Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.24K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 342

2022-05-15 11:12:13
የሁለቱ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ በእንጅባራ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ በእንጅባራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

“የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለዘላቂ ሠላም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው መድረኩ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ ዓለምነሽ ይባስ ተገኝተዋል፡፡

በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይል እና የተለያዩ የጸጥታ ተቋማት አዛዦች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ መድረኩ የሁለቱን ክልል ሕዝብ የቆየ ትስስር እና አብሮነት የሚያንጸባርቁ የአማራ፣ አገው፣ የሽናሻ እና ጉሙዝ ሕዝቦች የተለያዩ የጥበብ ሥራዎች እየቀረቡ ነው፡፡

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ በሁለቱ ክልሎች መካከል መልካም ግንኙነትን በመገንባት በጋራ ለመሥራት፣ ለማደግ እና በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያግዛል መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.6K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 10:56:18
የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ፡፡

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለአንድ ቀን በሚያካሂደው ስብሰባ የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጉባዔ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ላይ ከሊጉ አባላት ጋር በየደረጃው የተደረገውን ውይይት የአፈፃፀም ሁኔታ እንደሚገመግም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም “ምግቤን ከጓሮዬ፤ ጤናዬን ከምግቤ” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የከተማ ግብርና ንቅናቄ የአፈፃፀም ደረጃ በየክልሎችና በሁለቱ ከተሞች የሊጉ አመራሮች ሪፖርት ቀርቦለት እንደሚወያይ ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.5K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 10:34:20
በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ የተመራ ልዑክ የወንጪ ልማት ፕሮጀክትን እየጎበኘ ነው

ግንቦት7/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የመከላከያ ሚኒስትር እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን የወንጪ ልማት ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው።

ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

ወደ ሃይቁ መዳረሻ የሚወስዱ 32 ኪሎሜትር ርዝመት ያላቸው ሦስት መንገዶች እየተገነቡ ሲሆን አፈፃፀማቸውም 58 በመቶ መድረሱ ተነግሯል።

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ - ደንዲ ፕሮጀክት የሀገሪቱን የኢኮ ቱሪዝም ልማት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግም እምነት ተጥሎበታል።

በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም የግንባታ ሥራው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጀመሩ የሚታወስ ነው።


አሳየናቸው ክፍሌ (ከወንጪ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.6K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 09:54:09
የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የከተማ ግብርና ሥራዎችን ጎበኙ

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ብሔራዊ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ የከተማ ግብርና ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

ጉብኝቱ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ የሚመራ ሲሆን መነሻውን ያደረገው እድሳቱ ተጠናቅቆ አገልግሎተ እየሰጠ የሚገኘውን የማዘጋጃ ቤት ህንጻ ነው።

ምግባችን ከደጃችን በሚል መሪ ሀሳብ የከተማ ግብርና ለማጠናከር ውጤታማ ሥራ በተከናነባቸው በየካ፣ በለሚኩራና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች በግለሰብ፣ በአርሶአደርና በመንግሥት ተቋማት የለሙ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ሥራዎች በመጎብኘት ላይ መሆናቸውን ኤኤምኤን ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
404 views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 09:43:55
በደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው የደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 127 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ደንዲ ሃይቅ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጣልያኑ "ዊ ቢውልድ" ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔትሮ ሳሊኒ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የወንጪ ደንዲ ኢኮ-ቱሪዝም ፕሮጀክት አስተባባሪና የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

የገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ዋና ዓላማ በቅድሚያ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቀሚነት ማረጋግጥ ስመሆኑም ተጠቁሟል።

በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም የግንባታ ሥራው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መጀመሩ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
524 views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 09:24:10
የገርጂ ዘመናዊ መኖሪያ መንደር በተለያዩ አካላት ተጎበኘ

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው እና የአልሙኒየም ፎርምወርክ የግንባታ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደርን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) እና ባለሀብቱ ነጅብ አባቢያ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ኮርፖሬሽኑ በግንባታ ቴክኖሎጂ እና አስተዳደር እያሳየ ባለው የላቀ አፈጻጸም የመኖሪያ መንደሩን በ18 ወራት ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ መቃረቡ ተገልጿል።

ይህም በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ጥራትን፣ ቅልጥፍና እንዲሁም ዘመናዊነትን አጣምሮ እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ መንደር በአጭር ጊዜ መገንባት መቻሉ ኮርፖሬሽኑ ብቃት ባላቸው እና የፕሮጀክት አስተዳደር እውቀት ባካበቱ አመራሮች እየተመራ መሆኑን ማሳያ መሆኑን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

የመኖሪያ መንደሩ የተገነባበት እና የተመራበት አጠቃላይ ሂደቱ ለዘርፉ ምሁራን፣ አልሚ ባለሃብቶች እና ተማሪዎች በግንባታ እንዱስትሪው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ለሚያደርጉት ሳይንሳዊ ጥረት ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ፕሮጀክት ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

የመኖሪያ መንደሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጭ አገራት ዜጎች እና በተለያዩ አካላት እየተጎበኝ ሲሆን በቀጣይ ከፕሮጀክቱ ልምድ ተወስዶ እንደሀገር በሰፋፊ የቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታም ሰፊ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
666 views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 21:52:35
የተለያዩ ኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) ባሳለፍነው ሳምንት 131 ሚሊየን 481 ሺሕ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል 40 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 90 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዛቸውን ነው የገለጸው፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሲሆን በቅደም ተከተላቸው 14 ነጥብ 7 ሚሊየን፣ 9 ነጥብ 7 ሚሊየን እና 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻላቸው ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ኅብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 15 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ሥራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የክልልና የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ሕዝብ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
1.4K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 21:27:59
በኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን እና የምህድስና ዘርፍን ማሳደግ የኅልውና ጉዳይ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን እና የምህድስና ዘርፍን ማሳደግ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የኅልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የክብር ዶክትሬት በሰጠበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር በዛሬው እለት የምናከብራቸው እና እውቅና የምንሰጣቸው ሁለት ሰዎች አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የምህድስና ዘርፎች ባደረጉት ጥረት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በጎ ተፅዕኖ በመፍጠራቸው ነው ብለዋል።

የክብር ዶክትሬት ያገኙት አኪንውሚ አዴሲና እና ፔትሮ ሳሊኒ በአኅጉሪቱ በአርዓያነት እንደሚጠቀሱ እምነቴ ነው ሲሉም አክለዋል።

የአረንጓዴ ኢኮኖሚን እና የምህንድስና መስኮች በዓለም ዙሪያ እጅግ የተከበሩ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለብዙ ሀገራትም የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ በማለት ገልፀዋል።

በኢትዮጵያም የአረንጓዴ ኢኮኖሚን እና የምህድስና ዘርፍን ማሳደግ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የኅልውና ጉዳይ ነው ብለዋል።

የምግብ ዋስትናን እና ዘላቂ ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ዘርፎች ስለመሆናቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአረንጓዴ ኢኮኖሚና ምህንድስና በአፍሪካ ቀስ በቀስ እያደገ መሆኑን አንስተዋል።

በአኅጉሪቱ የሕዝብ መሰረተ-ልማት እያደገ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኮኖሚያዊ እድገቱም በቀላሉ ሊወሰድ አይችልም ብለዋል።

በደረሰ አማረ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.4K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 20:34:30
ጠ/ሚ ዐቢይ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የክብር ዶክተሬት ላገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው "እውነተኛ የአፍሪካ ልጆች ዶ/ር አኪኒዩሚ አዴሲና እና ዶ/ር ፒዬትሮ ሳሊኒ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በማግኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።

የተቀበላችሁት በኢኮኖሚክስ እና በምሕንድስናው መስክ ላበረከታችሁት ታላቅ አስተዋጽዖ የሚገባችሁ ዕውቅና ነው ሲሉም አክለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ በዛሬው ዕለት የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው መርኃ ግብር ለተሸላሚቹ የክብር ዶክትሬቱን አበርክተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
420 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 19:51:57
የመገናኛ ብዙኃን፣ መረጃ እና ምርምር ቋት ሥራ ጀመረ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት የመገናኛ ብዙኃን፣ መረጃ እና ምርምር ቋትን ሥራ አስጀመረ፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቱ ከነሐሴ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲያዘጋጀው እንደቆየ የገለፀውን አገልግሎቱን ‹‹ሚዲያ፣ ኢንፎርሜሽን እና ምርምር ቋት›› ሲል ይፋ አድርጓል፡፡

አገልግሎት የጀመረው የበይነ መረብ ቋት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ታሪክ፣ እድገት፣ ተቋማዊ ሁኔታ እንዲሁም መገናኛ ብዙኃንን የሚዳስሱ የጥናትና የምርምር ውጤቶች፣ የጋዜጠኞችን ግለ ታሪኮችና ሌሎች ከ20 በላይ ልዩ ልዩ ይዘቶችን በአንድ ገጸ ድር ያቀፈ ነው ተብሏል፡፡

ተቋሙ ለዋልታ በላከው መግለጫ ከፎዮ አይ ኤም ኤስ በተገኘ 93 ሺሕ ዶላር እየተከወነ ያለው ይኸው ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በዓይነቱ የተለየ መሆኑን ጠቅሶ በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃንና ተግባቦት ዙሪያ ያለውን የመረጃ ተደራሽነት ክፍተት ለማጥበብ ያግዛል ብሏል፡፡

ለስኬቱ ጋዜጠኞች፣ ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሁም የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ማኅበራት እንዲያግዙም ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያተኮሩ ከ10 በላይ ፕሮጀክቶችን ተግብሯል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.0K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ