Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ 10 ዞኖች ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ድጋፎች መደ | AddisWalta - AW

በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ 10 ዞኖች ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ድጋፎች መደረጉ ተገለጸ

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው ዓመት በድርቅ ለተጎዱ 10 ዞኖች ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የተለያዩ ድጋፎች መደረጉን የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ ገለጸ።

ድጋፉ ከፌዴራልና ከክልሉ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከክልሉ ህዝብ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተገኘ መሆኑም ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል የቡሳ ጎኖፋ ኃላፊ ሀብታሙ ሲሳይ እንደገለጹት የኦሮሞ ህዝብ የመደጋገፍ፣ መተጋገዝና የመረዳዳት ባህል የሆነው ቡሳ ጎኖፋ ስርዓት ተቋማዊ እንዲሆን ተደርጎ እሴቱን ለማጎልበት ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የክልሉ መንግስት ቡሳ ጎኖፋን በአዋጅ በማቋቋም ህዝቡ ወደ ነበረበት የገዳ ስርዓት እሴት እንዲመለስ ማስቻሉን የገለፁት ኃላፊው በዚህም በዘንድሮው ዓመት በ10 የክልሉ ዞኖች የተከሰተውን ድርቅ በራስ አቅም ለመቋቋም ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid032dPsxaNcrokjG9ZFCukjvtmD6jf7aLbRii531sygUwyvSyzVuhYovPguBeV5myxpl