Get Mystery Box with random crypto!

የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ | AddisWalta - AW

የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሰኔ 27/2015 (ዋልታ) የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡


ከንቲባዋ በስማርት ሲቲ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረ የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ለከተማዋ ነዋሪዎች የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ ፣ ፈጣን እንዲሁም የዜጎችን እንግልት የሚያስቀር አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአገልግሎትአሰጣጥ እንዲሻሻል የቴክኖሎጂ ስራዎች በማደራጀት የነዋሪዉን ፍላጎት መሰረት ያደረገና በጥናት የተደገፈ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፤

የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ከንቲባዋ ተቋማት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን በመተግበር የህዝቡን ፍላጎት የሚሟላ አሰራሮች ስለመዘርጋታቸውን መግለጻቸው ከከንቲባ ፅ/ቤጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡