Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል ግንቦት 28/2 | AddisWalta - AW

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሄደዋል።

በሳምንቱ ከተደረጉ ውድድሮች መካከል በስዊድን የተካሄደው የስቶኮልም ማራቶን ይገኝበታል።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በወንዶች አትሌት አሸናፊ ሞገስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ደራራ ሁሬሳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጸጋዬ መኮንን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን በበላይነት ጨርሰዋል።

በሴቶቹ ውድድር አትሌት ሲፋን መላኩ አንደኛ በመውጣት ስታሸንፍ አትሌት ሶሮሜ ነጋሽ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት የኔነሽ ዲንቄሳ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ማጠናቀቃቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡