Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-09 20:46:23
2.0K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 19:07:11 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን (፫)

#ጳጉሜ
የጻጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው።
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጹዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጻመው የፈቃዱ ጾም ነው።

ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው። ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት(5) ወይም(6 )ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት።
በአራት አመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል። በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሥስት ወራት ጸጋ/ Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች ትለያለች። ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ በዘመነ ሉቃስ ማብቂያ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም /ህዳር 15 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል።

በቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ የጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል።
ይህ ግን አንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም/ ጽጌ ጾም / በብዘዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም። የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው። እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው ከቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን።
ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋረስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥቶ ደንበር አሰፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ።

ዮዲ 2:2-7። እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመነ 12 ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ነገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእሰራኤል ልጆች አለቀሱ።

#ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች።
የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበት መንገድ ለመጠበቅ ሱባኤ በገባች በሥስተኛው ቀን ገለፀላት። ዮዲ 8:-2 ። ከዚህ በኅላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል። ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾም በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው።
ስለዚህ ምመዕናን ጥንተ ጠላታችን ሴጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለን ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ።

#የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው።
ይህም #ጻጉሜ የአመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው።

# ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
# ወለወላዲቱ ድንግል
# ወለ መስቀሉ ክብር አሜን (፫)

የዪቲዩብ ቻናል ስለከፈትኩ ለማበረታታት subscribers ያድርጉልኝ ✥ ✥

Bisrat negari kidus gebrel tube ብስራት ነጋሪ ቅዱስ ገብርኤል
https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
403 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 19:06:36
330 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:00:12 እሊህ ሦስቱ አባቶችም የካህናት አለቆችና እኛ ወደ አለንበት ከቅርጺቱ ሥዕል ጋር መጥተው ወቀሷቸው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም ነገሩአቸው።
ከዚህም በኋላ ጌታችን አባቶችን ወደቦታችሁ ሒዱ አላቸው ወዲያው ተመለሱ ቅርጺቱንም ወደቦታሽ ተመለሽ አላት እርሷም ወደ ቀደመው አኗኗርዋ ተመለሰች ይህንንም አይተው የካህናት አለቆች አላመኑም ሌላም ብዙ አለ ብነግርህ መወሰን አትችልም ነገር ግን ለብልህ ጥቂት ቃል ትበቃዋለች ለሰነፍ ግን ቢነግሩት በቁም ነገር ላይ አይታመንም።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ማነጋገሩን ገታ ራሱንም እንደሚያንቀላፋ አደረገ እንድርያስም አንቀላፋ እንድርያስንና ደቀ መዛሙርቱን እንዲሸከሙአቸውና ሊገቡበት ወደሚሹት አገር በውጭ እንዲአኖሩዋቸው መላእክትን አዘዛቸው።
ከዚህም በኋላ እንድርያስ በነቃ ጊዜ ዐይኖቹን ገለጠ የከተማውንም በር ተመለከተ በየብስም ላይ እንዳለ አውቆ ደነገጠ አደነቀም። ደቀ መዛሙርቱንም አነቃቸውና እንዲህ አላቸው ጌታችንን በባሕር ላይ ሳለን ያላወቅነው ምን አደረገብን ሲፈትነን መልኩን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታይቶናልና።
ደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አሉት እኛም በጌትነቱ ዙፋን ላይ ሁኖ የመላእክት ሠራዊት ሁሉ በዙሪያው ሁነው ጌታችንን አየነው አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብንም ቅዱሳንን ሁሉ አየናቸው ንጉሥ ዳዊትም በመሰንቆ ይዘምር ነበር። እናንተንም ዐሥራ ሁለት ሐዋርያት በፊቱ ቁማችሁ ዐሥራ ሁለቱንም የመላእክት አለቆች በፊታችሁ ሌሎች መላእክት በኋላችሁ ሁነው አየናችሁ። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስንም መላእክትን እንዲህ ብሎ ሲያዛቸው ሰማነው የሚሉአችሁን ሁሉ ሐዋርያትን ስሟቸው።
እንድርያስም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው ይህን ድንቅ ምሥጢር ያዩ ዘንድ ደቀ መዛሙርቱ የሚገባቸው ሆነዋልና። ከዚህም በኋላ እንድርያስ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ በታላቅ ድምጽ ጮኸ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከእኛ ከባሮችህ ሩቅ እንዳልሆንክ አወቅሁ። ነገር ግን በመርከብ ላይ እኔ እንደማስተምረው ሰው መስለኸኝ በድፍረት ተናግሬሃለሁና ጌታዬ ይቅር በለኝ ።
በዚያንም ጊዜ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእንድርያስ ዳግመኛ ተገለጠለት እንዲህም አለው። አዎን እኔ ነኝ በሊቀ ሐመር አምሳል በባሕር ውስጥ የተገለጥኩልህና መርከቡን የቀዘፍኩልህ። አትፍራ አትደንግጥ እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁ ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት በክብር ዐረገ እንድርያስም መንገዱን ሄደ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጌቶቻችን ሐዋርያት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፦ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ

የዪቲዩብ ቻናል ስለከፈትኩ ለማበረታታት subscribers ያድርጉልኝ ✥ ✥

Bisrat negari kidus gebrel tube ብስራት ነጋሪ ቅዱስ ገብርኤል
https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
372 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:00:12 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 30-ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሚልክያስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ጌታችን ለሐዋርያው ለቅዱስ እንድርያስ በባሕር ውስጥ በሊቀ ሐመር አምሳል የተገለጠለትና ድንቅ ተአምር ያደረገበት ነው፡፡
+ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የሀገረ ፈርማው ኤጲስቆጶስ አባ ሙሴ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
✞✞✞✞✞
ነሐሴ ሠላሳ በዚች ቀን ከዐሥራ ስድስቱ ነቢያት አንዱ ታላቅ ነቢይ ሚልክያስ አረፈ። ይህም ነቢይ የእስራኤል ልጆች ከተሰደዱበት ከባቢሎን ሀገር በተመለሱ ጊዜ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፋቸው ገሥጿቸዋል።
ሁለተኛም ነቋር ስለሆነ መሥዋዕት ስለ አሥራትና በኵራት ገሥጿቸዋል። በዚህ ነቢይ አንደበት እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሯልና ርኅራኄ አድርጋችሁ ምጽዋትን መጽውቱ፣ ዐሥራቴንና በኵራቴንም አስገቡና እስቲ ፈትኑኝ እኔ ከሰማይ ዝናሙን ባላወርድላችሁ በረከትንም አስቲበቃችሁ ባልጨምርላችሁ የምድራችሁንም ፍሬ ነቀዝና መሰክ እንዳይበሉት እከለክላለሁ።
ዳግመኛም ከክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አስቀድሞ መጥምቁ ዮሐንስ ስለ መምጣቱ ስለ ነቢዩ ኤልያስም ተናገረ። ደግሞ ስለ አይሁድ የሥርዓተ ክህነት ፍጻሜ ተናገረ በአሕዛብም አገር ውስጥ ለእግዚአብሔር የሚቀበላቸውን መሥዋዕት የሚያሳርጉ ዕውነተኞች ንጹሐን ካህናት እንዳሉ ገለጠላቸው።
በበጎ ተጋድሎውም እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ ከዚህ ዓለም በመፍለስ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞
በዚችም ቀን ጌታችን በባሕር ውስጥ ለሐዋርያ እንድርያስ በሊቀ ሐመር አምሳል ተገልጦ ድንቅ ተአምር አደረገለት።
እንድርያስም ጌታችንን በመርከብህ አሳፍረን ነገር ግን የምንከፍልህ የመርከብ ዋጋ የለንም አለው። በሊቀ ሐመር የተመሰለ ጌታችንም ስለምን የላችሁም አለው እንድርያስም በከረጢታችን ወርቅን፣ ብርን እንዳንይዝ ጌታችን ስለአዘዘን ነው አለው። ጌታችንም እንዲህ ከሆነ ወደ መርከቤ ወጥታችሁ ተሳፈሩ አላቸው ያንጊዜም ወደ መርከብ ወጥተው ተሳፈሩ።
ከዚህም በኋላ ጌታችን እንድርያስንና ደቀ መዛሙርቱን ከባሕሩ ማዕበል የተነሣ መታገሥ እንድትችሉ ተነሥታችሁ እንጀራ ብሉ አለ። አንድርያስም አድንቆ እንዲህ አለው በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት እንጀራ እግዚአብሔር ይስጥህ። ደቀ መዛሙርቱ ግን በባሕር ላይ ጉዞ ስለአልለመዱ ከባሕሩ ማዕበል ፍርሀት የተነሣ መብላት መነጋገርም ተሳናቸው ።
ጌታችንም እንድርያስን ደቀ መዛሙርትህን ወደ ምድር እንዲወርዱ እዘዛቸው ሲፈሩ አያቸዋለሁና ይህ ካልሆነ እንዳይፈሩ አንተ የኢየሱስ ደቀ መዝሙሩ ከሆንክ ጣዕም ባለው ቃል አስተምራቸው እነሆ ከየብስ ርቀናልና አለው። ጌታችንም መርከቡን መቅዘፍ ጀመረ እንድርያስም ማስተማርና ማጽናናት ያዘ በልቡም ጸለየ ያን ጊዜም ከባድ እንቅልፍን አንቀላፉ ስለተኙለትም እንድርያስ ደስ አለው።

እንድርያስም ወደ ጌታችን ተመልሶ እንዲህ አለው ዐሥራ አራት ጊዜ በባሕር ላይ ጒዞ አድርጌአለሁ እንዳንተ የሚቀዝፍ አላገኘሁም። ጌታም መልሶ እንዲህ አለው እኛስ በባሕር ላይ ስንጓዝ ሁል ጊዜ እንቸገራለን። ነገር ግን አንተ የክብር ባለቤት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደሆንክ ባሕር ስለአወቀችህ ማዕበሏን በአንተ ላይ አላነሣችም እንድርያስም በታላቅ ቃል እንዲህ ብሎ ጮኸ። የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግንሃለሁ ከሚያከብርህ ሰው ጋር ተገናኝቼ ተነጋግሬአለሁና።
ከዚህም በኋላ ጌታችን እንድርያስን እንዲህ አለው አንተ የክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ነህና ንገረኝ። አይሁድ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ስለምን አላመኑም የሠራውን ብዙ ድንቅ ተአምርን ሰምተናልና አለው። እንድርያስም እንዲህ አለው አዎን ወንድሜ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ገልጦልናል አንካሶችንም በትክክል እንዲሔዱ አድርጓልና፣ ደንቆሮዎችንም አሰምቷልና፣ ዲዳዎችንም አናግሮአልና፣ ለምጻሞችንም አንጽቷልና፣ ውኃውንም ወይን አድርጓልና፣ አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣን አንሥቶ ያዘ ሕዝቡንም በመስክ ሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ ሣሩም እንጀራ እስቲለብስ ድረስ በልተው ጠገቡ የተረፈውንም በብዙ ቅርጫቶች አነሣን ይህም ሁሉ ሲሆን አላመኑም።
ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው ይህን ያደረገ በግልጥ ነው ወይስ በሥውር። እንድርያስም እንዲህ አለው ይህንስ በግልጥ ነው ያደረገ በሥውር ያደረገውም አለ ግን የምትፈትነኝ መሰለኝ ጌታችንም እንዲህ አለው ወንድሜ ሆይ ልቤን ደስ ስለሚላት ነውና ንገረኝ።
እንድርያስም እንዲህ አለው ልጄ ሆይ በጎ ሥራህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ አሁንም ስማ ጌታችን ያደረገውን ተአምር እኛ ዐሥራ ሁለታችን ሐዋርያቶቹ ከእርሱ ጋራ ስንጓዝ ከሊቃነ ካህናትና ከሕዝቡ ብዙዎች አሉ። ወደ ምኵራብም ደረስን ጌታችንም እንዲህ አለ በሰማይ ባሉ በኪሩቤልና በሱራፌል አምሳል በምድር ላይ ሰው የሠራትን ይቺን የተቀረጸች ሥዕል ታያላችሁን።
ከዚህም በኋላ ወደሥዕሊቱ ተመልሶ ብልህ ሰው የተጠበበብሽ የሰማያውያን መልክን ያደረግሽ አንቺን እላለሁ ከቦታሽ ተነቅለሽ ውረጂ የካህናት አለቆችንም ውቀሻቸው እኔም ዕሩቅ ብእሲ ወይም እግዚአብሔር እንደሆንኩ መስክሪ አላት። ወዲያውኑ ከቦታዋ ተነቅላ ወረደች እንደሰውም በመናገር እንዲህ አለች እናንተ የደነቆራችሁ አይሁድ የራሳችሁ መደንቆር ያልበቃችሁ ሌሎችንም ለማደንቆር የምትሹ ለድኅነታችሁ ሰው የሆነ እግዚአብሔርን እንዴት ዕሩቅ ብእሲ ትሉታላችሁ አስቀድሞ ሰውን የፈጠረው በንፍሐት ልጅነትንም የሰጠው ይህ ነው።
አብርሃምን የተናገረው፣ ይስሐቅንም ከመታረድ ያዳነው፣ ያዕቆብንም ወደ አገሩ ያስገባው ይህ ነው ለሚፈሩት በረከትን የሚሰጥ ለማይታዘዙለት ቅጣትን የሚያዘጋጅ ይህ ነው ።
እውነት እነግራችኋላሁ እናንተ ስለምትክዱት ሕጉንና ሥርዓቱንም ትለውጣላችሁና ስለዚህ እነሆ መስዋዕታችሁ ይሻራል ምኵራቦቻችሁም በዋሕድ ወልደ እግዚአብሔር ስም አብያተ ክርስቲያናት ይሆናሉ። ይህንንና የሚመስለውን ተናግራ ዝም አለች።
እኛም የካህናት አለቆችን መልሰን እንዲህ አልናቸው እነሆ ቅርጺቱ ሥዕል ተናግራ ወቀሰቻችሁ ታምኑ ዘንድ ይገባችኋል። የካህናት አለቆችና አይሁድም እንዲህ አሉን ይህ የሚያናግረው በሥራይ ነው አብርሃምን በወዴት አገኘው ከሞተ ዘመኑ ብዙ ነውና።
ጌታ ኢየሱስም ወደ ቅርጺቱ መለስ ብሎ እንዲህ አላት አብርሃምን እንዳነጋገርኩት አላመኑምና ሔደሽ እንዲህ በይው። አስቀድሞ አዳምን የፈጠረው፣ አንተንም ወዳጁ ያደረገህ፣ አንተ ልጆችህ ይስሐቅና ያዕቆብን ይዘህ ተነሥ ከመቃብርም ወጥተህ ወደዚህ ኑ የካህናት አለቆችን ትወቅሱአቸው ዘንድ እኔ የማውቃችሁና የተነጋገርኳችሁ መሆኔን አስረዷቸው። ቅርጺቱም ሥዕል ይህን ሰምታ እያየናት ሔደች ወደ አብርሃምም መቃብር ደርሳ በውጭ ቁማ ጠራቻቸው። ወዲያውኑ ከሦስቱ አርእስተ አበው ጋር ዐሥራ ሁለቱ ወጡ ከእኛ ውስጥ ወደ ማን ነው የተላክሽ አሏት። ቅርጺቱም እንዲህ ብላ መለሰች ወደ ሦስቱ የአባቶች አለቆች ነው እናንተ ግን እስከ ትንሣኤ ሙታን ድረስ ተኙ ያን ጊዜም ወደ መቃብራቸው ተመለሱ።
321 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 06:58:35
335 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:03:20 ነሀሴ 27 ልደታቸው ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን

አቡነ ዘርአ ብሩክ ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!
፣ተወዳጆች ሆይ ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ባለ 12 ክንፉ አባታችን አቡነ ዘርአ ብሩክ ከእለታት አንድ ቀን በቅዱስ ሚካኤል በአል ታህሳስ 12 ቀን እግዚአብሔር ነፍሳትን ከሲኦል እንዲያወጡ አዘዛቸው። አባታችንም የፈጣሪያቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ወደ ሲኦል ወረዱ። ወደ አስፈሪው ሲኦል ገብተው በእሳት ሰንሰለት ለዘመናት በሰይጣን የታሰሩትን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ነፍሳት አገኙ።

ፃድቁም የእሳቱን ሰንሰለት በፈጣሪያቸው ስልጣን ፈተው እነዛን ምስኪን ነፍሳት ከስቃይ አወጧቸው። ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተመለከቱ። በሲኦል የተናቀች እና የወደቀች የአንድ የደግ መምህር የኤዎስጣቴኦስ ደቀ መዝሙር ስሙም አብሳዲ የሚባል ነፍስ ሰም ከፈትል እንደሚጣበቅ ተጣብቃ በሲኦል ባህር ውስጥ ስትሰቃይ አገኟት።

አቡነ ዘርአ ብሩክም ያቺን ነፍስ "እግዚአብሔር በዚህ የስቃይ ቦታ የጣለሽ በምን በደልሽ ነው" አሏት። ያቺም ምስኪን ነፍስ "በጥቂት ነገር እግዚአብሔር በዚህ የመከራ ቦታ ጣለኝ ኃጥአቴም ""ቂም ""
ናት" አለቻቸው። አባታችን አቡነ ዘርአ ብሩክም "በዚህ በመከራ ቦታ ምን ያህል ዘመን ኖርሽ" አሏት።

ምስኪኗ ነፍስም "በዚህ በመከራ ቦታ ከተቀመጥኩ 500 ዘመን ሆኖኛል" አለቻቸው። አባታችንም ይህን ነገር ከዚያች ነፍስ ሰምተው አዝነው "ከቅዱሳን ጋር በገነት ትኖሪ ዘንድ ነይ ውጪ" አሏት"

ያን ጊዜ ከሞት ጉድጓድ አውጥተው በዚያች ቀን ከሲኦል ከወጡት ነፍሳት ጋር በእግዚአብሔር ፊት አቆሟ። እግዚአብሔርም ያችን ነፍስ በፃድቁ ቃል ኪዳን በገነት ውኃ ተጠምቃ ከገብበት መውጣት፣ ካገኙ ማጣት ከሌለባት ገነት እንደገባች ድንቅ ገድላቸው ይነግረናል።

ቸል የምንለው ቂም ምንኛ የነፍስ እዳና ፍዳ እንደሚያመጣብን፣ ለዓመታት በሲዖል እንደሚያኖረን ልብ እንበል ። የጻድቁ የአቡነ ዘርአ ብሩክ ጸሎት እና በረከት አይለየን።

የዪቲዩብ ቻናል ስለከፈትኩ ለማበረታታት subscribers ያድርጉልኝ ✥ ✥

Bisrat negari kidus gebrel tube ብስራት ነጋሪ ቅዱስ ገብርኤል
https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
598 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:03:08
473 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:18:52
እግዚ ኦኦኦ መሐረነ ክርስቶስ [፫]
በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ [፫]
ያድነነ ከመሀቱ ይሰውረነ
በምህረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ [፫]
ስማነ አምላክነ ወመዳኒነ [፫]
እግዚ ኦኦኦ መሐረነ ክርስቶስ [፫]
እንደቸርነትህ አቤቱ ማረን [፪]
እንደምህረትህ ይቅርታን ስጠን [፪]
ከሀጢአትም አንጻኝ ከክፉ በደሌ [፪]
ለዚያች ክፉ ሐጢአት እንዳልሆናት ሎሌ [፪]
እኔስ አበሳዬን በደሌን ሳውቀው [፪]
ከቶ የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው [፪]
አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረገሁ [፪]
አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቀሁ [፪]
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን [፪]
መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሃን [፪]
አሁን ትባርክ ዘንድ ማኅበራችንን ሀይማኖታችንን
ጌታ ሆይ ላክልን ጰራቅሊጦስን ድንግል ማርያምን
አሁን ትጠብቅ ዘንድ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጌታ ሆይ ላክልን ቅ/ሚካኤል ቅ/ገብርኤል
አቡነ ዘበሰማያት᎐᎐᎐᎐᎐᎐
በሰላመ ገብርኤል᎐᎐᎐᎐᎐

የዪቲዩብ ቻናል ስለከፈትኩ ለማበረታታት subscribers ያድርጉልኝ ✥ ✥

Bisrat negari kidus gebrel tube ብስራት ነጋሪ ቅዱስ ገብርኤል
https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
421 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:28:31 ነገ እኮ ነሐሴ 25 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ

ለስማዕቱ #ቅዱስ_መርቆሪዎስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ /እኔ ጌታዬን አልክድም/ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሱ ፊት ሳይፈራ ሳያፍር ከተናገራቸው የተወሰደ "ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት ተሣሃለነ በከመ ዕበየ ሣህልከ” /ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ እንደ ይቅርታው ብዛት ይቅር ይበለን።”/ አሜን። (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁጥር ፯)

ቅዱስ መርቆሬዎስ አገሩ ሮም አስሌጥስ ነው። አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈጸመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል። የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ “ፕሉፖዴር” ነው፤ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው። በጥበብ በፈሪሀ እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ።

ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል። መምለኬ ጣዖት ነበር። በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አጽናንቶት ዘመቱ። መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት። ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን “አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ /እኔ ጌታዬን አልክድም/ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ። በመጨረሻም ህዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን:: ዘኁልቁ 22፡28

የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕልም በአዎንታ አንገቱን ዘንበል አድርጎ ምስክርነት ሰጥቷል። ይህም ሊታወቅ ዛሬ በሀገራችን በምድረ ተጉለት በስሙ ከታነጸ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ደነነ ስዕሉ እያሉ ሲዘምሩ ጎንበስ ቀና ሲሉ እንደሚታይ ይነገራል። የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤቱ በረከቱ አማላጅነቱ ቃል ኪዳኑ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን። እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ። ማቴ.፲፡፴፰-፵

እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። (ዕብ ፲፪፡፩¬-፪)

የሰማእቱ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን ይጠብቅልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸው ቅዱሳን ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀይጠብቀን አሜን።

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw

259 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ