Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለፃድቁ ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አባታችን አቡነ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

እንኳን ለፃድቁ ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእለተ ቀናቸው የልባችሁን መሻት ይሙሉላችሁ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ አሜን አሜን አሜን::
አሜን አሜን አሜን
ገድሉ ታአምራቱ
*************************
ገድሉ ታአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋህዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለሐይማኖት ዘኢትዮጵያ
አ.ዝ .........................//
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፍር የታጠቀ
ንጹህ ባሕታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የፀጋዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አሰከተለ
አ.ዝ .........................//
ደካማ መስሏቸው በአንደ እግሩ ሲያዩት
ባለ ስድስት ክንፉ ተክልዬ የእኛአባት
እሱስ አንበሣ ነው ይናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አ.ዝ .........................//
ከካህናት መካከል ህሩይ ነው ተክልዬ
መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ
እትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቷን ባረካት
አ.ዝ .........................//
የባረከው ውኃ የረገጠው መሬት
ገላው ያረፈበት ሆኗል ፀበል እምነት
ኑና ተመለከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክልዬ ዛሬም እንደ ጥንቱ
@wdasemaryam
@wdasemaryam
✥ደሳለኝ✥