Get Mystery Box with random crypto!

ግምቱ ከ355 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ዋለ ግንቦት 28/2015 (ዋል | AddisWalta - AW

ግምቱ ከ355 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) ከግንቦት 18 እስከ 24/2015 በተደረገው ክትትል ግምታቸው ከ355 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

2 መቶ 54 ሚሊዮን የገቢ እና 101 ነጥብ 8 ብር የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮሚሽኑ የተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት አማካኝነት መሆኑም ተገልጿል፡፡

አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ናቸው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዙ ነው የተገለጸው፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ሶስት ግለሰቦች እና አራት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ኮሚሽኑ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ በረቀቀ ሁኔታ የሚፈጸም እና በባህሪው ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታት ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡