2022-05-29 05:57:06
ግንቦት 21 . እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን በድብረ
ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት
ቀን የታየችበት ነው።
ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ
ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን
እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር።
እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ
ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው
ይከትማሉ ፤ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት
ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤ህዝቡ የተለያየ
ጥያቄ ይጠይቆታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ
ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል
አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው
ይጠይቃታል፤እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው
ነበር፤አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው
ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር
ነው።የእመቤታችን ረድአት እና በርከቱ በሁላችን ላይ ይድርብን
አሜን፡፡ =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት:
የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት
በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::
+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:
+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ
ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ:
ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ
አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን
ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር::
+ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ
መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን
አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::
+በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት
ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ::
+እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት
ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን
ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::
+የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር
የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው
ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም
ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል:
መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም
ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው
ነበር::
+እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር
ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ ከእመቤታችንን በዕንባ
ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው
ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::
+"+ አባ መርትያኖስ +"+
=>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ
አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል
ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር::
+አንድ ቀን አንዲትን ልጅ ከመሸ በእንግድነት ተቀብለዉ ሽቶ
አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ
ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን የቤቱን
ጠረን ቀይረዉ አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው
ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት
108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው::
=>ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት
ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን
ይደርብን::
=>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ)
2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን
በእሳት ያቃጠሉ አባት)
3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ
=>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>
የሚቀበለው የልመናዋ ክብር ፍጹም የሆነ የረድኤትዋም ሀብት
ጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚመላ የተወደደ የልጅዋ ቸርነት ከሁላችን ጋር
በእዉነት ይሁን ከቅዱሳን እረዴት በረከት ያሳትፈን ለዘለዓለሙ
አጽሜን
https://www.facebook.com/100002926496363/posts/pfbid02dq6tSisM6Jp2S51DAMz3EbokBCiYGHCwFjb1r9WzQCycb8ezfKooaqvvFmdy6hWGl/?app=fbl
4.5K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 02:57