Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.24K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 344

2022-05-14 13:46:48
የቦሌ ክፍለ ከተማ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ሥራ አስጀመረ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የቦሌ ክፍለ ከተማ ከክረምት በጎ ተግባራት ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነውን የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ሥራ በይፋ አስጀምሯል።

ቤት የማደስ ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አለምፀሃይ ሽፈራው እንደገለጹት በዘንድሮ ክረምት ከ300 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ቤት የማደስ ተግባር ይከናወናል።

አቅመ ደካሞቹ ቤቶቻቸው ከላይ የሚያፈሱ፣ የተጎሳቆሉ እና የተጎዱ በመሆናቸው በተለይ በክረምት ወራት የሚደርስባቸው እንግልት ከፍተኛ እንደሆነም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስታውሰዋል።

ከዚህ ቀደምም ክፍለ ከተማው የ110 አቅመ ደካሞችን ቤት አድሶ እና አስፈላጊውን የቤት ቁሳቁስ አሟልቶ ማስረከቡን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በክፍለ ከተማው ከ41 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ለስድስት ወር የሚሆን ማዕድ ለማጋራት የታቀደ ሲሆን እስካሁን ከ31 ሺሕ በላይ ለሚሆኑት ማጋራት መቻሉንም አስረድተዋል።

ክፍለ ከተማው ለሚያከናውናቸው ቤት የማደስ እና ማዕድ የማጋራት ተግባራት የክፍለ ከተማው ባለሃብቶች ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ለድጋፉ አመሰግነዋል።

ከዚህ ቀደም ቤቶቻቸው የታደሰላቸው ነዋሪዎችም ክረምት በመጣ ቁጥር ይደርስባቸው የነበረው እንግልት እንደቀረላቸው ገልጸው ይህ እንዲሆን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በነስረዲን ኑሩ
1.3K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:22:50
ሕወሓት ለዳግም ጦርነት ዝግጅቱ ከስህተቱ አለመማሩን የሚያረጋግጥ ነው - አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በትግራይ አጎራባች ክልሎች ዳግም ወረራ ለመፈፀም እያደረገ ያለው ዝግጅት ከስህተቱ አለመማሩን እና በፀረ-ሕዝብነቱ መቀጠሉን የሚያረጋግጥ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

ለትግራይ ክልል ሕዝብ ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዳይሆን አሸባሪ ቡድኑ ለማስተጓጎል የሚያደርገውን ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር እንዲያቆም ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ለዳግም ጦርነት በግልጽ እየተዘጋጀ መሆኑን ዓለም ዐቀፍ ጋዜጠኞች ጭምር እያጋለጡ መሆኑን ጠቅሰው "ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል እወርዳለሁ" የሚል የጥፋት አጀንዳውን ቀጥሎበታል ብለዋል።

የሰብአዊ ድጋፍና የግብርና ሥራ እንዳይስተጓጎል መንግሥት ያወጀውን የተኩስ አቁም ለዳግም ጥፋት እየተዘጋጀበት መሆኑንም ገልጸዋል።

በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች መንግሥት የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ በማድረግ ላይ ቢሆንም አሸባሪ ቡድኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች የማስተጓጎል ተግባር ስለመፈጸሙ ጠቅሰዋል።

ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶችም የተሳለጠ ሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ ማድረግ እንዲችሉ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

የአሸባሪ ቡድኑ እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ ከስህተቱ የማይማርና በፀረ-ሕዝብ ተግባሩ መቀጠሉን ማረጋገጫ ነው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች ለአርሶ አደሩ የዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት ተደራሽ በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው በትግራይ አካባቢ ግን ለግብርና ሥራውም ይሁን ለሰብአዊ አቅርቦቱ አሸባሪው ሕወሓት እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.8K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:06:41
"የጉሚ በለል" ውይይት በህገ-ወጥ ስደት ዙሪያ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) 22ኛው ዙር "የጉሚ በለል" ውይይት የህገ-ወጥ ስደት መንስኤው፣ የሚያስከትለው ጉዳት እና መፍትሄው በሚል መሪ ሃሳብ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ በርካታ ዜጎች ህይወታችንን እንቀይራለን በሚል ወደ ተለያዩ ሀገራት በህገ-ወጥ መንገድ በመሰደድ ለስቃይ እንደሚዳረጉ ተገልጿል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የህገ-ወጥ ስደት የተበራከተበት ምክንያት ሰዎች ህይወታቸውን ለመቀየር ካላቸው ህልም የሚመነጭ ነው ብለዋል።

የህገ-ወጥ ስደት ጉዳት ያለውና በስደቱ ምክንያት ሰዎች በሞራል እንዲሁም በአካል እና የተለያዩ ኢ-ሰብዓዊ ጉዳቶች እንደሚያደርስ ጠቁመዋል።

ይህን ችግር ለመፍታት መንግሥት የሥራ እድሎችን በማመቻቸትና ለዜጎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ህገ-ወጥ ስደትን መቀነስ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የህገ-ወጥ ስደት መበራከት የኢኮኖሚ ችግር መሆኑን ገልጸው የሥራ እድል መፍጠር እና ዜጎች በተለይም ወጣቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በህገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያዘዋውሩ ደላሎችን በመከታተል መንግሥት እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም ተጠቅሷል።

በቡላ ነዲ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.7K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 11:21:46
አገራዊ የምክክር መድረኮች በቀጣይ ዓመት ኅዳር ወር ይጀመራሉ ተባለ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) አገራዊ የምክክር መድረኮች በቀጣይ ዓመት ኅዳር ወር እንደሚጀመሩ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።

አገራዊ ምክክሩ የቅድመ-ዝግጅት፣ ዝግጅት፣ ምክክር እንዲሁም የትግበራና ክትትል የተሰኙ አራት ምዕራፎች መኖራቸውን የገለጹት የኮሚሽኑ ሰብሳቢ እስካሁን ባለው ሂደት የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች መካከል ዋነኛ የሆነው የእቅድ ሥራ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ተጠናቆ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና ግምገማ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

በተያዘው ክረምት ደግሞ የዝግጅት ምዕራፎች ተጠናቀው በመጭው ዓመት ኅዳር ወር ላይ የምክክር መድረኮች እንደሚጀመሩ ነው የገለጹት።

የዝግጅት ምዕራፎችም የተሳታፊ ልየታና ሥልጠና እንዲሁም ለአገራዊ መግባባት የተሻሉ አጀንዳዎችን መለየት የሚሉ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ገልጸዋል።

የውይይት አጀንዳ የሚቀረጸው ከታችኛው ኅብረተሰብ ክፍል ፍላጎት እንደሆነ ጠቅሰው ከዚህ አኳያ ገለልተኛ የሕዝብ ወኪሎች በተገቢው መልኩ ይለያሉ ነው ያሉት።

ኮሚሽኑም መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሚዲያ ክፍሉን እያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የወሰንና ማንነት እንዲሁም በዕርቀ-ሰላም ኮሚሽኖች የተጠኑ የጥናት ሰነዶችን መረከቡን አንስተው ከሰነዶችም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በግብዓትነት ይጠቀማል ብለዋል። https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/5424395494307854
345 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 10:50:27
መንግሥት አልሻባብ በመሃል ሀገር ሊፈጥር ያቀደውን ሽብር ማክሸፉን ገለጸ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) መንግሥት አልሻባብ ከአሸባሪዎቹ ሕወሓት እና ሸኔ ጋር በጥምረት በመሆን በመሃል ሀገር ሊፈጥር ያቀደውን ሽብር በወሰደው እርምጃ ማክሸፉን ገለጸ፡፡

እስካሁን በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር 45 ተላላኪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል ያሉት ሚኒስትሩ በዚህም 105 ክላሽ እንኮቭ ጠመንጃ፣ 13 ብሬል፣ 4 መትረዬስ እና 4 ስናይፐር መሳሪያዎች በቤተ እምነትም ውስጥ ጭምር መያዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

የተጎዱ መስጊዶችንና አብያተክርስቲያናት መልሶ ለመገንባት መንግሥት ወደ ሥራ መግባቱንም ገልጸዋል፡፡

የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በአማራ ክልል ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ህግ በማስከበርና ክልሉን ወደ ተረጋጋ እንቅስቃሴ ለመመለስ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ የሚያደርግ ሀሳብ ተነድፎ ወደ ተግባር እንደተገነባም አመልክተዋል፡፡ https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/5424341247646612

በብርሃኑ አበራ
698 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 10:36:29
በክልሉ ለአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ቅድመ ዝግጅት ተደረገ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄቶሳ ወረዳ ዳያ ዳበሶ እና ጉሪ ቀበሌ በሚቀጥለው ወር ለሚካሄደው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ቅድመ ዝግጅት ተደረገ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኤልያስ ከድር በክልሉ በድርቅ እየተጎዱ ለሚገኙት አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የተፈጥሮ ደን ጥበቃ እና ችግኝ ተከላ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው በአየር ለውጥ ምክንያት ድርቅ እንዳይፈጠር ችግኝ መትከል እና የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አስቴር ጌታሁን (ከአርሲ ዞን)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
767 views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 10:34:14
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ እየሰጠ ያለ መግለጫ - በቀጥታ https://fb.watch/c-5eOPUwWh/
721 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 10:27:34
ወታደራዊ ሥልጠና ዝግጁነትን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የተደረገው ወታደራዊ ሥልጠና ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና አለው ሲሉ በደቡብ ዕዝ የኮር ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ነገሪ ቶሊና ገለጹ።

ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ አመራሮች በመታገዝ የተደረገው ወታደራዊ ሥልጠና የሠራዊቱን የማድረግ አቅም ከማሳደጉ በተጨማሪ የተጣለበትን ሀገራዊ አደራ በብቃት ለመወጣት ያስችለዋል ብለዋል።

በከፍተኛ ጥናት ላይ ተመሥርቶ ለወራት ሲደረግ በቆየው የተቀናጀ ወታደራዊ ልምምድ ሠራዊቱ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው የገለጹት ሜጀር ጄኔራል ነገሪ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁነቱ የላቀ ነው ብለዋል።

ሥልጠናውን ከተሳተፉ አመራሮች መካከል ሌተናል ኮሎኔል መለስ ሙሉ እና ሻለቃ ተክለጻዲቅ በበኩላቸው ሥልጠናው በተግባር ተደግፎ በተለያየ መልከኣ-ምድር እና የአየር ፀባይ መሰጠቱ ሠራዊታችንን ለማንኛውም ተልዕኮ ዝግጁ ያደርገዋል።

በተከታታይ ወራት ባደረግናቸው ሥልጠናዎች ከፍተኛ አቅም ገንብተናል ያሉት አመራሮቹ በአሁኑ ወቅት ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመፈፀም በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
765 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 10:18:31
የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህልን በማስቀጠል አንዳችን ላንዳችን ደጀን መሆን ይገባል ተባለ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የቆየውን የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን በማስቀጠል አንዳችን ላንዳችን ደጀን መሆን ይገባናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

ምክትል ከንቲባው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በመገኘት የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ ተግባር ባስጀመሩበት ወቅት የቆየውን የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን በማስቀጠል አንዳችን ላንዳችን ደጀን መሆን ይገባናል ብለዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽታዬ መሀመድ በበኩላቸው የቤት እድሳት ሥራችን በቀጣይ ሁለት ወራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን የክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

አመራሮች ከቤት እድሳቱ በተጨማሪ "ቆሻሻ መጣል ይብቃ" በሚል እየተካሄደ ባለው የፅዳት ዘመቻ ላይም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
825 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 09:51:41
ሕወሓት ሰላማዊ ዜጎችን እያሰረ መሆኑ ተገለጸ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት አስገድዶ ወደ ግዳጅ ያስገባቸው ምልምሎች መካከል ለመሸሽ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ዘመዶቻቸው የታሰሩባቸው ሦስት ሴቶች ገለፁ።

አሸባሪው ሕወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎችን ያሳተፈ ቅስቀሳ በማድረግ ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ናቸው፡፡

ሱዳንስ ፖስት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በኢሜይል መልዕክት አድርሰውኛል ብሎ እንደዘገበው ሕወሓት የሚያደርገው ጦርነት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጋር ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሰላማዊ ዜጎች በማሰር ትርጉም የለሽ ተግባር እየከወነ ነው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እና ሰላማዊ ዜጎች የሕወሓትን የሽብር ተግባር ለመቀላቀል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሲታሰሩ ይህ የመጀመሪያ አይደለም ያሉት ነዋሪዎቹ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ሕወሓት ጦርነት እንዳይቀጥልና ሰላምን እንዲቀበል ጫና ማድረግ እንደሚጠበቅበት ጠይቀዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.0K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ