Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.24K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-26 18:33:50
የአንድነት ፓርክ አሁናዊ ገፅታ ፎቶ በዋልታ
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0Lm5ic1Ub8bwn2Cr2d7U5699H3j9k5fPub7ko9uLXwJ4hQQTpZrBswHCRQjSLH7g6l
3.0K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 17:50:15

3.2K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:25:10
ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በኡጋንዳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኡጋንዳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል።

በአራት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአራተኛ ሃገር ጉብኝታቸውን በኡጋንዳ ማድረግ ጀምረዋል።

ሚኒስትሩ ኡጋንዳ ሲደርሱ የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሄነሪ ኦኬሎ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኡጋንዳ ቆይታቸውም ከሃገሪቱ ኘሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሰራዊት ያበረከቱ ሃገራት ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
3.6K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:18:49
ፍርድ ቤቱ ህገ መግስቱን በኃይል ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው የተጠረጠሩት የነ ፕሮፌሰር ሲሳይ አጉቾን መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ረ/ ፕሮፌሰር ሲሳይን ጨምሮ በአምስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሰራውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ከነገ በስቲያ ለሚያዚያ 20 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተጠርጣሪ በሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቾው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያብን ፣ አማሃ ዳኘው፣ ሰለሞን ልመንህ እና ሄኖክ አዲስን በሚመለከት መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው የስምንት ቀን ውስጥ የሰራውን የምርመራ ስራ በዝርዝር ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አቅርቧል።

በዚህም ተጠርጣሪዎች ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ በአማራ ክልል ሁከትና ብጥብጥ አመፅ በማስነሳት በንብረትና በሰው ላይ በደረሰ ጉዳት ተሳትፎ እንዳላቸው የሚገልፁ በጥናት የተዘጋጀ የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘቱን አብራርቷል።

ለበጎ አድራጎት እርዳታ በሚል ሰበብ በግልፅ አባላት ተመልምሎ አጣዬ አካባቢ ስልጠና ሲሰጡ እንደነበር የተገኘው ማስረጃ በግልፅ ያሳያል በማለት ለችሎቱ አስረድቷል።

የተለያዩ የገንዘብ ዝውውሮችን ለማጣራት ለባንኮች ደብዳቤ መጠየቁን እና በተጠርጣሪዎች እጅ የተገኘ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን፣ የተያዙ ቦንቦችንና የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም ሰለሞን ልመንህ እጅ የተገኙ የበርካታ የወጣቶች መታወቂያዎችና ሰነዶችን ህጋዊነት የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

እንደ አጠቃላይ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር የሚገናኝ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን መሰብሰቡን አስረድቷል።
3.3K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 14:28:13
የአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ ስረዓተ ቀብር ተፈፀመ

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) የአንጋፋው የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ አቀንቃኝ ዘሪሁን ወዳጆ የቀብር ሰነ-ስረዓት በመንበር ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ዘመድ ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈፀሟል።

አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ በ1949 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ለ48 ዓመታት በአፋን ኦሮሞ የተለያዩ ይዘት ያላቸው ሙዚቃዎች በማቀንቀን ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደረግ ቆይቷል።

አርቲስቱ ባጋጠመው ህመም ምክንያት በህንድ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከቀናት በፊት ህይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በፌናን ንጉሴ
3.7K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:59:29
20ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው በመካከለኛ ዘመን (2016 - 2020) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የተወያየው በመካከለኛ ዘመን /2016-2020/ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ሲሆን ማዕቀፉ በዋናነት የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና ታሳቢዎች ጋር ተጣጥሞ የተዘጋጀ መሆኑን፣ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየትና ለማመላከት የሚያገለግል የበጀት ዕቅድ መሳሪያ ሆኖ የ2016 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትን ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ የክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያ እና የፊሲካል ጉድለት መጠንን የሚያመላክት ሆኖ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ አረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ማዕቀፉ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት የተጋረጠውን የፊሲካል ስጋት ለመቅረፍ እና የፊሲካል ጤናማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑን በማመን፣ የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲመጣጠን ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ግምት ውስጥ በማስገባት ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
3.8K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 19:11:19 ዋልታ ምሽት ሚያዝያ 16/2015 በቀጥታ
https://fb.watch/k6oWZ35Soq/
1.6K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 17:00:46

2.4K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:58:15
ሀገሬ

የጮቄ ተራራ - የምሥራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ

በሠራዊት ሸሎ

ሚያዝያ 16/2015 (ዋልታ) የጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ መገኛው በምስራቅና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ ነው። ተራራው ልዩ ውበትና ተፈጥሯዊ ፀጋ የተላበሰ ድንቅ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም መስህብና መዳረሻ ቦታ ነው።

ይህንን ድንቅና ውብ የተፈጥሮ ስጦታ ባለቤት የሆነውን የጮቄ ተራራ ተፋሰስ ለመጎብኘት ከርዕሰ መድናዋ አዲስ አበባ 338 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይጠበቃል።

ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር ደግሞ 325 ኪሎ ሜትር ርቀት ለይ የሚገኝ ሲሆን ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ በስተምስራቅ አቅጣጫ 38 ኪሎ ሜትር ተጉዘው ያገኙታል።

ጮቄ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነ እረግረጋማ ሰለነበረና ሲረግጡት ጮቅ ጮቅ ስለሚል ከዚሁ መነሻ ስያሜውን እንዳገኘም ይነገራል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid031Z8rBt6sDb4nTr9fTmsRPH8EfsSpD5uUAqk35SDwa3hKVhDyuNNRcwaqZyjQ2LbLl
2.7K viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:35:20
ኮርፖሬሽኑ ነባር የጋራ መኖሪያ ቤት ስራዎችን እስከ ሰኔ 30 ለማስረከብ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

ሚያዝያ 16/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ነባር የጋራ መኖሪያ ቤት ስራዎችን እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም አጠናቆ ለማስረከብ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት ቤቶቹን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን በ13ኛ እና 14ኛ ዙር የቤት እጣ የወጣባቸው ቤቶች ላይ ያልተጠናቀቁ ቤቶችን አጠናቆ እስከ ሰኔ 30 ለማስረከብ ማቀዱን አመላክተዋል።

በቤቶቹ ላይ ያልተጠናቀቁ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውንና ቀሪ ስራውን ለማጠናቀቅ የተቀናጀ አሳታፊ የፕሮጀክት መዝጋት እቅድ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቶቹን የመዝጋት ስራው የነዋሪዎችን ቅሬታ መሰረት ያደረገ ሲሆን መብራትን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በ30 ሳይቶች ላይ እያከናወነ እንደሚገኝም ኮርፖሬሽኑ ጠቁሟል።

ከተማ አስተዳድሩም ያልተጠናቀቁ ቤቶችን አጠናቆ ለመጨረስ 21 ቢሊየን ብር ወጪ ማድረጉ ተመላክቷል።

ከተማ አስተዳደሩ የቤት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የቤቶች ልማት ስራ እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል።

በብሩክታይት አፈሩ
2.6K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ