Get Mystery Box with random crypto!

«ከቅዱስ ገብርኤል ክብር የተነሳ ምድር በራች /ራእ ፲፰ ÷፩ /18፥1» ገብርኤል ማለት የእግዚ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

«ከቅዱስ ገብርኤል ክብር የተነሳ ምድር በራች /ራእ ፲፰ ÷፩ /18፥1»

ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎትና በምሥጋና ታከበራለች፤ በተለይ ታኅሣሥ ፲፱ { 19 } ቀን የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን (ሠለሥቱ ደቁቅን )ከዕቶነ እሳት ( ከነደደ እሳት ) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው
ሊቀ መላአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዛሬም ለኛም ይድረስ
በምናውቀውና በማናውቀው መንገድ በሀገራችን በሕዝባችን ላይ ከምነድ እሳት በምልጃው በተራዳይነቱ ያድነን አሜን
በረከት ረድኤት አይለየን አሜን

ቴሌግራም ተቀላቀሉ
[ https://t.me/wdasemaryam ]

@wdasemaryam