Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ እና ብራዚል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ ግንቦት 28/2015 | AddisWalta - AW

ኢትዮጵያ እና ብራዚል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ብራዚል የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በኢንቨስትመንት፣ በአቪዬሽን፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በማእድን እና በታዳሽ ሃይል በትብብር መስራት እንደሚችሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ በበኩላቸው መንግስታቸው በስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማስታወቃቸውን ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡