Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.37K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2023-04-23 09:48:25
አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ሚያዝያ 15/2015 (ዋልታ) ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምፃዊው ለረዥም ጊዜ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በህንድ አገር ላይ እያለ እንዳረፈ ነው የተገለጸው።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለአርቲስቱ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው አርቲስቱ በሞት ቢለየንም ከትውልድ ትውልድ ተሻጋሪ ስራዎቹ ሲታወሱ ይኖራሉ ብለዋል።

አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በሙዚቃ ስራዎቹ ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ታላቅ አርቲስት ነበር ብለዋል።
2.5K viewsedited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 20:10:39
“ምክንያታዊ ወጣት ለአዲስ አበባ ብልጽግና!”

https://fb.watch/k3PCZhOsJa/
1.8K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 20:07:28
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባለሙያዎቹ ከተማዋ እየገነባቻቸው ካሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፊሎቹን መጎብነታቸውን ገልጸው በፈተና ውስጥም ቢሆን ሕዝብን የሚጠቅሙ ሥራዎች መሠራታቸውን አድንቀዋል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በሠራቸው ሥራዎች ልክ ለሕዝብ ግንዛቤ መፍጠር አለመቻሉን የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ መናገራቸውንም ጠቁመዋል።

ባለሙያዎቹ ያሉባቸውን ጥያቄዎች እና ድጋፍ የሚሹባቸውን ጉዳዮች መጠቆማቸውን እና አንዳንዶቹን የከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር እንደሚፈታቸው ከመግባባት ላይ መደረሱንም አስታውቀዋል።

ኪነ-ጥበብ ትውልድ የሚያንጽ አብሮ የመኖር ዕሴቶቻችንን የሚገነባ በመሆኑ ከለውጡ ወዲህ በርካታ አንፊ ቴአትር ማሳያ ቦታዎችን ገንብተናል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዳዲስ ቴአትር ቤቶች ግንባታም መጀመሩን እና ነባሮቹን የማደስ እና አቅማቸውን የማጎልበት ሥራ በመሥራት ላይ እንደሆነም ገልጸዋል።

ቴአትር ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር ታሪካዊ ማንነታቸው ተጠብቆ በአሠራር እና በአደረጃጀት ባለሙያው ነጻነቱ ተከብሮ በሙያው እንዲጠቀም ማድረግ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን በመወሰን ለባለሙያው እና ለጥበብ የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
1.9K viewsedited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:50:34

1.7K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:49:27

1.7K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:19:29
እንዲያውቁት!

“ምክንያታዊ ወጣት ለአዲስ አበባ ብልጽግና”

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከ16 ሺሕ ወጣቶች ጋር ያደረጉትን ውይይት ዛሬ ምሽት ከዜና በኋላ በዋልታ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች የምናስተላልፍ መሆኑን እየገለጽን እንዲትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
1.8K views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:00:21
የማታ 1፡00 ዜና ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ሚያዝያ 14/2015

https://fb.watch/k3Lw1RDgXL/
1.9K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 18:44:11
የአብሮነት እሴት በማጠናከር ወንድማማችነትን የሚያጸና ቀጣይነት ያለው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሥራ እንሰራለን - የክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) የዜጎችን የአንድነትና የአብሮነት እሴት በማጠናከር ወንድማማችነትን የሚያጸና ቀጣይነት ያለው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሥራ እንሰራለን ሲሉ የኦሮሚያና የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች ገለጹ።

የኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛና የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ክልሎቹ የሕዝቦችን አንድነት ማስቀጠል የሚያስችሉ የሕዝብ ግንኙት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ እንደገለጹት ሚዲያ ለሕዝብ አንድነትና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጎልበት አይተኬ ሚና አለው።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02Rr4Av1vC2dd7YRhnm24LM7xj7LAqX2ouL8bLe6HPRvpgiGjfcmdpym8XNcE8pYkwl
1.9K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:46:09
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1ለ0 አሸነፈ

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) የ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርኃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 1 ለ 0 አሸነፈ።

በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል በ71ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ቶጎዋዊው አጥቂ እስማኤል ኦሮ-አጎሮ ነው፡፡

እስማኤል ኦሮ-አጎሮ በሊጉ 19ኛ ግቡን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን ወደ 45 ከፍ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ባህርዳር ከነማ በ3 ነጥብ በልጦ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

ፋሲል ከነማ በ27 ነጥብ በነበረበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ20ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርኃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ በድሬዳዋ ከተማና ሀዋሳ ከተማ መካከል ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
2.2K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:31:35
በበይነ መረብ የሚሸጡ የመዋቢያ ምርቶች ጥራት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) በኢትዮጵያ በበይነ መረብ አማካኝነት የሚሸጡ የመዋቢያ ምርቶችና መድኃኒቶች ጥራት እና ደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የቁጥጥር ቡድን መሪ ሳሙኤል ማሪ ከዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የሚሸጡ ምርቶች ጥራት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጸው የምርቶቹ ሽያጭም ህጋዊ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

የመድኃኒቱም ሆነ ኮስሞቲክስ ደህንነት፣ ፈዋሽነት ወይም ውጤታማነት ላይ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል የኢንተርኔት ሽያጭ እንደሚከለከልና ከህግ ማዕቀፍ አኳያ ተቀባይነት እንደሌላቸው አመላክተዋል፡፡
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid023y2xAFY8DMpWH17ehZMtbTZvSHFoYYE2JxsiJt7NkSGU2Mq8ppRJybyWV6sDqnthl
2.3K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ