Get Mystery Box with random crypto!

ከውጭ የሚገቡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከ114 ሚሊየን ዶላር አዳነ ግንቦት 4/2014 ( | AddisWalta - AW

ከውጭ የሚገቡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከ114 ሚሊየን ዶላር አዳነ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በላፉት ዘጠኝ ወራት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከ114 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳኑን አስታውቋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዱካን ደበበ የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ የአፈፃፀም አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኮርፖሬሽኑ በ9 ወር አፈፃፀም 152 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ለውጭ ገበያ መላኩንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ያካሄደችው የኅልውና ዘመቻ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ፈተና እንደነበር ገልጸው በተለይም ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ፓርኮች ጫና ውስጥ እንደነበሩ አመላክተዋል።

በተጨማሪም የካሳና የድንበር ጉዳይ ፈተና እንደሆነበት እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ድጋፍ ማነስ እንደተስተዋለበት ተነስቷል።

ኮርፖሬሽኑ በታሪኩ የመጀመሪያ ያለውን 791 ሚሊየን ብር ከሼዶች ኪራይ እንዲሁም ከለሙ መሬቶች ትርፍ ማግኘቱም በመግለጫው ተመላክቷል።

በላፉት ዘጠኝ ወራት ከ76 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩም ተገልጿል።

በዙፋን አምባቸው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW