Get Mystery Box with random crypto!

#እናመሰግናለን የሁለተኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍት እና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ስራን ተከትሎ ፖሊኪዩር | TIKVAH-MAGAZINE

#እናመሰግናለን

የሁለተኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍት እና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ስራን ተከትሎ ፖሊኪዩር መድሃኒት ቤት 10 ሺህ ብር የወጣባቸውን መፅሀፍት ገዝቷል። በቀጣይ ቀናትም ያስረክባል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል 5 ሺህ ብር የወጣበት መፅሀፍ ልብወለዶችን ጨምሮ አስረክቧል (ለህዝብ ቤተመፅሀፍ)።

ውድ ቤተሰቦቻችን በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለማገዝ ፦
- በቤታችሁ ውስጥ ያለ የማትጠቀሙበት / ያገለገለ ዴስክቶፕ / ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣
- ነጭ ወረቀት
- ፕሪነተር
- የፕሪንተር ቀለም
- ከ9 - 12 ማንኛውም መፅሀፍ
- ከ1-8 አጋዥ መፅሀፍ አበርክቱ።

አዲስ አበባ ያላችሁ #ቅዳሜ እና #እሁድ በየአካባቢያችሁ የምንመጣ ይሆናል ፦ 0919743630

በሀዋሳ ከቀናት በኃላ ይጀምራል።

@tikvahethiopia