Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2021-10-03 21:11:48
@wdasemaryam
1.4K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 20:17:07 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 21-ብዙኃን ማርያም (የእመቤታችን የበዓሏ መታሰቢያ ነው፡፡)
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አስቀድሞ ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው ቅዱስ ቆጵርያኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
+ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ በነው የጠፉት ድንግሊቱ ዮስቴናም በሰማዕትነት ያረፈችው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም ይህች ዕለት የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም አርዮስን አስተምለው ለመመለስ በኒቅያ የተሰበሰቡባት ዕለት ናት፡፡ የጉባኤውም ፍጻሜ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ኅዳር ዘጠኝ ነው፡፡
+ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ግሸን ደብረ ከርቤ የገባበት ዕለት ነው፡፡ (የመስከረም ዓሥራ ሰባቱን ይመለከቷል፡፡)
+ ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
ቅዱስ ቆጵርያኖስና ድንግሊቱ ዮስቴና፡- ይኽም ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሃዲና ሥራየኛ ነበር፡፡ እንዲያውም ለሥራየኖች ሁሉ አለቃቸው ነበር፡፡ በዚህ በጥንቆላ ሥራው ከመመካቱ የተነሣ ‹‹ሥራይ በማድረግ የሚስተካከለኝ ካለ ልይ እስቲ…›› በማለት ወደ አንጾኪያ አገር ሄደ፡፡ ቆጵርያኖስም አንጾኪያ በገባ ጊዜ ወሬው ሁሉ በሀገሪቱ ተሰማ፡፡ በአንጾኪያ የሚኖር አንድ ወጣት በመልኳ እጅግ ውብ የሆነችውን ወጣት ዮስቴናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሄድ እያያት እጅግ አድርጎ ወደዳት ነገር ግን እርሷ የክርስቶስ ሙሽራ ናትና እሺ ልትለው ስላልቻለች ሊያገኛት አልቻለም፡፡ ገንዘብ በመስጠት፣ በጉልበት በማስፈራራት፣ በሥራይ ሥራ በእነዚህ ሁሉ ሊያገኛት ስላልቻለ ወጣቱ አሁን የቆጵርያኖስን ወደ ከተማው መምጣትና ዝናውን በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት ሄዶ ዮስቴናን እጅግ አድርጎ እንደወደዳትና ሊያገኛት እንዳልቻለ ነገረው፡፡
ቆጵርያኖስም ያንን ወጣት ‹‹እኔ የልብህን እፈጽምልሃለሁ አትዘን›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ቆጵርያኖስ ድንግሊቱን ዮስቴናን እንዲያመጧት በሥራዩ የአጋንንትን ሠራዊት ላካቸው፡፡ እነዚያ በሥራይ ወደ እርሷ ተላኩ አጋንንትም ወደ ድንግሊቱ ዮስቴና በፍጹም ሊቀርቧት አልቻሉም ምክንያቱም እርሷ ዮስቴና በጾም በጸሎቷ የጸናች ናትና ከጸሎቷ የተነሣ አጋንንቱ ተቃጠሉ፡፡ ቆጵርያኖስ በሥራዩ ኃይል ዮስቴናን ያመጡለት ዘንድ ደጋግሞ ላካቸው ነገር ግን አጋንንቱ ቅድስት ዮስቴና በፍጹም ሊቀርቧት አልቻሉም፡፡ ከዚም በኋላ ቆጵርያኖስ ሁሉንም አጋንንት ጠርቶ ‹‹ድንግል ዮስቴናን ይዛችሁ ካላመጣችሁልኝ እኔ ከእናንተ ተለይቼ ክርስቲያን እሆናለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የሰይጣናት አለቃ ቆጵርያኖስን ሊሸነግለው አሰበና ከሰይጣናት ውስጥ አንዱን ሰይጣን በዮስቴና ተመስሎ ለቆጵርያኖስ እንዲታየው አደረገ፡፡ ሰይጣኑም አለቃው እንዳዘዘው እንዲሁ አድርጎ (ዮስቴናን መስሎ) ተዘጋጀ፡፡
ሰይጣኑም ለቆጵርያኖስ ‹‹እነሆ አሁን ዮስቴና መጥታለች›› አለው፡፡ ቆጵርያኖስም እውነት ዮስቴና የመጣች መስሎት እጅግ ደስ ብሎት ሊቀበላት ተነሣ፡፡ በዮስቴና አርአያ የተመሰለውንም ምትሀት ባየ ጊዜ ‹‹የሴቶች እመቤት ዮስቴና ሆይ! መምጣትሽ መልካም ሆነ›› አላት፡፡ ቆጵርያኖስም የቅድስት ዮስቴናን ስሟን መጥራት በጀመረ ጊዜ በእርሷ ተመሰለው ሰይጣን እንደጢስ በኖ ጠፋ፡፡
ቆጵርያኖስም በዚህ ጊዜ የሽንገላው ምክንያት ምትሐቱ ሁሉ ከንቱ እንደሆነ ዐወቀ፣ አስተዋለ፡፡ በልቡም እንዲህ አለ፡- ‹‹ስሟን በጠሩበት ቦታ አጋንንት እንደ እንደጢስ የሚበኑ ከሆነ በቅድስት ዮስቴና ፊት ሊቆሙ ሊሸነግሏትስ እንዴት ይቻላቸዋል?›› አለ፡፡ ይህንንም ብሎ ወዲያውኑ የጥንቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠላቸው፡፡ ሄዶም ቅድስት ዮስቴናን አገኛትና ሰገደላት፡፡ እርሷም ሃይማኖትን አስተማረችውና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ሄዶ ንስሓ ገብቶ ተምሮ አምኖ ተጠመቀ፡፡ የምንኩስና ልብስንም ለበሰ፡፡ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ዲቁና ሾመው፡፡ አገልግሎቱንና መንፈሳዊ ተጋድሎውንም ባየ ጊዜ ዳግመኛም ቅስና ሾመው፡፡ ቆጵርያኖስም በተጋድሎና በአገልግሎት ከኖረ በጎ ምግባሩ፣ ሃይማኖት፣ ትሩፋቱ ከፍ ባለ ጊዜ በምዕራባዊቷ ግዛት ኤጲስ ቆጶስነት ተሾመ፡፡ ቅድስት ዮስቴናንም ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት፡፡
በግርጣግና የቅዱሳን ስብሰባ በሆነ ጊዜ ቅዱስ ቆጵርያኖስ ከጉባው አባላት አንዱ ነበር፡፡ ከብዙ ወራት በኋላም ከሃዲው ንጉሥ ዳኬዎስም ስለ ቅዱስ ቆጵርያኖስና ስለ ቅድስት ዮስቴና ሰማ፡፡ ንጉሡም ወደ እርሱ አስመጣቸውና
@wdasemaryam
@wdasemaryam
1.2K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 20:16:55
@Wdasemaryam
1.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 20:52:24
@wdasemaryam
@wdasemaryam
2.0K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 07:03:19 ✥እንኳን፡ለብርሃነ፡መሥቀሉ፡በሠላም፡በጤና፡አደረሣችሁ።✥

✥የመስቀሉ፡ቃል፡ለሚጠፉት፡ሞኝነት፥ለእኛ፡ለምንድን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ኀይል፡ነውና።✥

፩ኛ ቆሮንጦስ ፩÷፲፰



✥✥✥✥✥✥



✥መልካም በዓል✥
@wdasemaryam
2.4K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-23 20:53:21 (ሥር ሰዳችኹ በርሱ ታነጹ፥እንደ ተማራችኹም በሃይማኖት ጽኑ፥ምስጋናም ይብዛላችኹ።ቆላሲስ 2:7)
(አንድ፡ጌታ፡አንድ፡ሃይማኖት፡አንዲት፡ጥምቀት፤ኤፌ 4:5)
70 የኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች
1) የዳዊት ልጅ (ማቴ ፩፥፩)
2) የአብርሃም ልጅ (ማቴ ፩፥፩)
3) ክርስቶስ (ማቴ ፩፥፲፮)
4) ኢየሱስ (ማቴ ፩፥፳፩)
5) ዐማኑኤል (ማቴ ፩፥፳፫፤ ኢሳ ፯፥፲፬)
6) ተወዳጅ ልጅ (ማቴ ፫፥፲፯)
7) የእግዚአብሔር ልጅ (ማቴ ፳፮፥፷፫)
8) የሰው ልጅ (ማቴ ፳፮፥፷፬)
9) የአይሁድ ንጉሥ (ማቴ ፳፯፥፴፯)
10) የናዝሬቱ ኢየሱስ (ማቴ ፳፮፥፸፩)
11) ደንጊያና የመአዝን ራስ (ማር ፲፪፥፲)
12) የእስራኤል ንጉሥ (ማር ፲፭፥፴፪)
13) የልዑል ልጅ (ሉቃ ፩፥፴፪)
14) የመዳን ቀንድ (ሉቃ ፩፥፷፱)
15) ከላይ የመጣ ብርሃን (ሉቃ ፩፥፸፰)
16) ወልደ ማርያም (ሉቃ ፪:፱)
17) አቤቱ (ሉቃ ፰፥፳፬)
18) የተመረጠ ልጅ (ሉቃ ፱፥፴፭)
19) ሕያው (ሉቃ ፳፬፥፭)
20) ቃል (ዮሐ ፩፥፩)
21) አንድ ልጁ (ዮሐ ፩፥፲፰)
22) ረቢ (መምህር) (ዮሐ ፩፥፴፱)
23) መሲሕ (ዮሐ ፩፥፵፩)
24) ልጁ (ዮሐ ፰፥፴፮)
25) የእግዚአብሔር በግ (ዮሐ ፩፥፴፮)
26) እግዚአብሔር (ዮሐ ፩፥፩)
27) ሙሽራ (ዮሐ ፫፥፳፱)
28) የዓለም መድኀኒት (ዮሐ ፬፥፵፪)
29) የእግዚአብሔር እንጀራ (ዮሐ ፮፥፴፫)
30) የሰማይ እንጀራ (ዮሐ ፮፥፴፪)
31) የሕይወት እንጀራ (ዮሐ ፮፥፴፭)
32) የዓለም ብርሃን (ዮሐ ፰፥፲፪)
33) እኔ (ዮሐ ፰፥፶፰፤ ዘፀ ፫፥፲፬)
34) መልካም እረኛ (ዮሐ ፲፥፲፩)
35) ትንሣኤና ሕይወት (ዮሐ ፲፩፥፳፭)
36) መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት፣ በር (ዮሐ ፲፬፥፮)
37) እውነተኛ የወይን ግንድ (ዮሐ ፲፭፥፩)
[በሐዋርያት ሥራና በመልእክታት]
38) ቅዱስና ጻድቅ (የሐዋ ፫፥፲፬)
39) የሕያዋንና የሙታን ፈራጅ (የሐዋ ፲፥፵፪)
40) ጌታ (ሮሜ ፲፥፱-፲፫)
41) መድኀኒት (ሮሜ ፲፩፥፳፮)
42) የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ (፩ኛ
ቆሮ ፩፥፳፬)
43) በግዐ ፋሲካ (፩ኛ ቆሮ ፭፥፯)
44) ኋለኛው (ዳግማይ) አዳም (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፵፭)
45) የቤተ ክርስቲያን ራስ (ቆላ ፩፥፲፰)
46) ሕያው አምላክ (፩ኛ ጢሞ ፬፥፲)
47) በኲር (ዕብ ፩፥፮)
48) ሐዋርያ (ዕብ ፫፥፩)
49) ታላቅ ሊቀ ካህናት (ዕብ ፬፥፲፬)
50) የእምነታችን ራስና ፈጻሚ (ዕብ ፲፪፥፪)
51) የነፍስ እረኛና ጠባቂ (፩ኛ ጴጥ ፪፥፳፭)
52) የእረኞች አለቃ (፩ኛ ጴጥ ፭፥፬)
53) የሕይወት ቃል (፩ኛ ዮሐ ፩፥፩)
54) የአብ ልጅ (፪ኛ ዮሐ ፩፥፫)
55) የእግዚአብሔር አንድ ልጅ (፩ኛ ዮሐ ፬፥፱)
በዮሐንስ ራእይ
56) በኲረ ሙታን (ራእ ፩፥፭)
57) የምድር ነገሥታት ገዢ (ራእ ፩፥፭)
58) የታመነው ምስክር (ራእ ፩፥፭)
59) አሜን (ራእ ፫፥፲፬)
60) የይሁዳ አንበሳ (ራእ ፭፥፭)
61) የታረደው በግ (ራእ ፭፥፲፪)
62) የታመነና እውነተኛ (ራእ ፲፱፥፲፩)
63) የእግዚአብሔር ቃል (ራእ ፲፱፥፲፫)
64) ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)
65) የነገሥታት ንጉሥ (ራእ ፲፱:፲፮)
66) የጌቶች ጌታ (ራእ ፲፱፥፲፮)
67) አልፋና ኦሜጋ (ራእ ፳፪፥፲፫)
68) መዠመሪያውና መጨረሻው (ራእ ፳፪፥፲፫)
69) የዳዊት ሥርና ዘር (ራእ ፳፪፥፲፮)
70) የሚያበራ የንጋት ኮከብ (ራእ ፳፪፥፲፮)
@wdasemaryam
@wdasemaryam

#Share...
3.0K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 20:38:57 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 10-የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባበት ዕለት ነው፡፡
+ ጸዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሣላት ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር የተገለጠበት ዕለት ነው፡፡
+ ከከሃዲው ከሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ያዳነቻቸው ጥበበኛዋ ዮዲት ዐረፈች፡፡
+ ቅድስት አትናስያና ሦስት ልጆቿ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህችም ዕለት የከበረች ቅድስት መጥሮንያ በሰማዕትነት ዐርፋለች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት መጥሮንያ፡- ይህችውም ሰማዕት ቅድስት መጥሮንያ የአንዲት አይሁዳዊት ሴት አገልጋይ ነበረች፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊ ሴትም ቅድስት መጥሮንያን ክርስቲያን በመሆኗ ብቻ ሸክም ታበዛባትና ታንገላታት ነበር፡፡
ከሃይማኖቷም አውጥታ ጌታችንን ማመንን ልታስተዋት ብዙ ሞከረች፡፡ በአንዲት ዕለትም አይሁዳዊቷ ይዛት ወደ ምኩባራባቸው ሄደች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ግን ወደ ምኩራባቸው ሳትገባ ተመልሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ጸሎት አደረገች፡፡ ወደ ቤታቸው ተመልሰው በገቡ ጊዜ አሠሪዋ ‹‹ወደ እኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም?›› ብላ ጠየቀቻች፡፡ ቅድስት መጥሮንያም ‹‹ከእናንተ ምኩራብ እግዚአብሔር ርቋልኮ፣ እንዴት ወደ እርሱ እገባለሁ! በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት›› አለቻት፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊትም ከቅድስት መጥሮንያ ይህንን በሰማች ጊዜ እጅግ ተቆጥታ በኃይል ደበደበቻት፡፡ በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጋችባትና ያለምግብና ያለመጠጥ ለ4 ቀን አሠረቻት፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ውጭ አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ድጋሚ በእሥር ቤት ጣለቻትና በዚያው ተንገላታ ዐረፈች፡፡ ነፍሷንም እግዚአብሔር ተቀብሎ የሰማዕታትን አክሊል አቀዳጃት፡፡ አሠሪዋ ግን ሥጋዋን አውጥታ በመጣል በዚያም መጥሮንያ ራሷን የገደለች አስመሰለች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ራሷን የገደለች ስለመሰለ አይሁዳዊቷን ሴት ግን ማንም የመረመራት የለም፡፡ ነገር ግን ለተገፉ የሚፈርድ፣ ለተበደሉ የሚበቀል እውነተኛ ዳኛ ልዑል እግዚአብሔር ቁጣው በዚያች አይሁዳዊ ሴት ላይ ወረደ፡፡ ከደርቧ ላይ ስትወርድ ድንገት ወድቃ በዚያው ከመቅጽበት ሞተች፡፡ በነፍሷም ወደ ዘላለማዊ እሳት ሄደች፡፡
ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + + +
ጼዴንያ ማርያም፡- ጼዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሠርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብልታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረና ጠዋት ሊሄድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት ‹‹የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ገንዘቡን ሥዕሉን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ›› ብሏት ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ «አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ በጣም ደንግጦ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው እየሮጠ ወደ እርሱ ሲመጣበት አየ፡፡ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፣ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምፅ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡ መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያሟም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ፡፡
ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡ ያም መነኩሴ እነኚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በተመለከተ ጊዜ በልቡ «ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጽዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሄዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ አሁንም ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው? እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው» አለችው፡፡
መነኩሴውም «ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡ ተቀብላም ሥዕል ቤት አሠርታ በክብር አስቀመጠቻት፡፡ ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት፡፡ ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕል ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ፣ ዐይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም 10 ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡ ይህም በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ሁልጊዜ ይከበራል፡፡ የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ጣዕሟን ታሳድርብን፣ ልጇ አምላካችን በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + +
ዳግመኛም የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው በዚህ ዕለት ነው፡፡የቅዱስ መስቀሉ ፍቅር ይደርብን።
@wdasemaryam
@wdasemaryam
Share...
3.0K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 20:38:44
2.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 19:16:32 ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ †††

††† መስከረም 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †††

+" ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት "+

††† ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል:: ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ: አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው:: ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል:: (መዝ. 33:7)
¤እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል:: (መዝ. 90:11)
¤የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው:: (መሳ. 13:18)
¤ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! (ዳን. 10:21)
¤ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው:: (ዳን. 12:1)
¤በፊቱ ሲቆምም ስለ ክብሩ ጫማ አውልቆ: ባጭር ታጥቆ ነው:: (ኢያ. 5:13)

+ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር በዚህች ዕለት መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች:: በድሮው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች:: ይህች ከተማ ክርስቲያኖችም: ኢአማንያንም ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት::

+በከተማዋ የክርስቲያኖች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በእምነት ግን ጠንካሮች ነበሩ:: በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ባለ ፍጹም እምነት ሰው ነበር:: በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረጉ ነበር:: ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ (ዮናናውያን) ግን ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ::

+በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ:: በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ:: በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር::
+ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት:: ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ:: ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ::

+በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ቢወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው:: አሰበው: ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ ሊሆን ነው::
+እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ ቅዱስ ሚካኤልን ተማጸነ:: ከዚያ ላለመውጣትም ወሰነ:: ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ:: በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ::

+መጋቢውንም "ጽና: አትፍራ" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት:: በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ:: ወንዙም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ::
+የሚገርመው ሸለቆው የተፈጠረው በቤተ ክርስቲያኑ በታች ነው:: ቅዱስ ሚካኤል ግን መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ:: በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው:: መልአኩንም አከበሩት:: አሕዛብ ግን አፈሩ::

††† ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት †††

††† በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያን መሆን ብቻ የሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ ነበር:: ከምንም በላይ መከራው የጸናባቸው ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነበሩ:: ክደው ያስክዳሉ በማለት አብዝተው ያሰቃዩአቸው ነበር:: ቶሎም አይገድሏቸውም:: መከራውን ከማራዘም በቀር::

+ከእነዚህም አንዱ አባ ቢሶራ ነው:: እርሱ በምድረ ግብፅ 'መጺል' ለምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ነበረ:: በእድሜው አረጋዊ: በትምሕርቱ ምሑር: በምግባሩ ቅዱስና በእረኝነቱም የተመሠከረለት በመሆኑ በምዕመናን ዘንድ ተወዳጅ ነበር::

+መከራው እየገፋ ሲመጣ ግን ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት:: ስለ ሃይማኖት መሞትን እና ቶሎ ወደ ክርስቶስ መሔድን ናፈቀ:: ነገር ግን መልካም እረኛ ነውና በጐቹን (ምዕመናንን) እንዲሁ ሊተዋቸው አልወደደም:: ሰብስቦ ምን እንዳሰበ አማከራቸው:: የሰሙት ነገር ክርስቲያኖችን አስለቀሳቸው::

+"አቡነ ለመኑ ተኀድገነ-አባታችን ለማን ትተኸን ትሔዳለህ?" ሲሉም ከእግሩ ወደቁ:: እርሱ ግን አስረድቷቸው: አጽናንቷቸውም በእንባ ተሰናበታቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ "አብረንህ እንሞታለን" ብለው ተከተሉት:: ቅዱስ አባ ቢሶራን ከብዙ ስቃይ በኋላ አረማውያን ከነተከታዮቹ በዚህ ቀን ገድለውታል::

††† ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ †††

††† በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው:: ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው:: መንግስትን: ዙፋንን: ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል::

+ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ:: በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም:: በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና በጸሎት ተጋደለ::

+በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም: ሰውም አይቶ አያውቅም:: በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች:: እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ተራዳኢ መልአክን ይዘዝልን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::

††† መስከረም 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት
3.ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ
4.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት (ልደቱ)
5."14,730" ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማሕበር)

††† የፋርስ መንግስት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቁዋቁዋመኝ:: እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ:: እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት:: ††† (ዳን. 10:13)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››
@wdasemaryam
@wdasemaryam
Share ...
2.4K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 19:16:21
2.1K views✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ