Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.24K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 343

2022-05-14 19:14:23
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በስልጤ ዞን የምክክር መድረክ አካሄደ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከስልጤ ዞን አስተዳደር፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

ጉባኤው በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የተከሰተውን ጉዳት ተከትሎ የተፈጠረውን ቅሬታ ለማርገብ እና ሂደቱን ለመደገፍ መድረኩን ያዘጋጀ ሲሆን በዚህም ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማትን ጎብኝቷል።

የአብሮነት እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጉባኤው በሰፊው እንደሚሠራ የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ አስታውቀዋል።

በግለሰቦች እና ቡድኖች የተጀመረን ግጭት በሃይማኖት ተቋማት በማላከክ ሽፋን መስጠት ተገቢነት እንደሌለው ጠቅሰው የእምነት ግጭት ማሳያም ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም ሲሉ ተናግረዋል።

ጉባኤው በውይይቱ ዘላቂ የሆነ የመፍትሔ አቅጣጫ ላይ ባለ ስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። https://www.facebook.com/489211707826282/posts/5425384887542248/
1.3K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 19:05:01
የማታ 1፡00 ዜና በቀጥታ ከዋልታ ቴቪ ግንቦት 6/2014
https://fb.watch/c-z7H7vEZf/
1.1K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 18:58:50
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የክብር ዶክትሬት ሰጠ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው መርኃ ግብር ለተሸላሚቹ የክብር ዶክትሬቱን አበርክተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በልማትና ሌሎችም ተግባራት የላቀ ሚና የተወጡ ናቸው ተብሏል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ 8ኛው ፕሬዝዳንት በመሆን እየመሩ ያሉት አዴሲና በአኅጉሪቷ የድህነት ቅናሳ፣ የትምህርት መስፋፋት፣ የሥራ ፈጠራ እና ሌሎችም ተግባራት ላይ ውጤታማ ሥራ ማከናወናቸው ይታወቃል።

በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሲቪል ሥራዎች ግንባታ ስኬታማነት ኃላፊነታቸውን በብቃት የተወጡ ናቸው።

እንደኢዜአ ዘገባ በግድቡ ግንባታ ስኬት የላቀ ሚና ለነበራቸው ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.3K viewsedited  15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 17:42:10
ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጠ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ነጥብ 75 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና የመስጠት መርኃግብር አካሄደ።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሙያ መስኮች በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ከሁለት ዓመት በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ነው የፕሬዝዳንትነት አምባሳደርነት ማዕረግ የሰጠው።

በእውቅና መርኃግብሩ ተማሪዎቹ በአማራ ክልል ፖሊስ የማርሽ ባንድ ታጅበው በከተማው ትርኢት እየተካሄደ ነው።

ዩኒቨርሲቲው የእውቅና መርኃ ግብሩን እያካሄደ ያለው ለ3ኛ ዙር እንደሆነም ተመላክቷል።

መስከረም ቸርነት (ከደብረ ማርቆስ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
1.7K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 15:32:45
አሸባሪው ሕወሓት በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበረቸውን 7 ሺሕ የሚጠጉ ንፁሃን መግደሉን ጥናት አመለከተ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በጦርነቱ ምንም ዓይነት ተሳትፎ ያልነበረቸውን 6 ሺሕ 985 ንፁሃን ዜጎች መግደሉን ጥናት አመለከተ፡፡

ከዚህ ውስጥ 1 ሺሕ 797ቱ በጅምላ ተጨፍጭፈው የተገደሉ መሆናቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።

ቡድኑ በፈፀመው ወረራ ከ240 ሺሕ በላይ ሰዎች የሰብኣዊ ጉዳት ሰለባ ሲሆኑ 7 ሺሕ 460 ዜጎች ደግሞ በኃይል ታፍነው በመወሰዳቸው የት እንዳሉ አልታወቀም፡፡

የሽብር ቡድኑ ባደረሰው አስከፊ የሰብኣዊ ጉዳት የአስገድዶ መድፈር ሰለባ የሆኑት 1 ሺሕ 782 ዜጎች መሆናቸው ተነግሯል።

አሸባሪው እና ወራሪው ቡድን ባካሄደው ወረራ በአማራ ክልል ያደረሰውን ጉዳት በተመለከተ በጥናት ውጤቱ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

ጥናቱ አምስት ወራትን የወሰደ ሲሆን በአስር ዩኒቨርሲቲዎች እና በብሔራዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት ትብብር መደረጉ ተገልጿል፡፡

እንደኤፍቢሲ ዘገባ ጥናቱ ቡድኑ በወረራ ይዟቸው ነፃ የወጡ የክልሉን 8 ዞኖች ያካተተ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
277 viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 15:19:26
በክልሉ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሠራ ነው ተባለ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ለመተካት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አስታወቁ፡፡

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዶገለ ወረዳ ስንዴን ለማልማት በተዘጋጀ እርሻ ጉብኝት ተደርጓል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ በክልሉ ስንዴን ለማልማት 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት እና 200 ሺሕ ኩንታል ምርጥ ዘር መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ከመተካት በተጨማሪ ለኑሮ ውድነቱ መፍትሔ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ ጋና ማሃማድ በዞኑ በአጠቃላይ ለክረምት ግብርና የተዘጋጀው 586 ሺሕ 388 ሄክታር መሬት መሆኑን ገልጸው ከዚህም ከ20 ነጥበ 5 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ለማስገባት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አስቴር ጌታሁን (ከአርሲ ዞን)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
432 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 15:05:23
ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ከጸጥታ አካላት ጋር ተወያዩ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከፌዴራልና ከክልል ፀጥታ ኃይሎች አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሶማሌ ክልል የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ ንግድ መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የክልሉን አጠቃላይ ሰላም እና ደኅንነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
556 views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 14:58:12
ከማኅበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማኅበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ ኃይል አሳሰበ።

ግብረ ኃይሉ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች በይዘትም ሆነ በአፈጻጸም ስልታቸው ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ባሻገር በርካታ ግለሰቦች የጉዳቱ ሰለባ እንዲሆኑ እያደረገ ነው።

የማጭበርበር ወንጀሎቹ በዋናነት የሚፈጸሙት በውጭ አገር የሚኖሩ፣ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያውያን በስፋት የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ማለትም ፌስቡክ፣ ኢ-ሜይል፣ ዋትስአፕ፣ ቴሌግራም፣ ኢንስታግራም፣ ኢሞና ቫይበርን በመጥለፍና ወዳጅ መስሎ በመቅረብ ወንጀሎቹ እንደሚፈጸሙ ከተደረገው ክትትል ማወቅ እንደተቻለም ተገልጿል። https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/photos/a.489214534492666/5424636457617091/
616 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 14:53:07
ጠ/ሚ ዐቢይ ለሼህ መሐመድ ቢን ዛይድ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የአንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት "በሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በሳል አመራር በሀገሪቱ ዕድገት እና ብልጽግና እንዲመጣ ልባዊ ምኞቴ ነው" ብለዋል።

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን የሀገሪቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያንን የሚተኩ ይሆናል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
645 views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 14:42:51
ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ሠላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የከተማዋ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ጋር የተለያዩ የጸጥታ ሥራዎች ሲሰራ ቆይቷል።

በተለይም ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከል ከኅብረተሰቡ ጋር ባካሄደው ተግባራት የተለያዩ አጀንዳ ያነገቡ አካላት የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉትን ጥረት ለማክሸፍ ተችሏል ብለዋል።

ለአብነትም በመዲናዋ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ድምጽ አልባ የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ሕገ-ወጥ የሀገር ውስጥና የውጭ አገራት ገንዘቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል።

ለዚህም ኅብረተሰቡ ጥቆማ ከመስጠት ጀምሮ የአካባቢው ሰላምን ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላቱ ጋር ያደረገው ዘርፈ-ብዙ ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ መሆኑን ገልጸው ይህንን ሠላም ዘላቂ ለማድረግ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

ጸጥታን የሚያደፈርሱ የተለያዩ ጉዳዮችን በንቃት እንዲከታተልም ጥሪ አቅርበዋል።
በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ኅብረተሰቡን ለማሸበር ከሚነዙ የተለያዩ መረጃዎች ኅብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅም ተናግረዋል፡፡

በዚህም መዲናዋን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ አጀንዳ ያነገቡ አካላትን ለመከላከልና ለመቆጣጠርም ሰፊ እድል እንደፈጠረለትም ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
795 views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ