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ
ቅዱስን ጸጋ በሃምሳኛው ቀን ከተቀበለ በኋላ ወደ ብዙ አገሮች ተዘዋውሮ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ መግኒን ወደምትባል አንዲት ሀገር ደርሶ በውስጧ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡አገልጋይ ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመላቸውና ወደ አቴና በመመለስ በዚያም ብዙዎችን አስተምሮ ሲያሳምን ክፉዎች ይዘው በድንጋይ ወገሩት፡፡ ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ሥቃዮችም አሠቃዩት፡፡ብዙ ካሠቃዩትም በኋላ በመጨረሻ የሚነድ እቶን እሳት ውስጥ ጨምረውት ሰማዕትነቱ በዚሁ ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ የሰማዕቱ
ሐዋርያ የቅዱስ አድሊጦስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
@wdasemaryam
@wdasemaryam
1.8K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ