Get Mystery Box with random crypto!

#Update በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት 6 ቀናት በስቴም ፖወርና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ት | TIKVAH-MAGAZINE

#Update

በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት 6 ቀናት በስቴም ፖወርና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ትብብር ሲሰጥ የነበረው የወጣቶች የመጀመሪያ ደረጃ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።

በሥልጠናው በርካታ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ቅዳሜ ዕለት በሚካሄድው የምርቃትና የሰርተፊኬት አሰጣት ሥነ-ስርዓት የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው ማብቂያውን ያገኛል።

ቅዳሜ ዕለት በሚኖረን መርሐግብር ወደ 200 የሚጠጉ ከተሰጡት ስልጠናዎች ከ90 % በላይ የወሰዱ ወጣቶች በአካል ተገኝተው ሰርተፊኬታቸውን የሚቀበሉ ይሆናል። ሌሎች ተሳታፊዎች በሰለጠኑበት ርዕስ ሰርተፊኬታቸውን በዲጂታል መልኩ ይቀበላሉ።

የሚሳተፉት ሰልጣኞች ከዚህ ቀደም በወጣው ማስታወቂያ ቅድሚያ ተመዝግበው ማረጋገጫ የተሰጣቸው ሲሆኑ በቀሩት ቀናት አዲስም ሆነ ማረጋገጫ ከተሰጣቸው ተሳታፊዎች ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

#STEMPower #TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine