Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Sale
Packingmachine
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 155

2022-12-31 11:35:22
" ሌሎችም ትምህርት ይሆናል "

በአዲስ አበባ ሳሪስ ፤ ከካዲስኮ ህንፃ ጀርባ ፍሬህይወት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጣቸውን ፈጣን ምላሽ አድንቀው ሁሉም በመስኩ ህዝቡን በተመሳሳይ መልኩ እንዲያስተናግድ ጠይቀዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እንደገለፁት በአካባቢያቸው ሊወድቁ የተቃረቡ 3 የኤሌክትሪክ ፖሎች ስለመኖራቸው ለደቡብ ሪጅን ዞን 6 ሱፐርቫይዘር አቶ ታደሰ ጥላሁን ያመለክታሉ። ወዲያውም በሌላ እንዲተኩ ከተቋሙ ምላሽ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

ይህ ፈጣን ውሳኔ ባይወሰን በንብረት እና በሰው ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ እንደነበር አክለዋል።

ሱፐርቫይዙር እና የመሩት ቡድን በስራቸው መመስገናቸውን የገለፁት እኚሁ የቤተሰባችን አባል ለረጅም ጊዜ ከተቋሙ እንዲህ አይነት ፈጣን ምላሽ አገኝተው እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ይህ ለሌሎችም ህዝብን ለማገልገል የተቋቋሙ ተቋማት መማሪያ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

@tikvahethmagazine
19.9K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 11:35:12
@GTechMobile
Christmas offer

የቴሌግራም ቻናሉን በመቀላቀል በጥሩ ዋጋ የቀረቡ ስልኮችን፣ ታብሌቶችን ይሸምቱ።

በተጨማሪ ስልኮት ላይ ብር በመጨመር(Exchange )የተሻሉ የቅርብ ምርቶችን መውሰድ ይችላሉ ።

https://t.me/GTechMobile
18.4K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 11:35:12
Today is the day to make that effort!
.
.
.
Our telegram
https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
18.8K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 21:14:19
በሁለተኛው ዙር የመፅሀፍት እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ማሰባሰብ ስራ ፦

- አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል (ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ) አንድ Hp ላፕቶፕ ኮምፒዩተር አበርክቷል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል 3000 ብር ወጪ የተደረገባቸውን አጋዥ መፅሀፍት ገዝቶ አበርክቷል።

በዚሁ አጋጣሚ ጃፋር መፅሀፍት ቤትን እናመሰግናለን።

ውድ ቤተሰቦቻችን የሁለተኛው ዙር የማሰባሰብ ስራ ጦርነት ለጎዳቸው ት/ቤቶች የሚውል ሲሆን ፦

- ከ9-12 ክፍል ያሉ ማንኛውም መፅሀፍት
- ከ1-8 ያሉ አጋዥ መፅሀፍት
- ቤት ውስጥ ያገለገለ ኮምፒዩተር
- ፕሪንተር
- የፕሪንተር ቀለም
- ነጭ ወረቀት

በተጨማሪ ለአንድ የህዝብ ቤተ መፅሀፍ ትውልድን የሚያንፁ ልብወልደ ሆነ ማንኛውም መፅሀፍ ማበርከት ትችላላችሁ።

አዲስ አበባ ያላችሁ ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ያላችሁበት ድረስ መምጣት እንችላለን ደውሉልን ፦ 0919743630

ከሰሞኑን በሀዋሳ ያሉ አስተባባሪዎችን እናሳውቃለን።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia
10.7K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 20:30:55
#ንግድባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 12 ወራት በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ብቻ ከ1 ነጥብ 9 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ አድርጓል።

የገንዘብ ልውውጡ የተከናወነው በሞባይል ባንኪንግ፣ ሲቢኢ ብር፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ኤቲኤም እና በፖስ የባንኩ ዲጂታል አገልግሎቶች ነው።

@tikvahethmagazine
15.9K viewsedited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 16:11:33
በደብረ ብርሃን ከተማ አንዲት እናት 4 ህጻናትን በሰላም ተገላገለች

በደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና የጤና ባለሙያ የሆነችው አፀደ ገብረሃና በደብረ ብርሃን በደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተደረገላት የቀዶ ህክምና 2 ሴት እና 2 ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላግላለች።

በሆስፒታል ይህ በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ሀኪም ዶክተር ዳግም ሽመላሽ፤ ታህሳስ 20/2015 ዓ.ም አንዲት እናት 4 ህፃናትን በቀዶ ህክምና ማዋለዳቸውን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት እናትና ህፃናቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የህፃናቶቹ ወላጆች ካለቸው ገቢ አንፃር አሁን ላይ ባለው የኑሮ ሁኔታ ልጆቹን ለማሳደግ የሚቸገሩ በመሆኑ ደጋፊ አካል እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethmagazine
24.2K viewsedited  13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 16:11:17
@GTechMobile
Christmas offer

የቴሌግራም ቻናሉን በመቀላቀል በጥሩ ዋጋ የቀረቡ ስልኮችን፣ ታብሌቶችን ይሸምቱ።

በተጨማሪ ስልኮት ላይ ብር በመጨመር(Exchange )የተሻሉ የቅርብ ምርቶችን መውሰድ ይችላሉ ።

https://t.me/GTechMobile
21.9K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 16:11:00
Today is the day to make that effort!
.
.
.
Our telegram
https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
20.8K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 09:46:24
#እናመሰግናለን

የሁለተኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍት እና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ስራን ተከትሎ ፖሊኪዩር መድሃኒት ቤት 10 ሺህ ብር የወጣባቸውን መፅሀፍት ገዝቷል። በቀጣይ ቀናትም ያስረክባል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል 5 ሺህ ብር የወጣበት መፅሀፍ ልብወለዶችን ጨምሮ አስረክቧል (ለህዝብ ቤተመፅሀፍ)።

ውድ ቤተሰቦቻችን በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለማገዝ ፦
- በቤታችሁ ውስጥ ያለ የማትጠቀሙበት / ያገለገለ ዴስክቶፕ / ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣
- ነጭ ወረቀት
- ፕሪነተር
- የፕሪንተር ቀለም
- ከ9 - 12 ማንኛውም መፅሀፍ
- ከ1-8 አጋዥ መፅሀፍ አበርክቱ።

አዲስ አበባ ያላችሁ #ቅዳሜ እና #እሁድ በየአካባቢያችሁ የምንመጣ ይሆናል ፦ 0919743630

በሀዋሳ ከቀናት በኃላ ይጀምራል።

@tikvahethiopia
12.6K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 19:53:49
#Update

በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት 6 ቀናት በስቴም ፖወርና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ትብብር ሲሰጥ የነበረው የወጣቶች የመጀመሪያ ደረጃ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።

በሥልጠናው በርካታ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ቅዳሜ ዕለት በሚካሄድው የምርቃትና የሰርተፊኬት አሰጣት ሥነ-ስርዓት የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው ማብቂያውን ያገኛል።

ቅዳሜ ዕለት በሚኖረን መርሐግብር ወደ 200 የሚጠጉ ከተሰጡት ስልጠናዎች ከ90 % በላይ የወሰዱ ወጣቶች በአካል ተገኝተው ሰርተፊኬታቸውን የሚቀበሉ ይሆናል። ሌሎች ተሳታፊዎች በሰለጠኑበት ርዕስ ሰርተፊኬታቸውን በዲጂታል መልኩ ይቀበላሉ።

የሚሳተፉት ሰልጣኞች ከዚህ ቀደም በወጣው ማስታወቂያ ቅድሚያ ተመዝግበው ማረጋገጫ የተሰጣቸው ሲሆኑ በቀሩት ቀናት አዲስም ሆነ ማረጋገጫ ከተሰጣቸው ተሳታፊዎች ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

#STEMPower #TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
16.1K viewsedited  16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ