Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.03K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-05 16:20:51
ኢትዮጵያ እና ብራዚል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ብራዚል የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በኢንቨስትመንት፣ በአቪዬሽን፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በማእድን እና በታዳሽ ሃይል በትብብር መስራት እንደሚችሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ በበኩላቸው መንግስታቸው በስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማስታወቃቸውን ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
2.5K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 16:10:24

2.4K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 15:44:10
የቦሌዋ ገበሬ

በኢየሩስ ወርቁ

እሌኒ ተሾመ ትባላለች የአዲስ አባባ ከተማ ነዋሪ ናት፡፡ የአራት ልጆች እናትና ልጆቿን ያለ አባት የምታሳድግ ብርቱ ሴት ናት፡፡ በኑሮዋ ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፈችው እሌኒ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮዋን የሚደግፍላት እንድ ብስራት ከወደ ቤተመንግስት አንደተበሰረላት ትናገራለች፡፡

የከተማ ግብርና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተበሰረበት ግዜ ጀምሮ ጊዜ ሳታጠፋ ወደሰራ የገበችው ብርቱ ሴት ኑሮዋን ያቀለለላትን የከተማ ግብርናን ተቀላቀለች፡፡ በዚህም የእሷንና የቤተሰቧን ህይወት በቀላሉ ለመግፋት አዲስ መንገድ እንደፈጠረላት ትገልጻለች፡፡

እሌኒ እንደ ሁሉም ኢትዮጲያዊያን እናቶች ልጆቿን በፈተና የምታሳድግ ሴት ናት፡፡ ከኢሌኒ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ማስፈንጠሪያውን በመጫን መሉ ጽሁፉን ያንቡቡ!!

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/652608043572195
2.8K viewsedited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 14:50:17
አመሻሽ በ12 ሰዓት ይጠብቁን !!
3.0K viewsedited  11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:55:16

3.3K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:05:02
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከብራዚሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተገናኙ

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ተገናኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር ዛሬ ተገናኝተናል ብለዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ግንኙነትን ስለማጠናከር እና በብዝኃ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
3.5K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:03:13
የቀን 6፡00 ዜና ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ግንቦት 28/2015 https://fb.watch/kZnABvBOnX/
3.1K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 10:45:19
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሄደዋል።

በሳምንቱ ከተደረጉ ውድድሮች መካከል በስዊድን የተካሄደው የስቶኮልም ማራቶን ይገኝበታል።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በወንዶች አትሌት አሸናፊ ሞገስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ደራራ ሁሬሳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጸጋዬ መኮንን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን በበላይነት ጨርሰዋል።

በሴቶቹ ውድድር አትሌት ሲፋን መላኩ አንደኛ በመውጣት ስታሸንፍ አትሌት ሶሮሜ ነጋሽ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት የኔነሽ ዲንቄሳ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ማጠናቀቃቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
3.5K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 09:02:08
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከ #ዋልታ_ቴቪ ግንቦት 28/2015 https://fb.watch/kZcUOfpFo9/
3.5K views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 21:53:42

4.2K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ