Get Mystery Box with random crypto!

#ንፅህት_ቅድስት ንፅህት ቅድስ ቡርክት የአምላክ እናት እመቤት ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱ አንድ ሆኑ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

#ንፅህት_ቅድስት

ንፅህት ቅድስ ቡርክት
የአምላክ እናት እመቤት
ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱ አንድ ሆኑ
ተዋሀዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ/2/
#አዝ
ፍፁም መንፈሳዊ ልዩ ፍቅር
አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር
መሰረቱ ዛሬ ልጆችሽ
ቅድስት ሆይ ባርኪያቸው ተገኝተሽ
#አዝ
ድንግል ጎጇቸውን ቀድሰሽ
እውነተኛ ፍቅር መስርተሽ
በመሀከላቸው ተገኝተሽ
ሁሉን አሰጫቸው አማልደሽ
#አዝ
ሙሽሮቹም አምነው ይጠሩሻል
እናታችን ባርኪን ነይ ይሉሻል
ፈጥነሽ ድረሺና በሰርጋቸው
ነይ ተመላለሺ መሀላቸው
#አዝ
አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ
የህይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ
ሙሽሮቹም ዛሬም ይጠሩሻል
የጎጇችን ፋና ነይ ይሉሻል
#አዝ
ቃና ዘገሊላ ተገኝተሽ
መልካሙን ጋብቻ የባረክሽ
ዛሬም ከልጅሽ ጋር በሰርጋቸው
ነይ ተመላለሺ መሀላቸው

#በወርሀ_ሚያዝያ_ሰርጋችሁን የምትፈፅሙ መልካም ጋብቻ እንዲሆንላቹ እንመኝላቹሀል።

@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam