Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-04 09:07:06 #ንፅህት_ቅድስት

ንፅህት ቅድስ ቡርክት
የአምላክ እናት እመቤት
ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱ አንድ ሆኑ
ተዋሀዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ/2/
#አዝ
ፍፁም መንፈሳዊ ልዩ ፍቅር
አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር
መሰረቱ ዛሬ ልጆችሽ
ቅድስት ሆይ ባርኪያቸው ተገኝተሽ
#አዝ
ድንግል ጎጇቸውን ቀድሰሽ
እውነተኛ ፍቅር መስርተሽ
በመሀከላቸው ተገኝተሽ
ሁሉን አሰጫቸው አማልደሽ
#አዝ
ሙሽሮቹም አምነው ይጠሩሻል
እናታችን ባርኪን ነይ ይሉሻል
ፈጥነሽ ድረሺና በሰርጋቸው
ነይ ተመላለሺ መሀላቸው
#አዝ
አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ
የህይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ
ሙሽሮቹም ዛሬም ይጠሩሻል
የጎጇችን ፋና ነይ ይሉሻል
#አዝ
ቃና ዘገሊላ ተገኝተሽ
መልካሙን ጋብቻ የባረክሽ
ዛሬም ከልጅሽ ጋር በሰርጋቸው
ነይ ተመላለሺ መሀላቸው

#በወርሀ_ሚያዝያ_ሰርጋችሁን የምትፈፅሙ መልካም ጋብቻ እንዲሆንላቹ እንመኝላቹሀል።

@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam
2.8K views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 05:54:54
ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ፤ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ፤ ማርያም እምነ ናስተበቊዐኪ ፤ እምአርዌ ነዓዊ ተማሕፀነ ብኪ ፤ በእንተ ሐና እምኪ ፤ ወኢያቄም አቡኪ ፤ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ ።

ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ : -
ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ፤ ወትትሐሠይ መንፈስየ ፤ በአምላኪየ ወመድኃኒየ ፤ እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ፤ ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ ፤ እስመ ገብረ ሊተ : ኃይለ ዐቢያተ ፤ ወቅዱስ ስሙ ፤ ወሣህሉኒ : ለትውልደ ትውልድ ፤ ለእለ ይፈርህዎ ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ ፤ ወዘረዎሙ ለእለ የዐብዩ ኅሊና ልቦሙ ፤ ወነሠቶሙ ለኃያላን እመናብርቲሆሙ ፤ አዕበዮሙ ለትሑታን ፤ ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን ፤ ወፈነዎሙ ዕራቆሙ ለብዑላን ፤ ወተወክፎ ለእስራኤል ቊልዔሁ ፤ ወተዘከረ ሣህሎ ፤ ዘይቤሎሙ ፤ ለአበዊነ : ለአብርሃም ፤ ወለዘርዑ እስከ ለዓለም ፤ አሜን ።

ቴሌግራም ተቀላቀሉ
[ https://t.me/wdasemaryam ]

@wdasemaryam
756 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 06:48:29
✥የ36ቱ ቅዱሳት አንስት ስም ዝርዝርና የሚውሉበት ቀን !✥

1. ኤልሳቤጥ የካቲት 16 ቀን
2. ሐና መስከረም 7 ቀን
3. ቤርዜዳን ወይም ቤርስት ታህሳስ 10 ቀን
4. መልቲዳን ወይም ማርና ጥር 4 ቀን
5. ሰሎሜ ግንቦት 25 ቀን
6. ማርያም መቅደላዊት ነሐሴ6 ቀን
7. ማርያም እንተ እፍረት የካቲት 6 ቀን
8. ሐና ነቢይት የካቲት 20 እና ጥቅምት 6 ቀን
9. ማርያም እሞሙ ለደቂቅ ዘብድዎስ ጥር 18 ቀን
10. ሶፍያ (በርበራ) ጥር 30 ቀን
11. ዮልያና (ዮና) ኅዳር 18 ቀን
12. ሶፍያ (መርኬዛ) ጥር 30 ቀን
13. አውጋንያን (ጲላግያ) ጥቅምት 11 ቀን
14. አርሴማ ግንቦት 11 ቀን
15. ዮስቲና ጥር 30 ቀን
16. ጤግላ ነሐሴ 6 ቀን
17. አርኒ (ሶፍያ) ኅዳር 10 ቀን
18. እሌኒ ጥር 29 ቀን
19. ኢዮጰራቅሊያ መጋቢት 26 እና ነሐሴ 2 ቀን
20. ቴዎክላ (ቴኦድራ) ጥር 4 ቀን
21. ክርስቲያና (አጥሩኒስ) ኅዳር 18
22. ጥቅሞላ (አሞና) ጥር 30 ቀን
23. ጲስ ጥር 30 ቀን
24. አላጲስ ጥር 30 ቀን
25. አጋጲስ ጥር 30 ቀን
26. እርሶንያ (አርኒ) ጥር 30 ቀን
27. ጲላግያ ጥር 30 እና ጥቅምት 11 ቀን
28. አንጦልያ (ሉክያ) የካቲት 25 ቀን
29. አሞን (ሶፍያ) ጥር 15 አና ነሐሴ 3 ቀን
30. ኢየሉጣ ነሐሴ 6 ቀን
31. መሪና ሐምሌ 27 ቀን
32. ማርታ እህተ አልአዛር ጥር 18 እና ግንቦት 27 ቀን
33. ማርያም የማርቆስ እናት ጥር 30 ቀን
34. ሣራ (ሶፍያ) የይሁዳ እናት ጥር 30 ቀን
35. ዮሐና (ዮላና) የኩዛ ሚስት ታህሳስ 26 ቀን
36. ሶስና ግንቦት 12 ቀን ናቸው፡፡
ከጌታችን ሳይለዩ አገልግለው በኋላም መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ጊዜ አብረው
ስለነበሩ ግማሾቹ ከሐዋርያት ጋር ተከፋፍለው ተሰማርተዋል፡፡

በረከታቸው ይድረሰን አሜን
1.1K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 07:54:21
«ከቅዱስ ገብርኤል ክብር የተነሳ ምድር በራች /ራእ ፲፰ ÷፩ /18፥1»

ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎትና በምሥጋና ታከበራለች፤ በተለይ ታኅሣሥ ፲፱ { 19 } ቀን የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን (ሠለሥቱ ደቁቅን )ከዕቶነ እሳት ( ከነደደ እሳት ) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው
ሊቀ መላአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዛሬም ለኛም ይድረስ
በምናውቀውና በማናውቀው መንገድ በሀገራችን በሕዝባችን ላይ ከምነድ እሳት በምልጃው በተራዳይነቱ ያድነን አሜን
በረከት ረድኤት አይለየን አሜን

ቴሌግራም ተቀላቀሉ
[ https://t.me/wdasemaryam ]

@wdasemaryam
518 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 13:50:24
እንኳን ለዳግሚያ ትንሣኤ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሣኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ ሦስት ጊዜ ተገልጦላቸዋል።
፩.በዕለተ ትንሣኤ ምሽት በፍርሃት ሳሉ
፪.ያላመነ ቶማስን ለማሳመን በተነሣ በስምንተኛው ቀን (ማለትም ዛሬ)
፫.ከተነሣ ከሃያ ሦስት ቀናት በኋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው።

ጌታ አርባውን ቀን ለአንዱም ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር። እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር።

ጌታችን ከተነሣ በኋላ ለሳምንት ተለይቷቸው ስለ ነበር በቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም እንጂ መልክአ ኢየሱስ በማኅበር አይደገምም።

በዚህች ዕለት ደቀ መዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ጌታችን "ሰላም ለእናንተ ይሁን።" ብሏቸዋል። ቶማስንም "ና ዳስሰኝ።" ብሎታል። ሐዋርያው እጁን ከተወጋ ጐኑ ላይ ቢያሳርፍ በመቃጠሉ "ጌታዬ አምላኬም" ሲል ጮሆ ምሥጢረ ተዋሕዶውን መስክሯል።

ጌታም ቶማስን "እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ - ስላየኸኝ አመንከኝ!
ብጹዐንሰ እለ እንዘ ኢይሬእዩኒ የአምኑኒ - ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹዐን (ንዑዳን ክቡራን) ናቸው።" ብሎታል።
(ዮሐ. ፳፥፳፬)

ጌታችን ከትንሣኤው እና ከቅዱሱ ሐዋርያ በረከትን ያድለን።

"ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ። በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን።' አላቸው። ከዚያም በኋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ። እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው። ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን።' አለው። ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል። ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው።' አለው።"
(ዮሐ ፳፥፳፮-፳፱)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
371 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:31:08 እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳቹ
መልካም በዓል

"የድህነታችን ተግሳፅ በእርሱላይ ነበረ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን"ት.ኢሳ፶፫፥፭

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ?ሉቃ፳፬፥፭

ክርስቶስ ተንሰአ ሙታን
በአብይ ሀይለ ወስልጣን
አስሮ ለሴጣን
አጋዝዎ ለአዳም
ሠላም
እመየዘሰ
ኮነ
ፈሠሐ ወሰላም
@ደሳለኝ
495 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 00:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 05:34:10
742 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 02:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 05:34:09 |የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም የ ኦሪት መስዋዕት የሆነዉ
የእንስሳት ደም ማብቃቱን ገልጦ ለድህነተ
ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ
ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ
|የነፃነት ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ
መሆኑ ማብቃቱና የሰዉ ልጅ ያጣዉን ክብር
መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን
ስ�#ዓርብ ፡-
~
ጌታችን ከ ጲላጦስ አደባባይ እስከ ሊጦስጥራ
የተንገላታበት ለአዳምና ለልጆቹ በምልዕልተ
መስቀል ለሞት እራሱን አሳልፎ የሰጠበት ቀን
ነዉ፡፡
...............
† #ቅዳሜ ፡-
~
|በዚች ዕለት የጌታችን መከራ
በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትዉል ቅዳም
ሥዑር ወይም የተሻረችዉ ቅዳሜ
ትባላለች፡፡
|ካህናቱም ለምዕመናን ለምለም ቄጤማን
የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜም
ትባላለች፡፡
|እንደዚሁም ልዑል
እግዚአብሔር በዚህ ቀን 22ቱን ስነ ፍጥረታት
ፈጥሮ ከስራዉ ያረፈበት ዕለት በመሆኑ ቅ/
ቅዳሜ ይባላል፡፡
ከህማሙ ከመከራው በረከት ያሳፈን!!
በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::
765 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 02:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 05:34:09 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ሰሞነ ህማማት "
Please share

#ሰሙነ_ሕማማት_ምን_ማለት ነው?
ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
የሚከለከሉ ና የሚፈቀዱ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለምን?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

"በህማማት የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው"
1. በህማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይስ ለምን አናማትብም ?
የመስቀል ክብር እና ሐይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በሗላ ነው፡፡ በሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው፡፡በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ ማማተብ ስርዓት አይደለም፡፡ግን አነድ ሰዉ ተሳሰቶ ቢያማትብ ምንም በደልም ሐጢአትም አይሆንበትም።
2. በሰሞነ ህማማት ለምን አንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛ ግን እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህም በተጨማሪ ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰምነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም፡፡
3. በሰሞነ ህማማት የማይደረጉ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው? ማንኛውንም ለስጋ የሚያደሉ ተግባራትን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜያችንን የጌታን ህማም መከራ በማሰብ በፆም በፀሎት በስግደት ማሳለፍ ፤ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ፤በትዳር ያሉ በፆም ወቅት በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ አለባቸው፡፡
4.ታቦት ከመንበሩ አይነሳም ምንም የንግሰ በዓልም አይከበርም
5.ፍትሐት፣ክረሰትና የለም

6.ሰላምታ ያለባቸው ጸሎቶች ለምሳሌ መልክዓ ቅድሳን አይጸለይም ከሱ ይልቅ መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ግብረ ሕማማት እና መጽሐፈ ማሕያዊ የተባለ ብዙ ቃልኪዳን ያለው የጌታን መከራ የሚያወሳ መጽሐፈ ጸሎት
ይነበባሉ

ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

በሰሙነ ህማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
የተከናወኑትን ተግባራት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
† #ሰኞ
~
ጌታችን ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን
በለስ ከሩቁ አይቶ በለሲቱን ቀረባት ነገር ግን
ከቅጠል በቀር ምንም አልተገኘባትም ከአሁን
ጀምሮ ማንም ከ አንች ፍሬን አይብላ ብሎ
እረገማት በለስ የተባሉ እስራኤላዊያን ናቸዉ፡፡
...............
† #ማክሰኞ
~
ሻጮች እና ለዋጮችን ከቤተ
መቅደስ ባሶጣ ጊዜ ይኼንን በማን ኃይል
እንዳደረገዉ የአይሁድ መምህራን ጠይቀዉት
ነበር ማቴ 21-23
ስለሆነም የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
...............
† #ረቡዕ
~
ምክረ አይሁድ ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ
ሊቃነ ካህናት እና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ
እንዳለባቸዉ ምክር ያጠናቀቁበት ቀን በመሆኑ
...............
† #ሐሙስ
~
በቤተ ክርስቲያን የተለያየ
ስያሜዎች ያሏቸዉ በርካታ ድርጊቶች
የተፈጸሙበት ነዉ፡፡
|ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡
መድኃኒዓለም ክርስቶስ አይሁድ መጥተዉ
እስኪይዙት
ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነዉና ጸሎተ ሐሙስ
ተባለ
|ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር
ጎንበስ
ብሎ በታላቅ ትህትና አጥቧልና
|የሚስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የሆነዉን ምስጢረ
ቁርባን በዚህ ዕለት ተመስርቷልና
658 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 02:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 13:19:47 እንኳን_ለበዓለ_ሆሳዕና_በሰላም_አደረሳችሁ !!!



የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩስአሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይም አእሩግ እና ህጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም “ በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው።
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና ከረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህ በዚሁ በዓለ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርአየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።
አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካሪያስ እንደተነገረው ‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’ 《ዘካ.9፣9》። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናገሮ ነበር።
ሲመጣም ‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።’’ በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። 《2ኛ ነገ. 9፣13》 ።
የሆሣዕና በዓል በቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡርክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ 《መዝ.117፣26》 በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ታድላለች።
በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚመለከቱ
የቅዱስ ማቴዎስ 《ማቴ. 21፣1-17》፤
የቅዱስ ማርቆስ《ማር.11፣1-10》፤
የቅዱስ ሉቃስና 《ሉቃ.19፣29-38》፤
የቅዱስ ዮሐንስ 《ዮሐ.12፣12-15》ወንጌላት ይነበባሉ
እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ ።
1.0K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ