Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-08-20 22:02:23 ሥርዓተ ቅዳሴ


1.6K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 18:49:43

1.7K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 00:24:41
1.9K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 00:23:31 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ደብረ_ታቦር (ነሐሴ 13)
ደብር ማለት ተራራ ሲሆን ታቦር ደግሞ የተራራው ስም ነው፡፡ ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን ገልጦበታል፡፡ ይህም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 13 ቀን ዘጠኙን ሐዋርያት ከእግረ ደብር/ከተራራው ግርጌ/ ትቶ ሦስቱን ሐዋርያት (ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን) አስከትሎ ወደ ተራራው ወጣ። በዚያም ለሦስቱ አርዓያው ተለውጦ፣ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ፣ ልብሱ እንደ በረዶ ነጽቶ፣ ሙሴና ኤልያስ በቀኝና በግራው ቁመው ታዩአቸው፡፡ ስምዖን ጴጥሮስ ‹‹እመሰ ትፈቅድ ንንበር ዝየ ወንግበር ሠልስተ ማኅደረ አሐደ ለከ፣ አሐደ ለሙሴ፣ ወአሐደ ለኤልያስ›› ትርጓሜውም ‹‹በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ፣ አንዱን ለሙሴ፣ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ›› እያለ ሲናገር ወዲያው ብሩህ ደመና መጥቶ ጋረዳቸውና ‹‹ዝንቱ ውእቱ ወልድዬ ዘአፈቅር ወሎቱ ስምዕዎ›› ትርጓሜውም ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት›› የሚል ቃል ሰሙ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም መቆም ተሳናቸው፤ ሙሴ ‹‹ትኄይሰኒ መቃብርየ›› መቃብሬ ትሻለኛለች ብሏል፤ ኤልያስም በሠረገላው ወደየመጡበት ተመልሰዋል፡፡ ሦስቱ ሐዋርያትም ደንግጠው ወድቀው ነበርና ጌታ ዳስሶ በአስነሳቸው ጊዜ ከእርሱ በቀር ሌላ ሰውን አላዩም፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ያዩትን ለማንም እንዳይናገሩ አዝዟቸው ከተራራው ወርደዋል፤ (ማቴ 17፥1-9)።

#ሙሴን_እና_ኤልያስን_የመረጠበት_ምክንያት
ሙሴ በትዳር ያለፈ ነቢይ ሲሆን ኤልያስ ደግሞ በድንግልና ኑሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀ ነቢይ ነው፡፡ ይህ የሚስረዳን ደብረ ታቦር የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትሆን እግዚአብሔር የፈቀደውና በጽድቅ የሚኖሩ ሁሉ (ሕጋውያንም ደናግላንም) መንግሥተ ሰማያትን ለመውረሳቸው ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ስትሆን ይህም በቤተ ክርስቲያን የነቢያት ትንቢት ከሐዋርያት ስብከት ጋር እንደሚነገርባት ያስረዳል።
አንድም ሙሴ ለ40 ዘመን እስራኤላውያንን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ለቃል ይነጋገር ነበር፤ እርሱም ፊትህን አሳየኝ እያለ እግዚአብሔርን ሲለምን ‹‹ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም፤…ጀርባዬንም ታያለህ ፊቴን ግን አታይም›› ብሎ መልሶለታል፤ (ዘጸ 33፥18-23)፡፡ ለኤልያስም ተስፋ ነበረውና ሁለቱን ከነቢያት አደረገ።
አንድም ከጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና፣ ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና ሐዋርያት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እንዲሁም በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊያስነሣቸው ማንም አይችልምና ይህን ሊገልጥላቸው አመጣቸው።

#ሦስቱን_ከሐዋርያት_ያደረገበት_ምክንያት
ዘጠኙን ሐዋርያት ትቶ ሦስቱን አስከትሎ መውጣቱ ምሥጢር ማየት የማይገባው ይሁዳ ነበርና ከምሥጢሩ ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል ከቀሩት ሐዋርያት ጋር ከተራራው ግርጌ ትቶት ወጥቷል። አንድም ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ሲገልጥላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹አይሁንብህ፤ ጌታ ሆይ ይህ ከቶ አይደርስብህም›› (ማቴ 16፥21-24) ብሎት ነበርና እሱን ስሙት የሚለውን የአብን ምስክርነት እንዲሰማ አስከትሎት ወጥቷል።
አንድም ጌታ ሙት ቢያነሣ፣ ዕውር ቢያበራ ሙሴ ነው ኤልያስ ነው ብለውት ነበርና የሙሴ የኤልያስ ጌታ መሆኑን እንዲመሰክሩ አምጥቷቸዋል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ በፊልጶስ ቂሣርያ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?›› ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ‹‹አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኤልያስ፣ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ›› አሉት፡፡ እርሱም(ኢየሱስ ክርስቶስ) ‹‹እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንኩ ትላለላችሁ?›› ብሎ ቢጠይቃቸው ስምዖን ጴጥሮስ ‹‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ›› ብሎ መለሰ፤ (ማቴ 16፥13-17)። በዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ኤልያስ ወይም ሙሴ አለመሆኑን የሙሴና የኤልያስ ጌታ መሆኑን ይገልጥላቸው ዘንድ ሦስቱን ሐዋርያት ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ ወጥቷል።
ዮሐንስና ያዕቆብም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ መቀመጥን ሽተው ሲለምኑት ‹‹የምትለምኑትን አታውቁም›› በማለት መክሯቸው ነበር፤ (ማቴ 20፥20-28፣ ማር 10፥35-45)። ክብረ መንግሥቱን ይገልጥላቸው ዘንድ እነዚህን ሁለቱን ሐዋርያት አስከትሎ ወጣ።
ከተራሮች ሁሉ ታቦርን የመረጠበት ምክንያት ነቢዩ ዳዊት ‹‹ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ›› ትርጓሜውም ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ገለጠ፤ (መዝ 89፥12)።
ደብረ ታቦር ከጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን ምእመናን በተለያዩ ሥርዓቶች ያከብሩታል። ወጣቶች ጅራፍ ያጮሃሉ፤ ችቦ ያበራሉ፣ እናቶች ደግሞ ዳቦ/ኅብስት ይጋግራሉ፡፡ ምሳሌነታቸውም እንዲህ ነው፡-
ጅራፍ፦ አብ ለልጁ ሲመሰክር ያሰማው ድምፅ ምሳሌ ነው።
ችቦ፦ እግዚአብሔር ብርሃኑን ሲገልጥ የፊቱ ብርሃን ምሳሌ ነው፡፡
ዳቦ/ኅብስት፦ ለእኛ ሲል ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰጠን የጌታችን ምሳሌ ነው። አንድም እግዚአብሔር ብርሃነ መለኮቱን ሲገልፅ በአካባቢው የነበሩ እረኞች ቀን መስሏቸው ብርሃኑን እያዩ ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ቤተሰቦቻቸው ኅብስት ጋግረው ወደ ልጆቻቸው መሄዳቸውን ያሳየናል።
እግዚአብሔር ሁላችንንም መልካም ሥራ ሠርተን መንግሥቱን እንድንወርስ ይርዳን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘነሐሴ 13 ፣ መድበለ ታሪክ
1.9K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 16:28:40

1.5K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 16:01:49

1.7K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 23:03:41 ✥የሲኦል ጥፋቱን ስቃዪን እያየች ለፍጥረታት ሁሉ ድንግል ሆይ ታዝናለች በዓየነ ብረቱ እንዲያየን ክርስቶስ ለምኝልን ማርያም ፍጥረት እንዲቀደስ።✥
✥ቅድስት ሆይ ለምኝልን✥
https://youtube.com/shorts/X77Kwkm_-6g?feature=share
1.7K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 16:05:06

1.7K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:34:55

1.8K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:08:39

1.8K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ