Get Mystery Box with random crypto!

ስ መድኃኔ ዓለም ሆይ፤ ኃያላን ሊቃነ መላእክት በፊትህ መቆም የማይቻላቸው። አንተን ልባቸው እንደ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam


መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ኃያላን ሊቃነ መላእክት በፊትህ መቆም የማይቻላቸው። አንተን ልባቸው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ጭፍሮች በሕዝብ አደባባይ ፊት አቆሙህ አቤቱ ! !
ፈጣሪየ ክርስቶስ ሆይ፤
ያለመጉደል እግዚአብሔር ዘሲና እግዚአብሔር ዘግብፅ እየተባልክ የምትመሰገን ዘንድ እግዚአብሔር ነህ። ዬ ዬ ዬ ስለኛ እንጨት ላይ ሰቀሉህ። አቤቱ ! አዲስ በታነፀ መቃብር መቃብር ጨምረው ቀበሩት። አቤቱ ! ! ።
ተማኀፀንኩ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
መጻጻውን መሪር ሐሞት በአጠጡህ ጊዜ ሁሉ ተፈጸመ በማለት በ 9 ሰዓት በገዛ ሥልጣንህ ነፍስህን ከስጋህ ለለየህባት ፀዓተ ነፍስህ ሰላም እላለሁ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
የኃያላን ጌታ የፍጥረታትም ሁሉ ፈጣሪ እንደ መሆንህ በዚያች ነፍስህ ከሥጋህ በተለየችበት ሰዓት የሲኦል ጠባቂዋ እስኪፈራ ሞት እስኪደነግጥ ድረስ መሬት ተነዋወጠች መቃብራት ተከፋፈቱ።
ተዘከረነ እግዚኦ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
አስቀድሞ ፊያታዊ ዘየማንን እንዳሰብከው አቤቱ አዳኝ ቤዛ በሚሆን መስቀልህ አስበን።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ ቸር ጠባቂ ነህና እንደዓይን ብሌን ጠብቀኝ። አቤቱ እኔን መከረኛውን ኀዘንተኛውን ሰው በምስጋናህ የወይን ጠጅ አስደስተኝ አረጋጋኝ።
ኦ ዘአዖሩከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
እጅ እግርህን በመቸንከር የኛን መከራ አሸክመው በቀራንዮ በተራራ ላይ ለአቆሙህ ማቆም ሰላም እላለሁ።ነገር ሊናገር ክሂሎት ይኖረዋል።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
አቤቱ የመልከ ጼዴቅ ምሳሌው ካህን ሆይ አንተ ግን በአንደበቱ መናገር ሲጀምር ባርከው አክብረው በሱላይ ቅዱስ መንፈስህን አሳድር::
ዘጸውአ ስመከ
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ስምህን የጠራ መታሰቢያህንም ያደረገ እሱ በዚያ በቁርጥ የፍርድ ቀን ከንቱ ሁኖ አይቀርም።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ቅድመ ዓለም የነበርክ ዛሬም ያለህ ለዘለዓለሙም ጸንተህ የምትኖር አምላክ ስትሆን የታሠሩ አገልጋዮችህን አንተ ታስረህ ፈታሃቸው በሞትህም ሞተህም የሞቱትን ወገኖችህን አስነሳሃቸው።
ለኀጡአ ምግባር
መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ሃይማኖት ስንዃ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ አነስተኛው አገልጋይ ማደሪያ ቤት መኖሪያ ቦታየ ከቅዱሳኖችህ ጋር ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን አቤቱ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከከንቱ ሞት አድነኝ።ሁሉ ከንቱ ነው። የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው። ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።
ስብሐት ለከ
አቤቱ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ምስጋና ይገባል። አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ የምትሆናቸው ለአንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።
አቤቱ ነፍስና ስጋን አዋህደህ በምግባር ሃይማኖት አጽንተህ የምታከብራቸው ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።
አቤቱ በመንግስትህ ሽረት በህልውናህ ሞት ኀልፈት የሌለብህ ለአንተ ለንጉሥ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል አቤቱ የቅዱስ አብ አካላዊ ቃል ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
አቤቱ አምልካችን ህያው ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ እንደ ቸርነትህ ሀገራችን ኢትዮጵያ አስባት
@wdasemaryam
@wdasemaryam