Get Mystery Box with random crypto!

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ተጠባቂ ጨዋተ ዛሬ በኢንተር ሚላንና ኤስ ሚላን መካከል ይከ | AddisWalta - AW

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ተጠባቂ ጨዋተ ዛሬ በኢንተር ሚላንና ኤስ ሚላን መካከል ይከናወናል

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ተጠባቂ ጨዋተ ዛሬ በኢንተር ሚላን እና ኤስ ሚላን መካከል ይከናወናል፡፡

ከታላላቅ የዓለማችን ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነው ሚላን ደርቢ ከ2005 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ይከናወናል፡፡

በሴሪኣው ያላቸው ፉክክር እንደተጠበቀ ሆኖ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ስኬታማ በመሆንና በርካታ ክብሮችን በማሳካት ኤሲሚላን ቀዳሚው ነው፡፡

በዚህም ከሪያል ማድሪድ ቀጥሎ 7 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ኤስ ሚላን ሲያሳካ ኢንተርሚላን 3 ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል፡፡

ዘንድሮ በሴሪኣው ባከናወኑት 34 ጨዋታ 63 ነጥብ በመሰብሰብ ኢንተርሚላን 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤሲሚላን በሁለት ነጥቦች አንሶ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የአምናው የስኩዲቶ ሻምፒዮን በቅርብ ሳምንታት ጨዋታዎች ወደ ቀደመ ብቃቱ እየተመለሰ የሚገኝ ሲሆን በሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ናፖሊን በመርታት ነበር ወደ ዛሬው ጨዋታ ማለፉን ያረጋገጠው፡፡ ኢንተርሚላን በበኩሉ ቤኔፊካን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ፖርቹጋላዊው ራፋኤል ሊኣኦ በጉዳት ለኤሲሚላን ግልጋሎት የማይሰጥ ሲሆን ጨዋታው በሳንሴይሮ ጁሴፔ ሜይዛ ስታዲየም ይከናወናል፡፡

በሌዊ በለጠ