Get Mystery Box with random crypto!

በሚያዝያ ወር 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የገቢ | AddisWalta - AW

በሚያዝያ ወር 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በሚያዝያ ወር ብቻ 33 ቢሊየን 927 ሚሊየን 965 ሺሕ 151 ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በሚያዝያ ወር 35 ቢሊየን 753 ሚሊየን 276 ሺሕ 983 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 33 ቢሊየን 927 ሚሊየን 965 ሺሕ 151 ብር ገቢ እንደተሰበሰበና ይህም የዕቅዱ 95 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ገቢው የተገኘው ከሀገር ውስጥ ታክስና ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ሲሆን አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ወር ጋር ሲነፃፀር የ31 ነጥብ 19 በመቶ ዕድገት እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ውጤቱ መመዝገብ የቻለው የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በትብብርና በትጋት በመስራታቸው መሆኑን ጠቅሰው በተገኘው ስኬት የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

ገቢያቸውን በወቅቱ አሳውቀው ግብር ለከፈሉ የፌዴራል ግብር ከፋዮች እንዲሁም ለአጋር አካላትና ሕዝቡ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW