Get Mystery Box with random crypto!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 'ሰሞነ ህማማት ' Please share | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ሰሞነ ህማማት "
Please share

#ሰሙነ_ሕማማት_ምን_ማለት ነው?
ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
የሚከለከሉ ና የሚፈቀዱ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለምን?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

"በህማማት የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው"
1. በህማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይስ ለምን አናማትብም ?
የመስቀል ክብር እና ሐይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በሗላ ነው፡፡ በሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው፡፡በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ ማማተብ ስርዓት አይደለም፡፡ግን አነድ ሰዉ ተሳሰቶ ቢያማትብ ምንም በደልም ሐጢአትም አይሆንበትም።
2. በሰሞነ ህማማት ለምን አንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛ ግን እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህም በተጨማሪ ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰምነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም፡፡
3. በሰሞነ ህማማት የማይደረጉ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው? ማንኛውንም ለስጋ የሚያደሉ ተግባራትን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜያችንን የጌታን ህማም መከራ በማሰብ በፆም በፀሎት በስግደት ማሳለፍ ፤ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ፤በትዳር ያሉ በፆም ወቅት በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ አለባቸው፡፡
4.ታቦት ከመንበሩ አይነሳም ምንም የንግሰ በዓልም አይከበርም
5.ፍትሐት፣ክረሰትና የለም

6.ሰላምታ ያለባቸው ጸሎቶች ለምሳሌ መልክዓ ቅድሳን አይጸለይም ከሱ ይልቅ መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ግብረ ሕማማት እና መጽሐፈ ማሕያዊ የተባለ ብዙ ቃልኪዳን ያለው የጌታን መከራ የሚያወሳ መጽሐፈ ጸሎት
ይነበባሉ

ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

በሰሙነ ህማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
የተከናወኑትን ተግባራት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
† #ሰኞ
~
ጌታችን ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን
በለስ ከሩቁ አይቶ በለሲቱን ቀረባት ነገር ግን
ከቅጠል በቀር ምንም አልተገኘባትም ከአሁን
ጀምሮ ማንም ከ አንች ፍሬን አይብላ ብሎ
እረገማት በለስ የተባሉ እስራኤላዊያን ናቸዉ፡፡
...............
† #ማክሰኞ
~
ሻጮች እና ለዋጮችን ከቤተ
መቅደስ ባሶጣ ጊዜ ይኼንን በማን ኃይል
እንዳደረገዉ የአይሁድ መምህራን ጠይቀዉት
ነበር ማቴ 21-23
ስለሆነም የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
...............
† #ረቡዕ
~
ምክረ አይሁድ ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ
ሊቃነ ካህናት እና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ
እንዳለባቸዉ ምክር ያጠናቀቁበት ቀን በመሆኑ
...............
† #ሐሙስ
~
በቤተ ክርስቲያን የተለያየ
ስያሜዎች ያሏቸዉ በርካታ ድርጊቶች
የተፈጸሙበት ነዉ፡፡
|ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡
መድኃኒዓለም ክርስቶስ አይሁድ መጥተዉ
እስኪይዙት
ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነዉና ጸሎተ ሐሙስ
ተባለ
|ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር
ጎንበስ
ብሎ በታላቅ ትህትና አጥቧልና
|የሚስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የሆነዉን ምስጢረ
ቁርባን በዚህ ዕለት ተመስርቷልና