Get Mystery Box with random crypto!

142 ግብር ከፋዮች ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን | AddisWalta - AW

142 ግብር ከፋዮች ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

ግንቦት 2/2015 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በስም የዘረዘራቸው 142 ግብር ከፋዮች ያሳተሟቸው እና ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ ዓላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን አስታወቀ።

በስም የተዘረዘሩት ግብር ከፋዮች ለሦስት እና ከሦስት ዓመት በላይ ግብር ያላሳወቁ መሆናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ ያሳተሟቸው ደረሰኞችም በተለያየ የታክስ አካውንቶች እዳ ያለባቸው ናቸው ብሏል።

እነዚህ ደረሰኞችን በማናቸውም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ አገልግሎት ላይ ውለው የተገኙ ከሆነ ሕጋዊነት እንደሌላቸው ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም ግብር ከፋዮች ይህንኑ በመገንዘብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የገቢዎች ሚኒስቴር አሳስቧል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0PyqeU3E7bTSPGK8ETNCkqmLT4Sjzu5N61MFHhyvTuyYwz6RaJsUYQupHxEmSBYEql