Get Mystery Box with random crypto!

በስፖርት ጉዳት ህክምና ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው ግንቦት 28/2015 ( | AddisWalta - AW

በስፖርት ጉዳት ህክምና ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) በባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ለህክምና ባለሙያዎች በስፖርት ጉዳት ህክምና ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ።

ስልጠናው እየተሰጠ ያለው ከስፔን ዩንቨርስቲ እና ስፔን ላሊጋ ከመጡ በዘርፋ ልምድ እና እውቀት ባላቸው የፊዝዮትራፒ እና የህክምና ባለሙያዎች አማካኝነት ነው።

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የስፖርት ህክምና ዴስክ ኃላፊ ዮናስ አለማየሁ ስልጠናው የባለሙያዎች የስፖርት ህክምና ሳይንስ ንግንዛቤ ለማሳደግ፣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፎችን ማግኘትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል ።


በስልጠናው የስፖርት ጉዳትን በመከላከል ፣ በስፖርት ጉዳት ህክምና ፣ በአመጋገብ እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስን በመጠቀም ስፖርተኞች በፍጥነት ከጉዳት ማገገም በሚችሉበት ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

በስልጠናው ከተለያዩ ሆስፒታሎች የመጡ የህክምና ባለሙያዎች ፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፣ በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች ለሙያው ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡