Get Mystery Box with random crypto!

የዐቢይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት #ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ አንዲት ቤተክርስቲያን ፥ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የዐቢይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት

#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥ አንድ ሲኖዶስ ፥ አንድ መንበር ።

ጾም ማለት ፤
፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።
፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።

፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤
፠ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤
፠ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤
፠ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤
፠ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤
፠ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ)

….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም።

#ዐቢይ_ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው።

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤

፩ኛ. ዘወረደ ይባላል፤

‹‹#ሃሌ_ሃሌ_ሉያ_ዘወረደ_እምላዕሉ_አይሁድ_ሰቀሉ፤
#ወሚመ_ኢያእመሩ፤
#እግዚአ_ኵሉ_ዘየሐዩ_በቃሉ፡፡››
‹‹ #ዘወረደ_እምላዕሉ_እመልዕልተ_ኵሉ››፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/

፪ኛ. ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡

የዐቢይ ጾም የመዠመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው፤ እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

፫ኛ. ሙሴኒ
የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ.4፥1-4/፡፡

ይህ ታላቅ ጾም ሌሎች ስያሜዎችም አሉት ፡፡

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥
አንድ ሲኖዶስ ፥
አንድ መንበር ።
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል
youtub @bisratnegarikidusgebrel
https://www.youtube.com/@bisratnegarikidusgebrel

facebook ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

telegram T.me/wdasemaryam