Get Mystery Box with random crypto!

|የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- ምክንያቱም የ ኦሪት መስዋዕት የሆነዉ የእንስሳት ደም ማብቃቱን ገ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

|የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም የ ኦሪት መስዋዕት የሆነዉ
የእንስሳት ደም ማብቃቱን ገልጦ ለድህነተ
ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ
ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ
|የነፃነት ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ
መሆኑ ማብቃቱና የሰዉ ልጅ ያጣዉን ክብር
መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን
ስ�#ዓርብ ፡-
~
ጌታችን ከ ጲላጦስ አደባባይ እስከ ሊጦስጥራ
የተንገላታበት ለአዳምና ለልጆቹ በምልዕልተ
መስቀል ለሞት እራሱን አሳልፎ የሰጠበት ቀን
ነዉ፡፡
...............
† #ቅዳሜ ፡-
~
|በዚች ዕለት የጌታችን መከራ
በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትዉል ቅዳም
ሥዑር ወይም የተሻረችዉ ቅዳሜ
ትባላለች፡፡
|ካህናቱም ለምዕመናን ለምለም ቄጤማን
የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜም
ትባላለች፡፡
|እንደዚሁም ልዑል
እግዚአብሔር በዚህ ቀን 22ቱን ስነ ፍጥረታት
ፈጥሮ ከስራዉ ያረፈበት ዕለት በመሆኑ ቅ/
ቅዳሜ ይባላል፡፡
ከህማሙ ከመከራው በረከት ያሳፈን!!
በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::