Get Mystery Box with random crypto!

'ድንግል ሆይ! ነደ እሳት የማያቃጥላት በነበልባል ያጌጥሽ ዕፅ ነሽ። በጭንጫ ላይ በታነፀ ፎቅ ለመ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

"ድንግል ሆይ! ነደ እሳት የማያቃጥላት በነበልባል ያጌጥሽ ዕፅ ነሽ። በጭንጫ ላይ በታነፀ ፎቅ ለመኖር እችል ዘንድ በዕውቀት ከፍ ከፍ አድርጊኝ፤ እንዳልወድቅም ደግፊኝ።"
(መልክአ ማርያም)

የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን አደረሳችሁ !!!

«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ሞት ለሟች

ይገባል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

በዓለ አስተርዮ

ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት

ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፋንታ በመሆኑ በሰልሳ አራት

አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው ።
ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም "ሞትሰ

ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ "ትርጉሙ ሞት

ለማንኛውም ሰው የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን

ያስደንቃል ።በማለት አደነቀ። በመሆኑም በ ዓሉ የወላዲት አምላክ

በዓለ ዕረፍት ከመሆኑም የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ

በየዓመቱ ይከበራል ።

የእረፍቷ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስልሳ አራት አመት

በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21ቀን እሁድ እለት ጌታ እልፍ አዕላፍት

መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም

ላሳርፍሽ መጣው አላት ። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ

ወር ከአምስት ቀን በማህፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጅህ

አለችው ። በሲዖል የሚሰቃዩትን ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ

ለእነዚህ ቤዛ ይሆናቸዋል አላት።እኚህን ከማርክልኝ ይሁን አለች ።

ቅድስት ስጋዋን ከቅድስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርነት

በዝማሬ መላእክት አሳረጋት ።ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት

በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው

ባጎበር አድርገው ይዘዋት ወደ ጌቴሰማኔ ሲወስዷት አይሁድ

አይተው ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደሞ

እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አደለምን ንፁ ናውዒ ሥጋሃ

ለማርያም ኑ እናቃጥላት ብለው ተነሱ ።ከመካከላቸው አንዱ

ታውፋኒያ ዘል ያልጋውን ሽንኮር ያዘ።የታዘዘ መላእክ መጥቶ ሁለት

እጁን በሰይፍ ቀጣው ።በድያለው ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን

ዘንበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበር አድርግለት

አለችዉ።ቢመልሰው ድኖለታል ።ከዚም በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ

ከመካከላቸው ነጥቆ ገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯታል ።

የፃድቅ መመኪያ የኃጢያንተስፋ የሆነች እመቤታችን

በረድኤት በአማላጅነቷ ሁላችንንም ትጠብቀን ።

አሜን አሜን አሜን ።
ጥር 21 የአስተርእዮ ማርያም ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌቱ ከሊቃውንቱ ጋር ለማመስገን እንዲረዳን እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል
#ሼር_Share_ያድርጉ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ዋህድ፤ ዕፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ፤ ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ፤ ዮሐንስ በልብሱ ከደነ ገፃ።

ወረብ
እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ በከየት እመ አምላክ/፪/
ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ በከየት/፪/

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ መጽአ ውስተ ዓለም፤ ወዓለሙኒ ኢክህለ ፀዊሮቶ፤ ፆረቶ ወአግመረቶ ማርያም።

ነግሥ
ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ፤ ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ፤ ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፤ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኲሉ።

ዚቅ
እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ፤ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኲሉ፤ አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ፤ ወአግአዛ እምእኩይ ውስተ ሠናይ፤ እሞት ውስተ ሕይወት፤ ወረሰየ ይዝክሩ ስማ ውስተ ኲሉ ዓለም።

ወረብ
ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ/፪/
ወአግአዛ እምእኩይ ውስት ሠናይ እሞት ውስተ ሕይወት/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለእስትንፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት፤ ከመ መዓዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤ ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፤ ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤ በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት።

ዚቅ
አንጺሆ ሥጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ፤ ኃደረ ቃል ላዕሌሃ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ወይቤላ ለድንግል፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሰሎሞን ይቤላ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት፤ ፍናወ ዚአኪ ገነት፤ እስመ ኪያኪ ኀረየ ለታዕካሁ፤ ከመ ትኩኒዮ ማኅደረ ለልዑል።

ወረብ
'አንጺሆ ሥጋሃ'/፪/ ላዕሌሃ ኃደረ/፪/
ቀዲሶ ኪያሃ 'ሃሌ ሉያ'/፪/ ይቤላ ለድንግል/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለገቦኪ ዘሐመልማለ ወርቅ ክዳኑ፤ በከመ ዳዊት ይዜኑ፤ ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ስኑ፤ በልኒ እግዝእትየ አፈቅረከ አኮኑ፤ እንዘ ረዳኢትከ አነ ዘይክለከ መኑ።

ዚቅ
እምሰማያት ወረደ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፤ ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለ፳ኤል፤ ወረደ ስኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ፤ ወስኑሰ ለያዕቆብ ዘይቤ ይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ፤ መድኅን እማርያም።

ወረብ
ወስኑሰ ለያዕቆብ 'ዘይቤ'/፪/ ያዕቆብ/፪/
'ይእቲ ሥጋ'/፪/ እማርያም እንተ ነሥአ መድኅን/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ
ፃዕር ወፃማ፤ ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ሞገስ ወግርማ፤ አጽንዒ በረድኤትኪ ለሕይወትየ ድካማ፤ እምሕይወተ ኄራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ።

ዚቅ
ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና፤ ጠሊላነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና።

ወረብ
ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም 'ጊዜ'/፫/ ዕረፍታ ለማርያም/፪/
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ፤ ዘተመሰለ ባሕርየ፤ ማርያም ድንግል ዐጸደ ወይንየ፤ ንስቲተ ለዕበየኪ እንተ አቅረብኩ ግናየ፤ ኢይትኃደግ ዲበ ምድር ምሥጢ ሰማየ።

ዚቅ
ኦ ትቤ ማርያም እወጽእ እምዝንቱ ሥጋየ፤ ወአሐውር ውስተ ሕይወት ዘለዓለም፤ ኦ ተዘከርኬ ዮሐንስ ዘይቤለከ ሊቅ አመ ትረፍቅ ዲበ ዕንግድዓሁ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ፤ በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕፁብ፤ ማርያም ድንግል ወለተ ኅሩያን ሕዝብ፤ ረሰይኩኪ እግዝእትየ ህየንተ እም ወአብ፤ ይሕፅነኒ ከመ ጥብ ፍቅርኪ ሐሊብ።