Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.24K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-29 10:26:10
ከያቤሎ እስከ ሞያሌ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለጸ

ሚያዝያ 21/2015 (ዋልታ) ከያቤሎ ወደ ቡኩሉ ጉማ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ መሰረቱ በጎርፍ ተሸርሽሮ በመውደቁ የተነሳ ከለሊት 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የደቡብ ሪጅን 1 ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር ምትኩ ንጉሴ እንዳስታወቁት በአካባቢው ከረጅም ጊዜ በኋላ እየጣለ ያለው ዝናብ ሦስት የብረት ምሰሶዎች መሰረት እንዲሸረሸር አድርጓል፡፡

ይህን ተከትሎ ለሁለቱ የብረት ምሰሶዎች የአፈር መሸርሸር መከላከያ ግንብ የተሰራ ሲሆን የአንደኛው ምሰሶ የአፈር መሸርሸር መከላከያ ግንብ ግንባታ እየጣለ በነበረው ዝናብ ምክንያት አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ትላንት ለሊት 8፡00 ላይ ከያቤሎ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ አንደኛው ምሰሶ በመውደቁ ወደ ቡኩሉ ጉማ ማከፋፈያ ጣቢያ ይሄድ የነበረው ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ገልፀዋል፡፡

በዚህ የተነሳ ቡኩሉ ጉማ፣ ሜጋ እና ሞያሌ ከተሞችን ጨምሮ በኬንያ ድንበር አካባቢ ያሉ ከተሞችና መንደሮች ኃይል ተቋርጧል ብለዋል፡፡

የኃይል መቋረጡን በጊዜያዊነት የእንጨት ምሰሶዎችን በመትከል ለማስተካከል ጥረት መጀመሩን የገለፁት ዳይሬክተሩ አካባቢው ሌላ አማራጭ መስመር ስለሌለው ችግሩ እስኪቀረፍ የአካባቢው ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል፡፡
3.5K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:15:19
ዋና ፀሐፊው በሱዳን አለመረጋጋት ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መከሩ

ሚያዝያ 21/2015 (ዋልታ) የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በሱዳን አለመረጋጋት ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መክረዋል።

ዋና ፀሐፊው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት ከእንግሊዝ፤ ካናዳ እና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በስልክ ተነጋግረዋል።

በውይይቱም፣ ኢጋድ ሁኔታውን በአንክሮ እየተከታተለው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን እያደገ ካለው የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት አንፃር ኢጋድ ያለውን ስጋትም አጋርቷል ብለዋል።

ዋና ፀሐፊው አክለውም፣ በሱዳን አፋጣኝ የተኩስ ማቆም፣ ያልተደናቀፈ ሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት እና የሲቪል ማህበረሰቡ ደህንነት ማስጠበቅ ላይ በጋራ ለመስራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ብለዋል።
3.5K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:08:36
አሁን የደረሰን መረጃ!

በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ


ሚያዝያ 20/2015 (ዋልታ) በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለዋልታ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ለአማራ ህዝብ እንታገላለን በሚል በውስጥም በውጭም በመቀናጀት የራሳቸውን ህቡዕ አደረጃጀት የፈጠሩ አካላት ከመሰል ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የህዝቡን የቁርጥ ቀን ልጆች መልሰው እየበሉ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች በትናንትናው ዕለትም የአማራ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ሓላፊ እና የክልሉ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን ግርማ የሺጥላን በመግደል አስነዋሪ ድርጊታቸውን አስመስክረዋል፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0322st2meE4YqMgKFudVteUM7GK33VKJGwZff9t6qBiqHRsswnAA3HoMAK98wY5Avjl&id=100064690148931&mibextid=Nif5oz
5.0K viewsedited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:16:37
#ምሳሌ!
የትውልዱ ሽልማት

(በሳሙኤል ሙሉጌታ)

እግር ኳስን ከጉልበታሞች ትግል ወደ አእምሯዊ የጥበብ ጨዋታ ከፍ ካደረጉት ተጫዋቾች መካከል ስሙ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ እሱ በሜዳ ውስጥ ካለ አንድ የእግር ኳስ ተአምር ይኖራል፡፡ ኳስ በግራ እግሩ ታግዛ አንዳች አስማት ትሰራለች። ጥበበኛው ተጫዋች እግሩ ስር የገባችውን ኳስ የሚገባትን የክብር ካባ አልብሶ ወዲህ ወዲያ እያደረገ ሲያንሸራሽራት ለተመለከተ አብሮት የሚጫወት ሰው ያለ አይመስልም፡፡ እሱ ዘንድ ጓንቱን የማይሰጥ በረኛ፣ ከኋላው የማይሮጥ ተከላካይ፣ እጁን በአፉ የማይጭን ደጋፊ የለም፡፡ እሱ ለእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪያን የተሰጠ የዚህ ትውልድ ታላቅ ሽልማት ነው፡፡ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ!

ዘመን በተሻገረው ስፖርት ውስጥ የራሱን ህያው ታሪክ በተመልካች ልብ ውስጥ ይፅፍ ዘንድ እ.ኤ.አ በ1987 በአርጀንቲናዋ ሮዛሪዮ ሳንታፌ ከተማ ተወለደ። ገና በልጅነት እድሜውና ባልጠነከረ አጥንቱ አጥንትን የሚያለመልም ጥበብ በጎዳናዎች ላይ ማሳየት የጀመረው ሜሲ ለግዙፎች ብቻ የተሰጠ በሚመስለው ስፖርት ላይ አዲስ አብዮት ፈጠረ፡፡ በእድሜም በቁመትም ከሚበልጡት ተጫዋቾች ጋር ቢጫወትም በሚያሳያቸው እግር ኳሳዊ ውሳኔዎችና ድሪብሎች ከሁሉም በላይ ያለ እድሜው ገዘፈ።

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02rCh6QeAu3WEjp67qKSB2QASrVGTNZW9xzA2ewNPJBipqTmTAMbbZJZNSYAJag44Jl
4.9K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:01:40
ዋልታ ምሽት ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ሚያዝያ 20/2015

https://www.facebook.com/watch/?v=755220992650606
4.1K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:55:43
በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ሰላምን ለማፅናት በትኩረት እንሠራለን - የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ከንቲባዎች

ሚያዝያ 20/2015 (ዋልታ) በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ሰላምን ለማፅናት በትብብር እና በልዩ ትኩረት እንሠራለን ሲሉ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ከንቲባዎች ተናገሩ።

የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በትግራይ ክልል ለሚካሄዱ የመልሶ ማቋቋም እና የልማት ሥራዎች ሕዝቡን በማስተባበር ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍም አድርገዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሰ መስዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የፌዴራል መንግሥት እና የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ልዑካን በትግራይ ክልል አብሮነትን ማጠናከርን እና ሰላምን ማፅናትን ያለመ ጉብኝት አድርገዋል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0Ldz52YLYJcN4jCiUAfiHDQn1RHYLRBTPvr43VBNfpWyZ9fLye7CLY9kgtV6ZH8opl
4.1K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:12:42
የግርማ የሺጥላ የአስከሬን ሽኝት እሑድ በአዲስ አበባ እንደሚከናወን የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ገለጸ

ሚያዝያ 20/2015 (ዋልታ) የግርማ የሺጥላ የአስከሬን ሽኝት እሑድ ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚከናወን የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ገለጸ።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በወላጆቻቸው ፍላጎት እና ጥያቄ መሠረት በተወለዱበት ሰሜን ሸዋ ዞን ማሀል ሜዳ እንደሚፈጸም ተገልጿል።

የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በነበሩት ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመው ድንገተኛ ግድያ እንዳሳዘነው በመግለጫው ገልጾ ድርጊቱ የሚወገዝ ነው ብሏል።

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0EgfQ2wWGe4e7MbLPpzXVFGN7BRigZ6JduHk3RhcsECHneQUrVqsYs2x1qNsVcS1zl
4.1K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 17:17:15

4.0K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 16:13:34
ድርጅቱ ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ሚያዝያ 20/2015 (ዋልታ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተለይ አገልግሎትን ከማስፋትና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ በልዩ ትኩረት መሰራቱን አንስተዋል።

በዚህም አጠቃላይ የድርጅቱን የኦፕሬሽን አገልግሎት መጠን 4 ሚሊየን 85 ሺሕ 765 ቶን ለማድረስ ታቅዶ 4 ሚሊየን 131 ሺሕ 929 ቶን በማድረስ ከእቅድ በላይ መፈፀሙን ገልጸዋል።

በጭነት ማጓጓዝ አገልግሎት የድርጅቱንና የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም 2 ሚሊየን 885 ሺሕ በላይ ቶን በማጓጓዝ ከእቅድ በላይ ተከናውኗል ብለዋል።

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድርጅት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በተጠቀሰው ወራት በጭነት አስተላላፊነት አገልግሎት በኩል በመልቲሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት 66 ሺሕ 194 ኮንቴይነር ለማጓጓዝ ታቅዶ 70 ሺሕ 742 ኮንቴይነር በማጓጓዝ የተሳካ ስራ መከናወኑን ጠቁመዋል።

ለሀገር ልማት በተለይም ለግብርና ስራዎች ግብዓትን በማስገባት ረገድ የላቀ አፈፃፀም መታየቱንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

በቀጣይም አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ የታገዘና ዓለም አቀፍ ተደራሽነትን ለማስፋት ተቋሙ ግዙፍና ዘመናዊ የዳታ ማዕከል እያስገነባ እንደሆነ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
4.3K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 14:29:03
ልዑኩ በትግራይ ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት የተጎዱ ፋብሪካዎችን ጎበኘ
ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ፋብሪካዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የልዑክ ቡድኑ በጉብኝቱ ሰማያታ የእምነበረድ ፋብሪካ እና ሸባ የቆዳ ፋብሪካን ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ፋብሪካዎቹ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው በፋብሪካዎቹ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ዜጎች ለችግር መጋለጣቸውም ነው የተገለጸው።
የክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች በበኩላቸው፣ ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።
159 views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ