Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን (፫) | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን (፫)

#ጳጉሜ
የጻጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው።
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጹዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጻመው የፈቃዱ ጾም ነው።

ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው። ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት(5) ወይም(6 )ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት።
በአራት አመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል። በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሥስት ወራት ጸጋ/ Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች ትለያለች። ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ በዘመነ ሉቃስ ማብቂያ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም /ህዳር 15 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል።

በቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ የጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል።
ይህ ግን አንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም/ ጽጌ ጾም / በብዘዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም። የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው። እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው ከቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን።
ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋረስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥቶ ደንበር አሰፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ።

ዮዲ 2:2-7። እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመነ 12 ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ነገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእሰራኤል ልጆች አለቀሱ።

#ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች።
የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበት መንገድ ለመጠበቅ ሱባኤ በገባች በሥስተኛው ቀን ገለፀላት። ዮዲ 8:-2 ። ከዚህ በኅላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል። ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾም በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው።
ስለዚህ ምመዕናን ጥንተ ጠላታችን ሴጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለን ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ።

#የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው።
ይህም #ጻጉሜ የአመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው።

# ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
# ወለወላዲቱ ድንግል
# ወለ መስቀሉ ክብር አሜን (፫)

የዪቲዩብ ቻናል ስለከፈትኩ ለማበረታታት subscribers ያድርጉልኝ ✥ ✥

Bisrat negari kidus gebrel tube ብስራት ነጋሪ ቅዱስ ገብርኤል
https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw