Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.03K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 349

2022-05-12 17:33:57
በደቡብ ክልል በበልግ እርሻ 400 ሺሕ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል እየተካሄደ ባለው የበልግ እርሻ እንቅስቃሴ እሰካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ 400 ሺሕ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዳንኤል ዳምጠው እንደገለጹት በዘር የተሸፈነው መሬት በክልሉ በ2014/2015 ምርት ዘመን በተለያየ ሰብል ለማልማት ከታቀደው አንድ ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ ነው።

የዘንድሮ በልግ ዘናብ ዘግይቶ በመግባቱና የዝናብ መቆራረጥ ችግር በማጋጠሙ ምክንያት በአብዛኞቹ በልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች የበልግ እርሻው ዘግይቶ መጀመሩን ተናግረዋል።

የዝናብ ሥርጭቱ መሻሻል እያሳየ ከመጣ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

በበልግ ልማቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች፣ ወጣቶችና ሴቶች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የበልግ ልማቱን ዕቅድ ለማሳካት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በክልሉ የሚመረቱት ዋና ዋና ሰብሎች ለሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለውጭ ገበያ ካላቸው አገልግሎት አንጻር መለየታቸውን አስረድተዋል። https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/photos/a.489214534492666/5419191571494913/?type=3&app=fbl
2.9K viewsedited  14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:31:59
ዳኝነት ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያሰችል ስትራቴጂ ይፋ አደረገ።

የስትራቴጂው ፋይዳ እና በቀጣይ አተገባበሩ ዙሪያ ላይ ከዳኞችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ በፍትህ አሰጣጥ ሂደት የትውውቅ አሰራር፣ ጉቦና የመሳሰሉት ብልሹ አሰራሮች ፈተና እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

የዳኞች አገልግሎት አሰጣጥ ከሙስና ተግባር የፀዳ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው አንዳንድ ዳኞች፣ የጉባኤ ተሿሚዎችና የፍርድ ቤት ሰራተኞች በሙስና ፍትሕ እንዲዛባ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዳኝነት ሥርዓቱ ውስጥ የሚፈጸም ሙስና በተገልጋዩ እና ፍትሕ ፈላጊው ላይ ተስፋ እያሳጣ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ፕሬዝዳንቷ የህግ ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ በማውጣት፣ የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ በማጽደቅ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ፍትሃዊና ጥራት ያለው እንዲሆን ለማስቻል ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ ዳኞች የዳኝነት ሙያ ከፍተኛ ሥነ ምግባርን መላበስ እና ለማኅበረሰቡም ተምሳሌት መሆንን የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህ ልንዘጋጅ ይገባል ብለዋል።
2.4K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:22:12
ከውጭ የሚገቡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከ114 ሚሊየን ዶላር አዳነ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በላፉት ዘጠኝ ወራት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከ114 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳኑን አስታውቋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዱካን ደበበ የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ የአፈፃፀም አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኮርፖሬሽኑ በ9 ወር አፈፃፀም 152 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ለውጭ ገበያ መላኩንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ያካሄደችው የኅልውና ዘመቻ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ፈተና እንደነበር ገልጸው በተለይም ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ፓርኮች ጫና ውስጥ እንደነበሩ አመላክተዋል።

በተጨማሪም የካሳና የድንበር ጉዳይ ፈተና እንደሆነበት እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ድጋፍ ማነስ እንደተስተዋለበት ተነስቷል።

ኮርፖሬሽኑ በታሪኩ የመጀመሪያ ያለውን 791 ሚሊየን ብር ከሼዶች ኪራይ እንዲሁም ከለሙ መሬቶች ትርፍ ማግኘቱም በመግለጫው ተመላክቷል።

በላፉት ዘጠኝ ወራት ከ76 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩም ተገልጿል።

በዙፋን አምባቸው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
2.3K viewsedited  13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 15:58:42
“ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሊካሄድ ነው

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ)“ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል ሃሳብ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሊካሄድ ነው፡፡

ኬሮድ ኢትዮጵያ የሚያዘጋጀው ሁለተኛ ዙር የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው።

የሩጫው ዋነኛ ዓላማው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እና አትሌቶችን ልምድ እንዲያገኙ በማሰብ ውድድር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ውድድሩ ሰኔ 19 መነሻውን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መዳረሻውን ወልቂጤ ከተማ በማድረግ ይከናወናልም ነው የተባለው፡፡

በሚኪያስ ምትኩ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
2.2K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 15:36:18
ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2013 ዓ.ም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ በመዲናዋ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ከ18 ሺሕ እስከ 20 ሺሕ ብር ጥሬ ገንዘብ ነው።

በተጨማሪም ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚጠቀሙበት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ ውጤታማ ሆነው ከዩኒቨርሲቲ እስከሚወጡ ድረስ ቢሮው ድጋፉን እንደሚቀጥል ታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ገነት ቅጣው ተማሪዎቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ተማሪዎች መሸለምና መደገፍ ሞራላቸውን ለመገንባትና ለሌሎች ተማሪዎችም አርአያ እንዲሆኑ ያደርጋልም ነው ያሉት።

እንደኢዜአ ዘገባ ተሸላሚ ተማሪዎች በበኩላቸው ድጋፉ የበለጠ ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡


ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
2.3K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 15:20:40
በሚያዝያ ወር 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በሚያዝያ ወር ብቻ 33 ቢሊየን 927 ሚሊየን 965 ሺሕ 151 ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በሚያዝያ ወር 35 ቢሊየን 753 ሚሊየን 276 ሺሕ 983 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 33 ቢሊየን 927 ሚሊየን 965 ሺሕ 151 ብር ገቢ እንደተሰበሰበና ይህም የዕቅዱ 95 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ገቢው የተገኘው ከሀገር ውስጥ ታክስና ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ሲሆን አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ወር ጋር ሲነፃፀር የ31 ነጥብ 19 በመቶ ዕድገት እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ውጤቱ መመዝገብ የቻለው የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በትብብርና በትጋት በመስራታቸው መሆኑን ጠቅሰው በተገኘው ስኬት የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

ገቢያቸውን በወቅቱ አሳውቀው ግብር ለከፈሉ የፌዴራል ግብር ከፋዮች እንዲሁም ለአጋር አካላትና ሕዝቡ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
2.2K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ