Get Mystery Box with random crypto!

የምስራቅ አፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው | AddisWalta - AW

የምስራቅ አፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው - ተመራማሪዎች

ሰኔ 27/2015(ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም ትብብራቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪዎች ገለጹ።

የአየር ንብረት ለውጥ ዓለማችንን እየፈተኑ ካሉ ችግሮች መካከል አንደኛው ነው ተብሏል፡፡

ምክንቱ ደግሞ የዓለም ሙቀት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ በአማካኝ በ1 ነጥብ 2 ድግሪ ሴልሺዬስ መጨመሩ ነው፡፡

በዚህም ጎርፍ፣ ድርቅ፣ የዝናብ ወቅት፣ ስርጭትና መጠን መዛባት እንዲሁም የአካባቢ መራቆት የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በዓለም የተለያዩ አካባቢዎች በስፋት ሲከሰቱ ይስተዋላል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጽእኖ ከሚደርስባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/671427648356901?ref=embed_post