Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.03K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-06-04 20:59:54

4.1K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 15:03:04
ኀልዮት

እንፅና!
(በቴዎድሮስ ኮሬ)
ፅናት ከተሰጥኦ፣ ከዕውቀትና ክህሎት በእጅጉ የላቀ ነው። ተስፋ ባለመቁረጥ ውስጥ ትልቅ ስጦታ አለ። ህይወት እንዳሰብነው ላይሄድ ይችላል፤ነገር ግን እርምጃዎቻችን ትንንሽ ቢሆኑ እንኳን ወደፊት መጓዛችንን አንግታ። ሁለቱ ታላላቅ ልማዶች ትዕግስትና ዕናት በስኬትና በውድቀት፣ በእውነተኛ ለውጥና ባሉበት ቦታ በመቅረት መካከል ያለውን የሚወስኑ ናቸው።

https://www.facebook.com/100064690148931/posts/pfbid02RJBESxAcmqLhi9qXJpot5E24QoJTMzEjBFVxvNQG5GDjySswR1sjdqLeCakZPv63l/?app=fbl
200 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:34:01

541 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:21:58

670 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 12:03:34
የቀን 6፡00 ዜና ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ግንቦት 3/2015https://fb.watch/ksq9IUDMQE/
1.4K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 11:54:23
የረጅም ጊዜ ዝቅተኛ የካርበን ልቀትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ልማት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ግንቦት 03/2015 (ዋለታ) ኢትዮጵያ የረጅም ግዜ የአነስተኛ ካርቦን ልቀትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ይፋ አደረገች ፡፡

ስትራቴጂው ይፋ የተደረገው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ ሚኒስትሮች፣ አምባባሳደሮቾ እና ሌሎች በዘርፉ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው።

የኢትዮጵያ የረጅም ግዜ ዝቅተኛ ካርበን ልቀት ልማት ስትራቴጂ የተዘጋጀው በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሲሆን ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በጋራ ተግባር ላይ ይውላል ተብሏል።

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአየር ንብረት ለውጥ ባለፉት አመታት ሀገራችን ላይ አሉታዊ ተጽኖ ማሳደሩን አስታውሰው የምንፈልገውን ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ የአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያም ባለፉት ግዚያት የተለያዩ የፖሊሲ ማእቀፎች አዘጋጅታ ሰራ ላይ ስታውል መቆየቷን አንስተዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ምንም እንኳን አሁን ላይ አማቂ ጋዝን ወደ አየር በመልቀቅ ትልቅ ደርሻ ባይኖራትም፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ከልማት እቅዶች ጋር አስተሳስሮ መጎዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

መንግስት ይህን በመገንዘብ በአስር ዓመት መሪ የልማት እቅድ ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይን እንደ አንድ ምሰሶ አድርጎ ማካተቱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በመስከረም ቸርነት
1.5K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 11:07:02
የሌማት ትሩፋት ትግበራ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ስለሚኖረው ፋይዳ ላይ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

ግንቦት 3/2013 (ዋልታ) የሌማት ትሩፋትን በመተግበር ምግብ ዋስትናን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል የግብርና ሚኒስቴር ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር የፓናል ውይይት እያካሄደ ነው::

በፓናል ወይይቱ ላይ ከአለም አቀፍ እና ከልማት አጋር ድርጅቶች የመጡ ተገባዥ እንግዶች ፣ ከምርምር ተቋማት እና ከዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ እንግዶች ተሳትፈዋል ::

የፓናል ውይይቱን በይፋ የከፈቱት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ኢትዮጵያ ግዙፍ የአሳ እርባታን ጨምሮ ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ልማት ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ይህንን ሀብት ባለፉት ዓመታት ሳንጠቀም መቆየቱን አስታዉሰዋል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በሌማት ትሩፋት በምግብ ራስን ለመቻል እየተሰራ ያለዉ ስራ አመርቂ ውጤት የታየበት ነው ብለዋል ::

አፈ ጉባኤው አክለውም በአረንጓዴ አሻራ እና በስንዴ ልማት ያስመዘገብነውን ውጤት በሌማት ትሩፋት ልንደግም ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት በሁሉም ክልሎች ይፋ ተደርጐ ወደ ስራ ከተገባ ወዲህ በአርብቶ አደሩ እና አርሶ አደሩ ዘንድ ልዩ መነቃቃት መፍጠሩን ተናግረዋል::

የሌማት ትሩፋት ከተጀመረ ዘጠነኛው ወሩ ሲሆን ከ34 ሚሊዮን በላይ ጫጩቶች፣ 1.2 ሚሊዮን የንብ ማነቢያ ቀፎዎች እና 1.2 ሚሊዮን ላሞች አቅርቦት መደረጉንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በዋናነት ከውጭ የሚገቡ የሌማት ትሩፋቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ::


በሜሮን መስፍን
1.7K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:08:04 "ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ አየር፤ ሰላማዊ ሕዝብ ያለበት አንዱ ቦታ ዳውሮ ይባላል። ኑ እና ዕረፉ፤ ኑ እና አስቡ፤ ኑ እና ጻፉ። ለብዙ ሥራዎች አእምሯችሁ እንዲከፈት፤ ውስጣችሁ እንዲረጋጋ፤ አእምሯችሁን እንድትጠቀሙ የሚያስችል የሕዝብ እና የአካባቢ ሰላም ያለበት ቦታ ነው፤ ሐላላ ኬላን ለማየት ቀጠሮ እንዳትይዙ።"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ


https://fb.watch/ksjmDBaWS7/
1.9K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 09:03:10
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከ #ዋልታ_ቴቪ ግንቦት 3/2015https://fb.watch/ksfEThUdBd/
2.2K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:02:53 “ቃል፣ ተግባር፣ ትውልድ” - የመጽሐፍ አውደ ርዕይ (ክፍል-3)
https://fb.watch/krxYytfQgX/
3.6K views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ