Get Mystery Box with random crypto!

✥ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ✥አሜን! ✥እንኳን ለጌታች | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

✥ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ✥አሜን!

✥እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

“ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።”

✥ልደት✥
✥ልደት ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ ከማኅፀን መወለድ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣት ማለት ነው። ምሥጢራዊ ትርጉሙም ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት፣መኖር፣መፀነስ፣ መወለድ፣ከእናት ሆድ ወደ ብርሃን መውጣት፣መገኘት፣ተገልጾ መታየት ማለት ነው፡፡

✥እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች።(ኢሳ.7፥14፣ሕዝ.44፥1)

✥የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና(ሚክ.5፥2፣ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡

✥አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት(ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡

@✥ደሳለኝ ዳኜ