Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ዛሬ በይፋ ይመረቃል ሰኔ 28/2015 (ዋልታ) አዲሱ የኢቢሲ ሚዲ | AddisWalta - AW

አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ዛሬ በይፋ ይመረቃል

ሰኔ 28/2015 (ዋልታ) አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ይመረቃል።

በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ የተገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተቋሙ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል ተብሏል።

በተራራ የተከበበው እና በእፅዋት ያጌጠው አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ዓለም በደረሰበት የሚዲያ ቴክኖሎጂ የተደራጁ ስቱዲዮዎችም ያሉት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለሚዲያው ሠራተኞች ምቹ የሥራ ከባቢን በመፍጠር ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲያድግ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

ኢቢሲ "ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል በአዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክሱ በሁሉም ሚዲየሞቹ አዳዲስ ይዘቶችን እና አቀራረቦችን አካቶ ወደ አድማጭ ተመልካች ለመድረስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁም ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡