Get Mystery Box with random crypto!

ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የአ | AddisWalta - AW

ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2013 ዓ.ም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ በመዲናዋ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ከ18 ሺሕ እስከ 20 ሺሕ ብር ጥሬ ገንዘብ ነው።

በተጨማሪም ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚጠቀሙበት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ ውጤታማ ሆነው ከዩኒቨርሲቲ እስከሚወጡ ድረስ ቢሮው ድጋፉን እንደሚቀጥል ታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ገነት ቅጣው ተማሪዎቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ተማሪዎች መሸለምና መደገፍ ሞራላቸውን ለመገንባትና ለሌሎች ተማሪዎችም አርአያ እንዲሆኑ ያደርጋልም ነው ያሉት።

እንደኢዜአ ዘገባ ተሸላሚ ተማሪዎች በበኩላቸው ድጋፉ የበለጠ ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡


ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW