Get Mystery Box with random crypto!

“ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሊካሄድ ነው ግንቦት 4/2014 | AddisWalta - AW

“ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሊካሄድ ነው

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ)“ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል ሃሳብ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሊካሄድ ነው፡፡

ኬሮድ ኢትዮጵያ የሚያዘጋጀው ሁለተኛ ዙር የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው።

የሩጫው ዋነኛ ዓላማው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እና አትሌቶችን ልምድ እንዲያገኙ በማሰብ ውድድር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ውድድሩ ሰኔ 19 መነሻውን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መዳረሻውን ወልቂጤ ከተማ በማድረግ ይከናወናልም ነው የተባለው፡፡

በሚኪያስ ምትኩ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW