Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-28 21:09:42 "ድንግል ሆይ! ነደ እሳት የማያቃጥላት በነበልባል ያጌጥሽ ዕፅ ነሽ። በጭንጫ ላይ በታነፀ ፎቅ ለመኖር እችል ዘንድ በዕውቀት ከፍ ከፍ አድርጊኝ፤ እንዳልወድቅም ደግፊኝ።"
(መልክአ ማርያም)

የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን አደረሳችሁ !!!

«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ሞት ለሟች

ይገባል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

በዓለ አስተርዮ

ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት

ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፋንታ በመሆኑ በሰልሳ አራት

አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው ።
ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም "ሞትሰ

ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ "ትርጉሙ ሞት

ለማንኛውም ሰው የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን

ያስደንቃል ።በማለት አደነቀ። በመሆኑም በ ዓሉ የወላዲት አምላክ

በዓለ ዕረፍት ከመሆኑም የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ

በየዓመቱ ይከበራል ።

የእረፍቷ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስልሳ አራት አመት

በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21ቀን እሁድ እለት ጌታ እልፍ አዕላፍት

መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም

ላሳርፍሽ መጣው አላት ። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ

ወር ከአምስት ቀን በማህፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጅህ

አለችው ። በሲዖል የሚሰቃዩትን ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ

ለእነዚህ ቤዛ ይሆናቸዋል አላት።እኚህን ከማርክልኝ ይሁን አለች ።

ቅድስት ስጋዋን ከቅድስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርነት

በዝማሬ መላእክት አሳረጋት ።ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት

በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው

ባጎበር አድርገው ይዘዋት ወደ ጌቴሰማኔ ሲወስዷት አይሁድ

አይተው ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደሞ

እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አደለምን ንፁ ናውዒ ሥጋሃ

ለማርያም ኑ እናቃጥላት ብለው ተነሱ ።ከመካከላቸው አንዱ

ታውፋኒያ ዘል ያልጋውን ሽንኮር ያዘ።የታዘዘ መላእክ መጥቶ ሁለት

እጁን በሰይፍ ቀጣው ።በድያለው ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን

ዘንበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበር አድርግለት

አለችዉ።ቢመልሰው ድኖለታል ።ከዚም በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ

ከመካከላቸው ነጥቆ ገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯታል ።

የፃድቅ መመኪያ የኃጢያንተስፋ የሆነች እመቤታችን

በረድኤት በአማላጅነቷ ሁላችንንም ትጠብቀን ።

አሜን አሜን አሜን ።
ጥር 21 የአስተርእዮ ማርያም ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌቱ ከሊቃውንቱ ጋር ለማመስገን እንዲረዳን እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል
#ሼር_Share_ያድርጉ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ዋህድ፤ ዕፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ፤ ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ፤ ዮሐንስ በልብሱ ከደነ ገፃ።

ወረብ
እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ በከየት እመ አምላክ/፪/
ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ በከየት/፪/

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ መጽአ ውስተ ዓለም፤ ወዓለሙኒ ኢክህለ ፀዊሮቶ፤ ፆረቶ ወአግመረቶ ማርያም።

ነግሥ
ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ፤ ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ፤ ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፤ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኲሉ።

ዚቅ
እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ፤ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኲሉ፤ አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ፤ ወአግአዛ እምእኩይ ውስተ ሠናይ፤ እሞት ውስተ ሕይወት፤ ወረሰየ ይዝክሩ ስማ ውስተ ኲሉ ዓለም።

ወረብ
ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ/፪/
ወአግአዛ እምእኩይ ውስት ሠናይ እሞት ውስተ ሕይወት/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለእስትንፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት፤ ከመ መዓዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤ ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፤ ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤ በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት።

ዚቅ
አንጺሆ ሥጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ፤ ኃደረ ቃል ላዕሌሃ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ወይቤላ ለድንግል፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሰሎሞን ይቤላ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት፤ ፍናወ ዚአኪ ገነት፤ እስመ ኪያኪ ኀረየ ለታዕካሁ፤ ከመ ትኩኒዮ ማኅደረ ለልዑል።

ወረብ
'አንጺሆ ሥጋሃ'/፪/ ላዕሌሃ ኃደረ/፪/
ቀዲሶ ኪያሃ 'ሃሌ ሉያ'/፪/ ይቤላ ለድንግል/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለገቦኪ ዘሐመልማለ ወርቅ ክዳኑ፤ በከመ ዳዊት ይዜኑ፤ ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ስኑ፤ በልኒ እግዝእትየ አፈቅረከ አኮኑ፤ እንዘ ረዳኢትከ አነ ዘይክለከ መኑ።

ዚቅ
እምሰማያት ወረደ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፤ ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለ፳ኤል፤ ወረደ ስኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ፤ ወስኑሰ ለያዕቆብ ዘይቤ ይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ፤ መድኅን እማርያም።

ወረብ
ወስኑሰ ለያዕቆብ 'ዘይቤ'/፪/ ያዕቆብ/፪/
'ይእቲ ሥጋ'/፪/ እማርያም እንተ ነሥአ መድኅን/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ
ፃዕር ወፃማ፤ ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ሞገስ ወግርማ፤ አጽንዒ በረድኤትኪ ለሕይወትየ ድካማ፤ እምሕይወተ ኄራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ።

ዚቅ
ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና፤ ጠሊላነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና።

ወረብ
ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም 'ጊዜ'/፫/ ዕረፍታ ለማርያም/፪/
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ፤ ዘተመሰለ ባሕርየ፤ ማርያም ድንግል ዐጸደ ወይንየ፤ ንስቲተ ለዕበየኪ እንተ አቅረብኩ ግናየ፤ ኢይትኃደግ ዲበ ምድር ምሥጢ ሰማየ።

ዚቅ
ኦ ትቤ ማርያም እወጽእ እምዝንቱ ሥጋየ፤ ወአሐውር ውስተ ሕይወት ዘለዓለም፤ ኦ ተዘከርኬ ዮሐንስ ዘይቤለከ ሊቅ አመ ትረፍቅ ዲበ ዕንግድዓሁ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ፤ በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕፁብ፤ ማርያም ድንግል ወለተ ኅሩያን ሕዝብ፤ ረሰይኩኪ እግዝእትየ ህየንተ እም ወአብ፤ ይሕፅነኒ ከመ ጥብ ፍቅርኪ ሐሊብ።
1.1K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 21:09:38
970 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 17:12:06

1.9K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 09:22:36

124 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 08:56:35 ❀✞ ገሃድ ዘውእቱ ተውላጠ ረቡዕ ወዐርብ ወአባ ታውንጦስ ወኪናርያ ወበጠሪቃዕ ንግስት ወጦምዳሪ ሰማዕት።✞❀
የጥር ፲ #ግጻዌ


ዘነግህ ምስባክ

‹‹ለበስከ ሰቀ ወኮንክዎሙ ነገረ።ላዕሌየ ይዛውዑ እለ ይነብሩ ውስተ አናቅጽ። ወኪያየ የኀልዩ እለ ይስትዩ ወይነ።››

‹‹ማቅ ለበስሁ ምሳሌም ሆንሁላቸው።
በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፤ ወይን የሚጠጡ እኔን ይዘፍናሉ።››
መዝሙር ፷፰፡፲፩

ወንጌል ዘነግህ

የማርቆስ ወንጌል ፩፡፩-፱
፩ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።
፪-፫ እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥

፬ ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

፭ የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፥ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

፮ ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ አንበጣና የበረሀ ማርም ይበላ ነበር።

፯ ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።

፰ እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር።

፱ በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።

የእለቱ ቅዳሴ ምንባባት

ወደ ገላትያ ሰዎች ፫፡፳-ፍጻሜው
፳ መካከለኛውም ለአንድ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

፳፩ እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም ነውን? አይደለም። ሕያው ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእውነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር፤

፳፪ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመን የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ ይሰጥ ዘንድ መጽሐፍ ከኃጢአት በታች ሁሉን ዘግቶታል።

፳፫ እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር።

፳፬ እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤

፳፭ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም።

፳፮ በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤

፳፯ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።

፳፰ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።

፳፱ እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።

፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ፬፡፲፬-፲፰
፲፬ እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።

፲፭ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

፲፮ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።

፲፯ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።

፲፰ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

ግብረ ሐዋርያት ፲፫፡፳፬-፴
፳፬ ከመምጣቱ በፊት ዮሐንስ አስቀድሞ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ሰብኮ ነበር።

፳፭ ዮሐንስም ሩጫውን ሲፈጽም ሳለ፦ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔስ እርሱን አይደለሁም፤ ነገር ግን እነሆ፥ የእግሩን ጫማ እፈታ ዘንድ ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ ይመጣል ይል ነበር።

፳፮ እናንተ ወንድሞቻችን፥ የአብርሃም ዘር ልጆች ከእናንተ መካከልም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥ ለእናንተ የዚህ የመዳን ቃል ተላከ።

፳፯ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤

፳፰ ለሞትም የሚያደርስ ምክንያት አንድ ስንኳ ባያገኙበት፥ ይገድለው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት፤

፳፱ ስለ እርሱም የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜ ከእንጨት አውርደው በመቃብር አኖሩት።

፴ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዓማ። ርትዕስ እምድር ሠረፀት።››

‹‹ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።እውነት ከምድር በቀለች፥››
መዝሙር ፹፬፡፲

ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ፫፡፩-፲፫
፩-፪ በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

፫ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።

፬ ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።

፭ ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤

፮ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

፯ ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

፰ እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤

፱ በልባችሁም፦ አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና፦ ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።

፲ አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።

፲፩ እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤

፲፪ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።

፲፫ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።

✥✥✥ቅዳሴ፦ዘእግዚእነ (ነአኩተከ)

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል
youtub @bisratnegarikidusgebrel
https://www.youtube.com/@bisratnegarikidusgebrel

facebook ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

telegram T.me/wdasemaryam
464 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 08:56:28
468 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 17:49:42 ✥ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ✥አሜን!

✥እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

“ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።”

✥ልደት✥
✥ልደት ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ ከማኅፀን መወለድ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣት ማለት ነው። ምሥጢራዊ ትርጉሙም ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት፣መኖር፣መፀነስ፣ መወለድ፣ከእናት ሆድ ወደ ብርሃን መውጣት፣መገኘት፣ተገልጾ መታየት ማለት ነው፡፡

✥እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች።(ኢሳ.7፥14፣ሕዝ.44፥1)

✥የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና(ሚክ.5፥2፣ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡

✥አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት(ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡

@✥ደሳለኝ ዳኜ
522 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 07:12:01

268 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 20:56:07

295 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 07:11:34
ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተመረጡ የተመረጠች፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተከበሩ የተከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናቷ ከቅድስት ሐናና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ከተወለደችበት ዕለት ግንቦት ፩ ቀን ጀምሮ በወላጆቿ ቤት ለሦስት ዓመት ከኖረች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ‹‹በዓታ ለማርያም›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡እንኳን አደረሳችሁ !

ለመቀላቀል
@wdasemaryam
T.me/wdasemaryam
YouTube .
https://www.youtube.com/@bisratnegarikidusgebrel
244 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ