Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-28 16:48:37 ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
446 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 16:44:57 የዐቢይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት

#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥ አንድ ሲኖዶስ ፥ አንድ መንበር ።

ጾም ማለት ፤
፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።
፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።

፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤
፠ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤
፠ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤
፠ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤
፠ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤
፠ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ)

….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም።

#ዐቢይ_ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው።

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤

፩ኛ. ዘወረደ ይባላል፤

‹‹#ሃሌ_ሃሌ_ሉያ_ዘወረደ_እምላዕሉ_አይሁድ_ሰቀሉ፤
#ወሚመ_ኢያእመሩ፤
#እግዚአ_ኵሉ_ዘየሐዩ_በቃሉ፡፡››
‹‹ #ዘወረደ_እምላዕሉ_እመልዕልተ_ኵሉ››፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/

፪ኛ. ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡

የዐቢይ ጾም የመዠመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው፤ እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

፫ኛ. ሙሴኒ
የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ.4፥1-4/፡፡

ይህ ታላቅ ጾም ሌሎች ስያሜዎችም አሉት ፡፡

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥
አንድ ሲኖዶስ ፥
አንድ መንበር ።
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል
youtub @bisratnegarikidusgebrel
https://www.youtube.com/@bisratnegarikidusgebrel

facebook ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

telegram T.me/wdasemaryam
577 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 17:54:20
            †           

[ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል ! ]


በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡

         †            †            †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
485 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 06:58:19

641 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 10:03:39

649 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 12:57:18

685 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:40:46         †      

ሰበር

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፍ ዐወጀ !

በቤተ ክርስቲያን ላይ የተጀመረው አደጋ እየቀጠለ ስለኾነ በመስቀል ዐደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሥኗል።

የሰልፉ ቀን የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ነው።

የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም !

              †   †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
1.4K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 17:56:31
480 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 14:50:31

646 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 21:09:42 ዚቅ
ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት፤ ብፁዓን ሐዋርያት ቦኡ ኀቤሃ፤ በሰላም አምኁ ኪያሃ፤ በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ለመቃብርኪ ለጌቴሴማኒ በመርኅባ፤ እንተ ይእቲ ለኢየሩሳሌም ቅሩባ፤ ማርያም ድንግል ለሀገረ መንግሥት ርግባ፤ ትትሜጦ ወረቀ እምአፌር ወጸበለ አፈው እምሳባ፤ ጌቴሴማኒ ለሥጋኪ ምስካባ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ዓውዳኒ ዘጽድቅ ወመርኅባኒ ዘዕንቊ፤ አንቀጸ አድኅኖ ሐዳስ ንጽቅ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ለመቃብርኪ ለኢየሩሳሌም በአድያማ፤ እንተ ይእቲ ጌቴሴማኒ ስማ፤ ማርያም ሰንበት ዕረፍተ ጽዑራን እምፃማ፤ አመ ኀደረ ላዕሌኪ ፀሐየ ቅዱሳን ዘራማ፤ ኃይለ ልዑል ጸለለኪ በመንክር ግርማ።

ዚቅ
ኢይሜንንዋ ኪያሃኒ ወአድያሚሃኒ ነያ ጽዮን ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር።

ማኅሌተ ጽጌ
እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፤ አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፤ ንዌድሰኪ እንዘ ንብል ምክሃ ዘመድነ፤ ዮም በፍሥሃ ለማርያም እምነ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ።

ዚቅ
አስተርአየ ዘኢያስተርኢ፤ ኮነ እሙነ አስተርእዮቱ ለመድኃኒነ ክርስቶስ፤ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፤ እምድንግል ተወልደ፤ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፤ በሥጋ ረቂቅ፤ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፤ በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤ በበህቅ ልህቀ።

አንገርጋሪ
ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን፤ ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ፤ አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተአቊረ፤ እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ፤ ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂዎ፤ ዘኪሩቤል ኢርእዮ።

አመላለስ
ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂሆ/፪/
ኢያርኂሆ ዘኪሩቤል ኢርእዮ ኢያርኂዎ ኢርእዮ ዘኪሩቤል/፪/

ወረብ
'አምላክ ኀደረ'/፪/ ውስተ ሥጋ ተዓቊረ እንዘ ኢይትጋባዕ አምላክ ኀደረ/፪/
ዘድንግል መናሥግተ 'ኢያርኂዎ'/፪/ ኢርእዮ ዘኪሩቤል/፪/

እስመ ለዓለም
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ ቃል ቅዱስ፤ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ ዘመንበሩ ዓቢይ ውእቱ፤ ያቀድም አእምሮ ኅሊና ሰብእ፤ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ ግሩም እምግሩማን፤ ዘመጽአ ውስተ ዓለም፤ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ ስብሐት ዘኢየኃልቅ፤ ወሰን ዘኢያንጸበርቅ፤ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ ዘይሥዕሎሙ ለሕፃናት፤ ወይነግሥ ለመላእክት መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ እስመ ንጉሥ ውእቱ ሰከበ በጎል፤ ሰገዱ ሎቱ ሰብአ ሰገል፤ መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ እምግርማሁ ትርዕድ ምድር ዜናዊ ስቡሕ ዘለዓለም፤ ወእስከ ለዓለም ንጉሥ ውእቱ።

ወረብ
ዘመንበሩ ዓቢይ መንበሩ ውእቱ መንበሩ ዘኪሩቤል/፪/
ያቀድም 'አእምሮ'/፪/ ኅሊና ሰብእ/፪/

✥✥✥ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይም youtub ጋብዙ

ለመቀላቀል
youtub @bisratnegarikidusgebrel
https://www.youtube.com/@bisratnegarikidusgebrel

facebook ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

telegram T.me/wdasemaryam
ይጋብዙ
1.2K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ