Get Mystery Box with random crypto!

AddisWalta - AW

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW A
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth — AddisWalta - AW
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 45.03K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-05 10:21:58
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ያካሄደውን የሕዝበ ውሳኔ ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ

ሰኔ 28/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል።

ምክር ቤቱ 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት መድረክ ነው እያዳመጠ የሚገኘው፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ሲሆኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔ አስፈጽሞ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔውን በማስፈጸም ያዘጋጀው ሪፖርት እንደሆነ ገልጸዋል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
805 viewsedited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 09:54:39

930 views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 09:06:14

1.2K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 20:10:20
የጂቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ሸገር ከተማ ገባ

ሰኔ 27/2015(ዋልታ) በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የተጓዘው የጂቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ሸገር ከተማ ገብቷል።

በጅቡቲ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታ ሲራጅ ዑመር የተመራው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ ሸገር ከተማ በሚገኘው ፉሪ-ለቡ የባቡር ጣቢያ ሲደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የጅቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ በባቡር ተጉዞ ነው ወደ ኢትዮጵያ የገባው።

ጉብኝቱ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ መስክ የኢትዮ-ጅቡቲ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

የልዑክ ቡድኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ሲሆን 112 አባላትን ያካተተ መሆኑም ተጠቅሷል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ አባላት በፉሪ ለቡ ባቡር ጣቢያ ውስጥ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ወንድማማችነት ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

የቡድኑ አባላት በትላንትናው እለት በድሬዳዋ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ የተሳተፉ ሲሆን አሮጌውን የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡርን ጨምሮ ሌሎች ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።

ዛሬም ወደ ፉሪ-ለቡ የባቡር ጠቢያ ከመምጣታቸው አስቀደሞ በአዳማ ከተማ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

የቡድኑ አባላት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የተለያዩ የህዝብ ለህዝብ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
3.2K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:42:28
የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሰኔ 27/2015 (ዋልታ) የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡


ከንቲባዋ በስማርት ሲቲ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረ የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ለከተማዋ ነዋሪዎች የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ ፣ ፈጣን እንዲሁም የዜጎችን እንግልት የሚያስቀር አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአገልግሎትአሰጣጥ እንዲሻሻል የቴክኖሎጂ ስራዎች በማደራጀት የነዋሪዉን ፍላጎት መሰረት ያደረገና በጥናት የተደገፈ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፤

የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ከንቲባዋ ተቋማት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን በመተግበር የህዝቡን ፍላጎት የሚሟላ አሰራሮች ስለመዘርጋታቸውን መግለጻቸው ከከንቲባ ፅ/ቤጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
2.9K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:03:48

2.7K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:02:43
ዋልታ #ምሽት - ሰኔ 27/2015 https://fb.watch/lz-1AeH6cV/
2.5K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:35:52
የምስራቅ አፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው - ተመራማሪዎች

ሰኔ 27/2015(ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም ትብብራቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪዎች ገለጹ።

የአየር ንብረት ለውጥ ዓለማችንን እየፈተኑ ካሉ ችግሮች መካከል አንደኛው ነው ተብሏል፡፡

ምክንቱ ደግሞ የዓለም ሙቀት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ በአማካኝ በ1 ነጥብ 2 ድግሪ ሴልሺዬስ መጨመሩ ነው፡፡

በዚህም ጎርፍ፣ ድርቅ፣ የዝናብ ወቅት፣ ስርጭትና መጠን መዛባት እንዲሁም የአካባቢ መራቆት የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በዓለም የተለያዩ አካባቢዎች በስፋት ሲከሰቱ ይስተዋላል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጽእኖ ከሚደርስባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/671427648356901?ref=embed_post
2.7K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:30:21
ፕሬዚዳንቷ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ቦርድ አጥኚ ኮሚቴን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

ሰኔ 27/2015 (ዋልታ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝደንት እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂ ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ቦርድ አጥኚ ኮሚቴ አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርን የስራ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ትብብር እና ድጋፍ በሚደረጉባቸው ጉዳዮች ዙሪያም ውይይት ማድረጋቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
2.5K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:02:03
ዋልታ #አመሻሽ - ሰኔ 27/2015 https://fb.watch/lzXue0R1bf/
2.6K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ