Get Mystery Box with random crypto!

ጥቅምት 4 #ወንጌላዊዉ_ዮሐንስ ቅዱስ #ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ፍቊረ_እግዚእ ለወርሐዊ በ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

ጥቅምት 4 #ወንጌላዊዉ_ዮሐንስ

ቅዱስ #ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ፍቊረ_እግዚእ ለወርሐዊ በአሉ እንኳን አደረሰን

የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም

ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው

ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው

ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው

ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው

የፍቁረ እግዚእ #ቅዱስ_ዮሐንስ ረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"

በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸው ቅዱሳን ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን "አሜን"



T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw