Get Mystery Box with random crypto!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ያካሄደውን የሕዝበ ውሳኔ ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ | AddisWalta - AW

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ያካሄደውን የሕዝበ ውሳኔ ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ

ሰኔ 28/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል።

ምክር ቤቱ 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት መድረክ ነው እያዳመጠ የሚገኘው፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ሲሆኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔ አስፈጽሞ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔውን በማስፈጸም ያዘጋጀው ሪፖርት እንደሆነ ገልጸዋል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።