Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.03K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-10 19:59:38
ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ስምምነት ሳይደረስ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከወላጆች ጋር በነበረ ውይይት ስምምነት ላይ መድረስ ያልተቻሉባቸው መድረኮችን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡

የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ አቅጣጫ ብቻ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
3.5K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:47:06

3.0K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:00:27 ዋልታ ምሽት ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ግንቦት 2/2015

https://fb.watch/kruhlgaVVn/
3.1K viewsedited  16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 18:37:42
ፍርድ ቤቱ በነሲሳይ አውግቸው ጉዳይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ፈቀደ

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) ፍርድ ቤቱ እነሲሳይ አውግቸው እና ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ ስድስት ግለሰቦች በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ፈቀደ።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ የ14 ቀን ጊዜ ለፖሊስ የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ በትናንት ዕለት በተጠርጣሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያብን፣ ሰለሞን ልመንህ እና ሄኖክ አዲስ፣ ነዋይ ዮሐንስ እና ጎበዜ ሲሳይ ላይ ፖሊስ ያቀረበውን የጥርጣሬ መነሻዎችን እና የተጠርጣሪ ጠበቆች ያቀረቡትን መከራከሪያ ነጥብ ተመልክቷል።

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid036oBk43iYRsWHcD1qxxwFVyQovxqRBXwK3CiTBYGgLcreLuTkwb1fcikZqnwL3yAHl
3.1K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 18:12:47

2.9K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 17:14:08
142 ግብር ከፋዮች ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በስም የዘረዘራቸው 142 ግብር ከፋዮች ያሳተሟቸው እና ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን አስታወቀ።

በስም የተዘረዘሩት ግብር ከፋዮች ለሦስት እና ከሦስት ዓመት በላይ ግብር ያላሳወቁ መሆናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ ያሳተሟቸው ደረሰኞችም በተለያየ የታክስ አካውንቶች እዳ ያለባቸው ናቸው ብሏል።

እነዚህ ደረሰኞችን በማናቸውም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ አገልግሎት ላይ ውለው የተገኙ ከሆነ ሕጋዊነት እንደሌላቸው ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም ግብር ከፋዮች ይህንኑ በመገንዘብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የገቢዎች ሚኒስቴር አሳስቧል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0PyqeU3E7bTSPGK8ETNCkqmLT4Sjzu5N61MFHhyvTuyYwz6RaJsUYQupHxEmSBYEql
3.3K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:11:42

3.3K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 13:41:10
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ተጠባቂ ጨዋተ ዛሬ በኢንተር ሚላንና ኤስ ሚላን መካከል ይከናወናል

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ተጠባቂ ጨዋተ ዛሬ በኢንተር ሚላን እና ኤስ ሚላን መካከል ይከናወናል፡፡

ከታላላቅ የዓለማችን ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነው ሚላን ደርቢ ከ2005 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ይከናወናል፡፡

በሴሪኣው ያላቸው ፉክክር እንደተጠበቀ ሆኖ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ስኬታማ በመሆንና በርካታ ክብሮችን በማሳካት ኤሲሚላን ቀዳሚው ነው፡፡

በዚህም ከሪያል ማድሪድ ቀጥሎ 7 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ኤስ ሚላን ሲያሳካ ኢንተርሚላን 3 ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል፡፡

ዘንድሮ በሴሪኣው ባከናወኑት 34 ጨዋታ 63 ነጥብ በመሰብሰብ ኢንተርሚላን 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤሲሚላን በሁለት ነጥቦች አንሶ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የአምናው የስኩዲቶ ሻምፒዮን በቅርብ ሳምንታት ጨዋታዎች ወደ ቀደመ ብቃቱ እየተመለሰ የሚገኝ ሲሆን በሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ናፖሊን በመርታት ነበር ወደ ዛሬው ጨዋታ ማለፉን ያረጋገጠው፡፡ ኢንተርሚላን በበኩሉ ቤኔፊካን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ፖርቹጋላዊው ራፋኤል ሊኣኦ በጉዳት ለኤሲሚላን ግልጋሎት የማይሰጥ ሲሆን ጨዋታው በሳንሴይሮ ጁሴፔ ሜይዛ ስታዲየም ይከናወናል፡፡

በሌዊ በለጠ
3.7K views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:04:54

3.5K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:02:52
በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ 10 ዞኖች ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ድጋፎች መደረጉ ተገለጸ

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው ዓመት በድርቅ ለተጎዱ 10 ዞኖች ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የተለያዩ ድጋፎች መደረጉን የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ ገለጸ።

ድጋፉ ከፌዴራልና ከክልሉ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከክልሉ ህዝብ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተገኘ መሆኑም ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል የቡሳ ጎኖፋ ኃላፊ ሀብታሙ ሲሳይ እንደገለጹት የኦሮሞ ህዝብ የመደጋገፍ፣ መተጋገዝና የመረዳዳት ባህል የሆነው ቡሳ ጎኖፋ ስርዓት ተቋማዊ እንዲሆን ተደርጎ እሴቱን ለማጎልበት ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የክልሉ መንግስት ቡሳ ጎኖፋን በአዋጅ በማቋቋም ህዝቡ ወደ ነበረበት የገዳ ስርዓት እሴት እንዲመለስ ማስቻሉን የገለፁት ኃላፊው በዚህም በዘንድሮው ዓመት በ10 የክልሉ ዞኖች የተከሰተውን ድርቅ በራስ አቅም ለመቋቋም ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid032dPsxaNcrokjG9ZFCukjvtmD6jf7aLbRii531sygUwyvSyzVuhYovPguBeV5myxpl
3.3K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ