Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን_አደረሳቹሁ ሰማእቱ እስጢፋኖስ , ጥቅምት 17 በዚህ ቀን የዲያቆናት አለቃ የሰ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

እንኳን_አደረሳቹሁ ሰማእቱ እስጢፋኖስ

, ጥቅምት 17 በዚህ ቀን የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ ቅዱስ እስጢፋኖስ ለተሾመበት ቀን መታሰቢያ ነው።
እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም «አክሊል» ማለት ነው።

ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር። ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል።

ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ። ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል።

በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ።
ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ። ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ «ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው» በመጨረሻም «ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል»ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት

አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። 《የሐ ሥራ 7፥58—60》

የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን



T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw